Get Mystery Box with random crypto!

በሰሞኑ በሲዳማ ሃገረ ስብከት ለይርባ ደባራ ኬላ መካነ ቅዱሳን አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወቅድስት ድንግል | ከ

በሰሞኑ በሲዳማ ሃገረ ስብከት ለይርባ ደባራ ኬላ መካነ ቅዱሳን አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት ከናንተ ከበጎ አድራጊ ምዕመናን እንደሰበሰብን ይታወሳል።

በዛሬው ቀን ደግሞ ማለትም በ22/01/2014 ዓ.ም በቦታው ተገኝተን ከናንተ የሰበሰብነውን ንዋያትን ለቦታው ገቢ ተደረጋል።

በዚህ መልካም ስራ ላይ የተባበራችሁ ምዕመናን በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልን እናመሰግናለን አምላከ ኤዎስጣቴዎስ የልቦናችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ።

በዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ እየፈለጋችሁ ነገር ግን ግዙ የተባልነው እቃ ተገዝቶ በማለቁ ምክንያት ያልተሳተፋችሁ በቀጣይ የበረከት ስራ እንገናኛል።

አምላክ ሰማያዊ ዋጋችሁን አያስቀርባችሁ።

ያደረስናቸው ንዋየ ቅድሳት ዝርዝር
1. አትሮንስ
2. ዚቅ(ዝክረ ቃል)
3. ተዓምረ ኢየሱስ
4. ሃይማኖተ አበው
5. ድርሳነ ሚካኤል ወገብርኤል ወሩፋኤል...(በአንድ ላይ)
6. መጽሐፈ ሰዓታት
7. ሥርዓተ ሰሞነ ሕማማት
8. መጽሐፈ ግንዘት
9. ሀዲስ ኪዳን ትርጏሜ
10. መጾር መስቀል
11. ጽንሓ
12. አውድ
13. ትልቁ መጽሓፈ ቅዳሴ
14. የመቀደሻ መስቀል( ለቅዳሴ አገልግሎት የሚውል መስቀል)
ብዛት 2
15. ማዕፈድ
16. መዝሙረ ዳዊት

በአጠቃላይ ከእናንተ በተሰበሰበው በ14000ብር

ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን

እግዚአብሔር ይስጥልኝ

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21


@BeGood16