Get Mystery Box with random crypto!

JUSTIN APOLOGETICS721]

የቴሌግራም ቻናል አርማ justin_apologetics721 — JUSTIN APOLOGETICS721] J
የቴሌግራም ቻናል አርማ justin_apologetics721 — JUSTIN APOLOGETICS721]
የሰርጥ አድራሻ: @justin_apologetics721
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 996
የሰርጥ መግለጫ

ከእስልምናና ከሌሎች ቤተ እምነቶች ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጫ
“ #አንድ ጌታ #አንድ ሃይማኖት #አንዲት ጥምቀት፤”
— ኤፌሶን 4፥5
አስተያየት ካሎት @Againest_hereticss_bot ላይ ያድርሱን

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 05:05:35 “ስለዚህም አንድ ክርስቶስ አንድ ገዢ እንደሆነ እናምናለን፣ ያለ መቀላቀልም ይህን ተዋሕዶ እናስተምራለን፣ ቅድስት ድንግልም እግዚአብሔርን የወለደች እንደሆነች እናምናለን፤ የእግዚአብሔር ቃል ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ሆኗልና፤ ከእርሷ የነሣውንም ሥጋ ከተፀነሰበት ቀን ጀምሮ ከእርሱ ጋር አንድ ባሕርይ አድርጎታልና።”
ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

@JUSTIN_APOLOGETICS721
108 views02:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:52:48 ከኦሪት ዘፍጥረት 3 ላይ በመነሳት በተለምዶ "የውርስ ኃጢዓት" ስለሚባለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ልናይ የሚገባው ነገር።

የውርስ "ኃጢዓት" አይደለም ማርያም ማንም ሰውም ኖሮበት አያውቅም

አክሊል
122 viewsedited  18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:39:00 የውርስ ኃጢዓት..??

" እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።"
(መዝሙረ ዳዊት 51: 5)

" አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።"
(ሰቆቃው ኤርምያስ 5: 7)፡

" አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤"
(ኦሪት ዘጸአት 20: 5)
122 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 17:37:22
98 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 17:37:10 #በመጀመሪያ_ፍጥረት_እግዚአብሔር_አንዲት_ሴትን_ለአንድ_ወንድ_ሰጥቷልና። ስለዚህ ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ። [መፅሐፈ ዲዲስቅልያ(didaskalia) 13:8-19]
ስለዚህ በክርስትና ከአንድ በላይ ማግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። አንድ ነገር ብየ ልጨርስ። አንድት ቅድስት ሴት ነበረች ሰሟ አፎምያ ይባላል። እናም ከባሏ ጋር እግዚአብሔር በማመሰገን ይኖሩ ነበር። ከዚያም ባሏ አረፈ። እሷም መበለት ሆና መኖረ ጀመረች።ይህን ያየ ሰይጣን ባል እንዲታገባ ይወተውታት ጀመር። እሷም አልስትለት ስትል መልአክ መስሎ አብርሃም ይስሀቅ ዳዊት አግብተዋ ሰለዚህ አንቺም እንደነሱ አግቢ ይላታል። ከዛም "መልአክ ከሆንክ መስቀልህ ወዴት አለ? የንጉስ ጭፍራ ሁሉ የንጉሱን ማሕተም ሳይዝ አይሔድምና አለችው"... ከዛም ሰይጣን መሆኑ ታወቀበት.....ሚካኤል ታደጋት።[ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ:12]
ይህ ታሪክ እኛ የሚወክል ነው። ከዚህ የምንረዳው ዳዊት አብርሀም ....ብዙ ሚስት አግብተዋልና እናንተ አግቡ የሚለን ከሰይጣን እንደሆነ ግልፅ ነው።

"ከአንድ በላይ ጋብቻ ከተፈጥሮ ህግ ውጭ ነው"
ስብሐት ለእግዚአ ኩሉ አሜን
@JUSTIN_APOLOGETICS721
99 viewsedited  14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 17:37:10 #መድብለ_ጋብቻ

በስመ አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ወአውሥአ ወይቤሎሙ ። ኢያንበብክሙኑ #ከመ #ዘፈጠሮሙ #እምትካት #ብእሴ #ወብእሲተ #ገብሮሙ ። ማቴ19:4
በእስልምና ከአንድ በላይ ማግባት የተፈቀደ ነው። ይህንን ከአንድ በላይ ማግባት ክርስቲያኖች አጥብቀው ይቃወማሉ። ይህንን ተቃውሞ መልስ መስጠት ሲሞክሩ ልክ መሆናቸውን ወይም መሳሳታቸውን ማሳየት ሳይሆን እናንተጋም እንዲህ አይነት ነገር አለበማለት ነው። "ስለዚህ ሁለታችንም ስህተት ነን" አይነት አንድምታ ያለው ነገር ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው። "እየቆሉ ጥሬ" ማለት ይሄኔ ነው።
በክርስትና ከአንድ በላይ ማግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። በእስልምና" ነብያቸው መሐመድ እስከ አስራ አንድ ወይም ዘጠኝየሚሉም አሉ" ሚስቶች ነበሩት።[ Sahih al-Bukhari, 268
In-Book Reference: Book 5, Hadith 21] ሙስሊሞች እስከ አራት ሚስት ድረስ ማግባት እንደሚችሉ በቁርአኑ ተቀምጧል። ይሄ ማለት ግን "አራት ብቻ" ማግባት አለባችሁ አይልም። ምክንያቱም "እስከ አራት" የተባለው አንድ ጊዜ ነው። ከዚያም ከእነዚህ አራት ሚስቶች ሁለቱ ጋር ቢለያይ ወይም አራቱ ጋር ቢለያይ ሌላ አራት ማግባት ይችላልና። "እየፈቱ ማግባት"
ይሄ ብቻ አይደለም ማንኛውም ወንድ ሙስሊም በገንዘቡ እየገዛ ዝሙት መፈፀም ይችላል[ሱራ 4:24] በምድር አራት የነበረው በገነት ወደ ሰባ ሁለት ሚስቶች ከፍ ይላል። ይሄም የሚያሳየው #ጋብቻ በእስልምና ምንም እንደሆነ ነው።
ወደ ክርስትና ስንመጣ ጋብቻ ቅዱስና የተከበረ ነው። ለዚህም ነው እግዚአብሔር በእሱና በእስራኤላውያን መካከል የነበረውን ትስስር በጋብቻ(በባልና ሚስት) እየመሰለ የሚናገረው። በሀዲስ ኪዳንም ክርስቶስ እና ቤተ ክርስቲያንን በሙሽራና በሙሽራይቱ እየመሰለ የሚናገረው።

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ከአዳም በላይ ለአዳም የሚያስፈልገውን ያውቃልና ከጉኑ ረዳት ትሆነው ዘንድ ሔዋንን ፈጠራት። ከአዳም ብዙ ሚስት የሚያስፈልገው ቢሆን ብዙ ሚስቶችን በፈጠረለት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ከመጀመርያ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ከአንድ በላይ ማግባት" ከተፈጥሮ ህግ ውጭ ነው። ለዚህም ይመስላል አብዛኛው ሙስሊም የቁርአኑን ህግ ፍቆ መጣል ባይችልም "የልቦና ህግ" አለና ሲተገብሩት አይታይም። ሴቶችም እንዲደበልባቸው አይፈልጉም። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው።
ከአንድ በላይ ጋብቻ ከብሉይ ኪዳንም ሆነ በሀዲስ ኪዳን የተፈቀደበት ቦታ የለም።
#ብሉይ ኪዳን
እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ከአንድ በላይ ማግባትን አልፈቀደም። እግዚአብሔር ባይፈግቅድም ያገቡ ሰዎች ግን ነበሩ። እግዚአብሔር ለሙሴ ሕግን ሲሰጠው ከአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ በስድስተኛው እና በዘጠነኛው ህግ እንዲህ የሚል ቃልን አስቀምጧል።
ዘጸአት 20¹⁴ አታመንዝር።¹⁷ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን #ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።
እዚህ ጋር ሁለት ነገር እንመለከታለን።
፩:እግዚአብሔር ማመንዘር እንደማይገባ ይነግረናል። እግዚአብሔር ይህንን ህግ ለእስራኤላውያን ሲሰጣቸው እነሱ የፈቱበት አፈታት ቢኖርም ጌታችን አታመንዝር የሚለውን ህግ ስሰጣችሁ ማስተላለፍ የፈለግሁት "እኔ ግን እላችኋለሁ" እያለ ተርጉሞልናል። ይህም ከአንድ በላይ ማግባት አይደለም አይቶ ለዝሙት መመኘት ሀጢያት እንደሆነ ነግሮናል። ማቴዎስ 5²⁷ አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል።²⁸ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።
፪የባልንጀራህን ሚስት አለ እንጂ ሚስቶች አላለም። ስለዚህ ከአንድ በላይ አግቡ አላለም። እዚጋ ሙስሊሞ ወገኖች አብርሃም ዳዊት ሰሎሞን... ከአንድ በላይ አግብተዋል ስለዚህ አልተከለከለም የሚል argument ያቀርባሉ። ሰዎቹ ከአንድ በላይ አገቡ ማለት እግዚአብሔር ፈቅዷል ወይም እኛም እነሱን ተከትለን ማግባት አለብን የሚል አንድምታ አያሲዝም።
ለምሳሌ፦1ኛ ነገሥት 11¹ ንጉሡም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፥ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያን በሲዶናውያንና በኬጢያውያን ሴቶች፥ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ።² እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፦ አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ።³ ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም።⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ።

ስለዚህ ሰሎሞን ስለሳተ እኛም መሳት አለብን? ኧረ በፍፁም። ታዲያ ሰሎሞን ብዙ ሚስት ስላገባ እናንተም አግቡ ማለት ምን ይሉታል?? ከአንድ በላይ አግብቶ የተስተካከለ ህይወት የመራ አላየንም። አብርሃም በሚስቱ ግፊት ወደ አጋር ቢገባ በኋላ ሳራ ላደረገችው በባሪያዋ እስከመናቅ ደርሳለች። ዳዊት ልጁ ልጁን ሲደፍር ልጁን ሲገድል ..... በራሱ ላይ ነብይ ተነስቶ እስከ መገሰፅ የደረሰበት ...... ስለሆነ ይሄ ውሀ የሚያነሳ ሙግት አይደለም።
#ሀዲስ #ኪዳን
በሀዲስ ኪዳን ይህ ሲፀና እናገኛዋለን።
ማቴ¹⁹:⁴⁴ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን?
ከመጀመሪያው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጥሯቸዋል። ስለዚህ ከአንድ በላይ ከመጀመሪያው ያልነበረ ነው። ተጓዳኝ ምንባብ፦ሮሜ 7:2-3&1ቆሮ 7:2&ጢሞ 4:11-12&1ጴጥ 5:3&ኤፌ5:31-33
ከባሏ ጋር ጥቂት ጊዜ የቆየች፣ ከእርሱም በሞት የተለየች በእድሜ ያነሰች መበለት ብትኖር ግን ከዚህ በኅላ እንዲህ እያደረገች ብትኖር ብፅዕት ናት። የእግዚአብሔር ነብይ ኤልያስ ወደ እርስዎ እንደመጣና እንደተቀሰቀሰችው እንደ ሲዶና፣ ስራጵታ መበለት......ከአሴር ወገን እንሆነች እንደ ፋኑኤል ልጅ ሐና ለፀሎትና ለምልጃ ዘወትር እንደተዘጋጀች። በድንግልና አስራ አምስት አመት ኖረች። ከባሏም ጋር ሰባት አመት ኖረች። ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ገብታ ሰማንያ አራት አመት መበለት ሆና ኖረች። የክርስቶስን መምጣት ተስፋ ታደርግና እግዚአብሔር ታመሰግን ነበር። እስራኤልንም ለማዳን መምጣቱን ተሰፋ ለሚያደርጉት ስለ እርሱ ትናገር ነበር።

እንደዚህ የምታደርግ ይህቺ ባልቴት በዚህም አለም በወዲያኛውም አለም ክብና ሞገስን ምስጋናንም ከእግዚአብሔር ዘንድ በመንግስተ ሰማያት ታገኛለች።.....የመጀመሪያ ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ ያማረና ንፁህ እንደሆነ ይህን ታስተውሉ ዘንድ ለናንተ አግባብ ነው። #ሁለተኛ የሚያገቡ ግን ከህግ የወጡ ይሆናሉ።በእግዚአብሔር ዘንድ ሀሰትን ተናገሩ እንጂ ስለ ጋብቻ ብቻ አይደለምና። #ሦስተኛ የሚያገቡ ግን #ከእግዚአብሔር_መንጋ_ከምዕመናን_አይቆጠሩ። #አራተኛ የሚያገቡ ግን ፈፅሞ መሰሰናቸው ታወቀ። ኀፍረትንና ወርደትን ያገኛሉ።
85 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:29:06 የእግዚአብሔር ወንጌል የህይወታችን ዓምድ(ምሰሶ) ነው፡፡

..............
የእግዚአብሔር ወንጌል ህይወታችንን  የሚቆጣጠር (Control of Life) ዋነኛ መሣሪያ መሆኑን ማወቅ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
ህይወታችንን በእግዚአብሔር ወንጌል መምራት የምንችለው ግን ከወንጌሉ ጆሮአችንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ዓይናችንን ያለመሰልቸት በማንበብ እና  በመሥማት የሰሙትን ለማስተዋል መንፈስ ቅዱስን በመለመን ያነበቡትን ወደ ህይወት እንዲቀየር ክርስቶስን በመለመን ጊዜያችንን ለእግዚአብሔር በመሥጠት ሕይወታችንን እግዚአብሔርጋ እና የእግዚአብሔር ወንጌልን መሪ አድርገን መኖር እንችላለን፡፡
ወንጌሉን ስናነብ የኛን የውስጥ ስነምግባር ይነግረናል ይመረምረናል እንድናስተካክል ይረዳናል ከዛ የተሰበረውን እንጠግናለን የተበላሸውንም ሕይወት እናድሰዋለን፡፡
ነገር ግን በዙሪያችን ያሉት ሁከት ፈጣሪወች ህይወታችንን አደጋ ላይ የጣሉት ወይ አደጋላይ ሊጥሉ ጫፍ ላይ የደረሱት ይታገሉናል
ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በሆነ አጋጣሚ ቁስል ይቆስላል ቁስሉ ደግሞ መግል ይይዛል ያን መግል ሁል ጊዜ እያፈረጠ ያጥበዋል እናም ከዚህ መግል ተቋዳሽ የነበሩ ዝንቦች ሲታጠብ አይወዱም ነበረ ሲታጠብ ይበሳጩና አያርፉም ቁስሉ ላይ፡፡ እናም አንተን እንደ ዝንቦቹ ያሉ በዙሪያህ ያሉት አንተ እንድትታጠብ ላይፈለጉ ይችላሉ አንተ ንስሃ ገባህ አንተ እራስህን ለካህን አሳየህ ስለዚህ እነሱ ባንተ ላይ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ የማያደርጉት ነገር የለም አንተ ግን ምናልባት መጀመሪያ ላይ ከሆነ ተጠንቀቅ ብትችል ቀስ በቀስ አምጣቸው ወደ እግዚአብሔር፡፡
ግን እነሱን በፍጹም እንዳትመስል፡፡ አመጣቸዋለሁ ብለህ እንዳትቀር ይህንም እንዳትዘነጋ  ጉድጓድ ውስጥ ላለ ሰው ዱላ ስጠው እንጂ እጅህን አትስጠው የሚባለው ለዚህ ነው አንተን ወደጉድጓዱ ለማስገባት ከፈለገ ዱላውን ለቀቅ አድርገህ ትመለሳለህ እጅህን ከሰጠህው ግን እጅህን ስቦ ጉድጓዱጋ ያስገባሃል፡፡ ለዚህም ነው አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜ የነገርከው ካልሰማ ፈቀቅ በለው (ቅዱስ ጳውሎስ)





https://t.me/Tmhrte_Tewahdo
127 views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 22:15:42 the Orthodox faith
138 viewsedited  19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 15:53:21
187 views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 21:50:14 " ክርስቶስ የሚታየውን ወተት ከአንቺ ደረት ተጠግቶ ጠጥቶ ነበር ዮሐንስ ደግሞ የተሰወሩ ምስጢራትን ከእርሱ ደረት ተጠግቶ ጠጥቷል ክርስቶስ ወደ አንቺ እቅፍ በመተማመን እንደ ተጠጋ ዮሐንስም ወደ ክርስቶስ እቅፍ በመተማመን ተጠግቷል ልጅሽ ድምጹን እንደምትናፍቂ ስላወቀ መጽናኛ ይሆንሽ ዘንድ በገናውን ዮሐንስን ሰጠሽ "

[_ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ_]
@JUSTIN_APOLOGETICS721
224 viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ