Get Mystery Box with random crypto!

........'ፍቅር ማለት ........ የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤ የሶስት ፊደል ጥምረት የቃ | Kalu HD Tube

........"ፍቅር ማለት ........

የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቃል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤

......ፍቅር ማለት ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤

የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."

"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና Aneche ነን ።

KALKIDAN