Get Mystery Box with random crypto!

↳ ቅዱሱ ተራራ ↲(፪ኛ ጴጥ፩÷፲፯-1፲፰ ) ደብረታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡ | "ቃለ እግዚአብሔር "

↳ ቅዱሱ ተራራ ↲(፪ኛ ጴጥ፩÷፲፯-1፲፰ )

ደብረታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡
ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላት መካከል የደብረታቦር በዓል አንዱ ነው፡፡
በእስክንድርያ ግን ዐበይት በዓላቶቻቸው ፯ ናቸው፡: በዚህም ምክንያት ከዐበይት በዓላት ውስጥ አስገብተው ደብረታቦር አይቆጥሩትም ፡ይሁን እንጂ በበዓልነቱ አይከበርም ማለት ግን አይደለም።

ደብረታቦር ወይም የታቦር ተራራ ጌታ በምድረ እስራኤል እየተዘዋወረ በማሰተማር ላይ በነበረበት ዘመን ነሐሴ ፲፫ ቀን ብርሃ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን የገለጠበት ታሪካዊ በዓል ነው፡፡ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚስተምረውና ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር፡(ማቴ ፲፯÷፬) ይህን በዓል ከቅዱስ ዮሐንስ በቀር ፫ቱም ወንጌላውያን በየወንጌሎቻቸው መዝግበውታል(ማር፬÷፪ ፲፫ ፤ ሉቃ ፱÷28-36)
ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም “ ከገናናው ክብር ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ከምስጋናን ተቀብሎአልና እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህ ድምጽ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን” በማለት የተገለጸውን ምስጢር ታላቅነት መስክሮአል(፪ኛ ጴጥ፪÷፲፯-፲፰፣በዓላት በዲ.ን ብርሃኑ አድማስ)
ቅዱሳን ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን ካዩ በኋላ የቃላቸው ትምህርት የእጃቸውም ተአምራት ብቻ ሳይሆን የልብሳቸውም ቁራጭ ጥላቸው ጋኔን ያወጣ ድወይ ይፈውስ ነበር( ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ)
ይህ ተራራ ከገሊላ ባሕር በምስራቅ ደቡባዊ በኩል ፲ ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 572 ኪ.ሜ ከፍታ አለው፡፡የታቦር ተራራ በሐዲስ ኪዳን በግልጽ ባይጠቀስም በብሉይ ኪዳን ግን ተጠቅሶ እናገኘዋለን(መሳ ፬÷፮-፲፬) ቅዱስ ዳዊትም “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፡፡ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች(መዝ 88÷12-13) ይላል፡፡ በደብረታቦር ዲቦራም ዘምራበታለች፡፡

ጌታችን በቂሣርያ ሐዋርያትን “ሰዎች የሰው ልጅን ማን ብለው ይጠሩታል “ በማለት በጠቃቸው ቀን የቀሩት ደቀ መዛሙርት በተራራው ሥር ትቶ ሦስቱን ( ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በተራራው ላይ ሳሉ የጌታችን መልክ ተለውጦ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፡ልብሱም እንደ በረዶ የነጻ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ብርሃነ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን ገለጠ(ሉቃ9÷29)
በደብረታቦር ተራራ ፭ ነገር ተከናውኗል፤
ሙሴና ኤልያስ ሲነጋገሩ ተሰምቷል፡፡
-መልኩ ተለወጠ (ወተወለጠ አርአያሁ በቅድሜሆሙ) (ማቴ ፲፯÷፪) በዚህ ሰዓት በሐዋርያት ላይ ያደረ ሥጋዊ መንፈስ ራቀ፡ በውስጣቸው ያለው የጨለማ ፍርሃት አሰወገደላቸው( ጥርጥርን አለማመን እነዚህን ነገሮች ሀሉ ከልቡናቸው አስወገደላቸው፤ ፡የእግዚአብሔርን ክብር እንዲያስታውሉ አእምሮቸው ብሩህ ሆነ፡፡በደመና ውስጥ ሁኖ የምወልደው የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን የሚል ቃል ተሰማ ( ዝንቱ ወእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ሰምዕዎ) ደመና የእግዚአብሔር የክብሩ ምሳሌ ነው፡፡

ልብሱ እንደ በረዶ ነጻ ( ወአልባሲሁኒ ኮነ ከመ ፀዓዳ)
ጌታችን በደብረ ታቦር ተራራ የብሉይና የሐዲስ ኪዳ ሰዎችን ( ነቢያትና ሐዋርያትን ) አንድ አደረጋቸው፡፡ እሱ አምላካችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ነውና ፡፡ሌላው ምስጢር ሙሴና ኤልያስ የተጠሩበት ሙሴ ነህ ይላሉ ኤልያስ ነህ ይላሉ ሲሉት እርሱ አምላከ ሙሴ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ሊያሳይ ነው፡፡
ከነቢያቱ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ “ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም ( ዘዳ 33÷28) በተባለው መሠረት “እባክህ ክብርህን ( ፊትህን) አሳየኝ ይህ ካልሆነማ ባለሟል መባሌ ምኑ ላይ ነው (ዘጸ33÷18-23) የሚለውን የባለሟልነት ጥያቄውን ሙሴን ከሙታን አስነስቶ ስለክብሩ የቀናውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ ክብሩን አሳይቷቸዋል የሙሴን ጸሎት ሳይረሳ ልመናውን ፈጸመለት፡፡
በጀርባ የተመሰለው ከ5500 በኋላ የተፈጸመው ምስጢረ ሥጋዌ ነው፡፡
ሙሴና ኤልያስ መሆናቸው በምን ይታወቃል?

ሙሴ ብልቱትነቱ ኤልየስም በፀጉርነቱ አንድም በአነጋገራቸው ታውቋል፡፡ ሙሴም የእኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል እግዚአ ሙሴ ይበሉህ እንጂ ኤልየስም የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ይልሃል እግዚአ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ ሲሉ ተሰምተዋል፡፡
አንደድም ምውት ለሕያው ሕያው ለምውት ሲጸልዩ ተስምተዋል፡፡ አንድም ሙሴ እኔ ባሕር ብከፍል ጠላት ብገድል ደመና ብጋርድ መና ባወርድ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና፡፡
ኤልያስም እኔ ሰማይ ብለጉም እሳት ባዘንብ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና ሲሉ ተስምተዋል ( አንድምታ ወንጌል ማቴ ምዕ.፲፯)
ፍጻሜው ግን ደብረታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት፡፡ሕጋውያንም ደናግልም እንዲወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ፡፡
ይህ በዓል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለይም በምእመናን ዘንድ የተለየ ስም አለው( ቡሄ ይባላል)፡፡
ቡሄ ማለት መላጣ ( ገላጣ) ማለት ነው፡፡ በሀገራችን ክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በደብረታቦር በዓል አካባበር ስለሆነ “ቡሄ “ ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ሊቃውንት "ቤሄ ከዋለ የለም ክረምት ደሮ ከጮኸ የለም ሌሊት”እንዲሉ(የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ- 127-128)
- ሕፃናት የሚያጮሁት ጅራፍ ጩኸት ድምፅ የድምፀ መለኮት ጅራፍ ሲጮህ ማስደንገጡን የሦስቱ ሐዋርያት ምሳሌ ሲሆን መደንገጣቸው በድምፀ መለኮቱ መደንገጣቸውን መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
- በአንዳንድ ቦታዎች የቡሄ ዕለት ማታ ችቦ ያበራሉ በደብረታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡
- ምእመናን በድበረታቦር ክብሩን አየን ዛሬም ያ ክበሩ ለገለጥን ያስፈልጋል፡፡ እገዚአብሔር ክብሩን የገለጠበት ያ ተራራ ዛሬ የእኛ አካል ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር ክብሩና ጥበቡ የሚገለጥበት ማዳኑ የሚታይበት የተባረከ ሕይወት ሊኖረን ይገባል

- የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ
እንኳን አደረሰን