Get Mystery Box with random crypto!

[ Photo ] ሳፈቅርሽ ኖራለሁ የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ | Kalu HD Tube

[ Photo ]
ሳፈቅርሽ ኖራለሁ

የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ብትጠይኝ ብትወጂኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እንነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ

የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!

የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባታፈቅሪኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው።

KALKIDAN