Get Mystery Box with random crypto!

ለዉጥ የለም አትበሉ ሆደ ጩቤ ይሉት~ አፈ ቅቤ ነግሶ በየቀኑ ሰበር~ በየቀኑ ለቅሶ መልካም ዜና | Kalu HD Tube

ለዉጥ የለም አትበሉ

ሆደ ጩቤ ይሉት~ አፈ ቅቤ ነግሶ
በየቀኑ ሰበር~ በየቀኑ ለቅሶ
መልካም ዜና ናፍቆት~ ጆሮ ግንባር ላይ ነው
'ምንሰማው ይቀድማል~ ባ'ይናችን ካየነው


ለ.ው.ጥ.ማ... አለ!
መፈናቀል አለ
መገዳደል አለ
ሴራ ማሴር አለ
መንገድ መዝጋት አለ
ቤት ማቃጠል አለ
ዘረኝነት አለ~ ዱለኝነት አለ
ይህ ሁሉ ተደርጎም~ ማስተባበል አለ።
ለዚህ ስራ ስኬት~ ለትግላችን ሲባል
ዓለም አጨብጭቦ~ ኖቤል ሸልሞናል
ስለዚህ...
እንለወጣለን~ ገና ከመሃሉ
ይሄ ሁሉ እያለ~ ለውጥ አታጣጥሉ
ከዚህ በላይ የለም~ ለውጥ የለም አትበሉ
የኋሊትም ቢሆን~ ብዙ ለውጦች አሉ።

@kaluEntertainmenttt
@kaluEntertainmenttt