Get Mystery Box with random crypto!

Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )

የቴሌግራም ቻናል አርማ jossiale2022 — Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center ) I
የቴሌግራም ቻናል አርማ jossiale2022 — Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )
የሰርጥ አድራሻ: @jossiale2022
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.22K
የሰርጥ መግለጫ

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 251921785903 እና 251711114443 ላይ ይደውሉ።
#ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:23:11
ኢትዮ ሜድካል ትሪንግ ፒኤልሲ የሲፒድ ማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቀቀ!!!
485 viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:34:04 #የወንዶች_የሽንት_ቱቦ_ላይ_እጢ_ማደግ (BPH)
==============================
@ይህ ችግር የአባትህ/ሽ፣ የወንድምህ/ሽ፣ የአጎትህ/ሽ ወይም የአያትህ/ሽ የመሆን እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። በቀናነት መረጃውን ሸር ሲያደርጉ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ሰዎችን ከችግር ለመገላገል አንድ እርምጃ ጀመራችሁ ማለት ነው።
============
• ከሽንት ከረጢት ሽንትን ተቀብሎ ወደ ውጭ በሚለቀው ቱቦ ላይ ፕሮስቴት(prostate) የሚባል የተፈጥሮ እጢ በትቦው ቀኝና ግራ ላይ ይገኛል።

• ችግሩ በወንዶች ላይ ብቻ የሚፈጠር ነው። ምክንያቱም እጢው ያለው ወንዶች ላይ ብቻ ስለሆነ ነው።

• እድሜ እየጨመረ ሲሄድ በተለይ ከ45 አመት በኋላ ቢያንስ ከ5 ወንዶች 3ቱ ላይ ይከሰታል። እድሜ ሲገፋ ፀጉር እንደሚሸብት፣ ጥፍር እንደሚያድግ፣ ቆዳ እንደሚያሸበሽብ ሁሉ ይህ እጢም መጠኑ ይጨምርና ያብጣል።
• እብጠቱም ቱቦውን በመጫን ይዘጋዋል። ሽንት ከሽንት ከረጢት እንዳይዎጣ ያደርጋል።ይህ ደግሞ በሽንት ከረጢት ላይ፣ በሽንት ቱቦ እና በኩላሊት ላይ ችግር ይፈጥራል።

#ምልክቶቹ
• ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና መጣደፍ
• የሚሸናው ሽንት አጣዳፊና ትንሽ መሆን
• ሽንቱ እየተጠባጠበ መውጣትና ማስማጥ
• በተለይ የሽንት መምጣት ድግግሞሽ ማታ ማታ መጨመር
• እየቆየ የሽንት ሙሉ በሙሉ መውጣት አለመቻል
• የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን መታየት
• ለመሽናት መቸገር
• የሽንት ጋር ደም መታየት ናቸው።

#የዚህ ችግር ዋና ምክንያት የእድሜ መግፋት ብቻ ነው። ችግሩ እንድጀምርና እንድነሳሳ የሚያደርጉ ነገሮች ግን አሉ።
እነርሱም ፦
• እድሜ
• በቤተሰብ ተደጋጋሚ ተከስቶ ከነበረ
• የስኳር በሽታ
• የልብ ችግር እና
• ውፍረት ናቸው።
#ህክምናው
• በቀላሉ እንደ ደረጃው ይታከማል።
1. በመድሀኒት
2. በባለሙያ በሚሰጡ ምክሮችና
3. በቀዶ ህክምና

#ካልታከመ ሊፈጠር የሚችለው
• ሽንት መሽናት አለመቻል
• የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን
• የሽንት ከረጢት ላይ ጠጠር መፈጠር
• የሽንት ቱቦ መጎዳት እና
• የኩላሊት መጎዳት ናቸው።
#ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች መልዕክቱን ያጋሩልን። ለተጨማሪ መረጃም ያማክሩን። ሁልጊዜ ዝግጅ ነን። በዚህ የቴሌግራም ሊንክ ገብተው የፈለጉትን የጤና መረጃ ያግኙ። ቤተሰብ ይሁኑ።
https://t.me/jossiale202
#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
3.0K viewsYoseph Alebachew, edited  14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:48:01
#የሰው_ልጅ_ጤናማ_ሆኖ_እንድኖሮ_ወሳኝ_የሆኑ_ነገሮች_የሚከተሉት_ናቸው።

ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተስማሚ የመኖሪያና የስራ ቦታ መኖር
ያልቆየ እና ያልተቀነባበረ ምግብ መመገብ

በቂ ውሀ በየቀኑ መጠጣት እና አልኮል እንድሁም ማንኛውንም አነቃቂ መጠጦች መቀነስ
ቋሚ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

በቂ እንቅልፍ መተኛት

ከማህበረሰብ ጋር ጤናማ ግንኙነት ወይም ተግባቦትን መፍጠር እና

እራስን በእውቀት፣ በጥበብ፣ በቀና አስተሳሰብ እና በመግባባት ክህሎት መገንባት ናቸው።

ለበለጠ መረጃ በቀጣዩ ሊንክ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰብ ይሁኑ። ችላ አይበሉ!!! #እኛ_የምንሰጠዎ_ጤናን_ነው።
https://t.me/jossiale2022
https://t.me/InfoHealthCenter

#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
1.9K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), edited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:56:58 #ሰለ_ደም_ማነስና_የደም_ግፊት

የደም ማነስና የግፊት ማነስ ልዩነት አላቸዉ። የደም ማነስ ከቀይ የደም ሴሎች ቁጥር ጋር ወይም የሄሞግሎቢን መጠን ጋር የሚገናኝ ሲሆን የደም ግፊት ማነስ ግን ከደም ቧንቧዎች መጨናነቅና ከደም መጠን( volume) ጋር ይዛመዳል።

የደም ግፊት ማነስ፥- ይህ በሰዉ ክንድ ላይ የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያን በመጠምጠም የሚለካ ሲሆን የአንድ ሰዉ የደም ግፊት የላይኛዉ (ሲስቶሊክ) ልኬት መጠን ከ90 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በታች የሆነ እንደሆነና የታችኛዉ የደም ግፊት ልኬት (ዲያስቶሊክ) መጠን ደግሞ ከ60 ሚሊ ሜትር ሜርኩሪ በታች ከሆነ የደም ግፊት ማነስ አለ ተበሎ ይገለፃል። ዝቅተኛ የደም ግፊት መኖር በሰዎች ላይ ምንም የሚታዩ የህመ ምልክቶችን ላያመታ ይችላል ምልክት ከተከሰት የራስ ማዞርና ራስን መሳት ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ዝቅተኛ የደም ግፊት ( የደም ግፊት ማነስ) ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል.



የደም ማነስ፦ ኦክሲጂንን በበቂ መጠን ወደ ሰዉነታችን የሚያደርሱ በቁጥር በቂና ጤነኛ ቀይ የደም ሴሎች ሳይኖሩ ሲቀር የሚከሰት ችግር ነዉ። ይህም ማለት የደም ማነስ የቀይ የደም ሴሎች ብዛት ወይም በውስጣቸው ያለው የሂሞግሎቢን ክምችት ከመደበኛው ያነሰበት ሁኔታ ሲኖር ነው።

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የደም ማነስ አለ የሚባለዉ የሄሞግሎቢን (Hb) ደረጃ በሴቶች ከ12.0 ግ/ዴሲ ልትርና በወንዶች ላይ 13.0 ግራም/ዴሲሊትር በታች ሲሆን ነዉ።

#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
2.4K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), edited  15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:46:50 #ሶሪያሲስ_psoriasis

ሰላም ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች እንደት ናችሁ? ለዛሬ ሶሪያሲስ ስለሚባለው የጤና ችግር እንሆ ብለናል።

እውቀት ጥሩ ነው። ግንዛቤ እንድሁ። እኛ ደግሞ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ እውቀትን የሚያሰፋ የጤና መረጃ እንሆ ብለናል። ይህን እውቀትና ግንዛቤ ለማግኘት ቀጣዩን ሊንክ ተጭነው ይግቡና እየመረጡ ይኮምኩሙ። እኛ እንሆ ብለናል። መጠቀም አለመጠቀም ግን የርስዎ ምርጫ ነው።
====================================
https://t.me/jossiale2022
=============================

• ይህ በሽታ የራሳችን በሽታ ተከላካይ ህዋሳት (ሴሎች) የራሳችንን የቆዳ ህዋሳት በማጥቃቱ የሚፈጠር የኢንፍላሜሽን ውጤት ነው።
• ሶሪያሲስ ቆዳ ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሲሆን የቆዳችን ሴሎች መራባት ካለባቸው በላይ እስከ አስር (10) እጥፍ በስህተት እንድራቡ የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ ቆዳችን ላይ ቡፍ ያለ ቅይ ሽፍታ ቅርፊት ያለው ነገር እንድፈጠር ያደርጋል።
• ሶሪያሲስ በማንኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊከሰት ይችላል። በተለይ በራስ ቅል ቆዳ ላይ፣ በክንድ ዙሪያ ላይ፣ በጉልበት አካባቢና በታችኛው የጀርባ አካባቢ በይበልጥ የተለመደ ነው።
• ሶሪያሲስ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም። አንዳንድ ጊዜ ግን በአንድ አይነት ቤተሰብ ውስጥ አልፎ አልፎ ሊታይ ይችላል። በዘር የሚተላለፍበት እድል አለ። በቤተሰብ መሀል ሊኖርና ሊያያዝ ይችላል። መሀል ላይ እየዘለለ አያት ላይ ከነበረ የልጅ ልጅ ላይ ሊከሰት ይችላል። ከህፃናትና አዛውንቶች ይልቅ ጎልማሶች በይበልጥ ይጠቃሉ።
• ሶሪያሲስ ትንሽ ቦታ ላይ ጀምሮ እየሰፋና እየዘለለ ወደሌላ የሰውነት ክፍል የሚሰራጭም ነው።
• ሙሉ ለሙሉ ማዳን ባይቻልም ምልክቶቹን ማከምና ተጠቂውን ጤናማ ማድረግ ይቻላል። ይህ ማለት ግን ህክምና ሲያቋርጥ አይመለስበትም ማለት አይደለም። ሽፍታውን፤ ቁስሉንና ቅርፊቱን ማጥፋት ይቻላል።
• የበሽታው ምክናየት ከውስጥ ከነጭ የደም ህዋሳት የሚጀምር ስለሆነ ነው ለማጥፋት አስቸጋሪ የሚሆነው።
#የበሽታው #ዋና #ዋና #መገለጫዎች
• ቅርፊት ያለው ወፈር ወፈር ያለ ቀያይ ሽፍታ
• ቅርፊቱ ሲሊቨር ከለር ሊኖረው ይችላል
• የመሰነጣጠቅና የመድማት ባህሪ ይኖረዋል
• እየባሰ ሲሄድ የማደግ፣ በአንድ ላይ የመሰብሰብና ብዙ ቦታ የመሸፈን ባህሪ ይኖረዋል
• በእጅና በእግር ጥፍር ላይ የነጠብጣብ አይነትና ቀለም የመቀየር ነገር ይታያል
• ጥፍር ከተጣበቀበት ቆዳ የመሸሽና ቅርፁን የማጣት ሁኔታ እናያለን
• የራስ ቅል ቆዳ የመፈርፈር ሁኔታ ይኖራል
• የተለያዩ የመገጣጠሚያ ኢንፊክሽን ሊኖር ይችላል
• የመገጣጠሚያ ህመምና እብጠት
#ሶሪያሲስ በሚከተሉት አይነቶች ይገለፃል
1. በእጅ መዳፍና በእግር ሶል ላይ የሚከሰት
2. በህፃንነት ወይም በወጣትነት የሚጀምር ሆኖ በቀያይና ትናንሽ ሽፍታ ቆይቶ እየቆየ ሲሄድ ግን በመተፈሻ አካላት ኢንፌክሽን፣ በቶሲል ኢንፌክሽን፣ በጭንቀትና ውጥረት፣ በቆዳ ጉዳት፣ በፀረ ወባ መድሀኒትና በሌሎችም ምክናየት የሚባባስ አይነት አለ።
3. በጣም ደማቅ ቀይና ሻይን የሚያደርግ ሽፍታ ይሆንና የቆዳ መታጠፍ በብብት ውስጥ፣ በብሽሽት ላይና በጡት ስር ላይ እንድፈጠር የሚያደርግ አይነት አለ።
4. የተቃጠለ ቀይና ተቃጥሎ የዳነ የሚመስል ቆዳ እንድኖር ሊያደርግ የሚችል ይህም በከባድ የፀሀይ ጨረር፣ በቆዳ ኢንፌክሽን፣ በአንዳንድ መድሀኒቶችና በህክምና መቋረጥ የሚባባስ አይነት አለ።
#የበሽታው #ምክናየት
• በትክክል ምክናየቱ አይታወቅም። ይሁን እንጅ የተለያዩ ነገሮች ጥርቅም ለችግሩ እንደ መነሻ ይቆጠራሉ።
1. ቲ ሴል የሚባል የነጭ የደም ህዋስ ክፍል ለኢንፌክሽንና ለኢንፍላሜሽን የሚሰጠው የተሳሳተ ምላሽ
2. አንዳንድ የቆዳ ህዋሳት በፍጥነት መመረታቸው ወይም መራባታቸው
3. ከ10-30 ቀን ይፈጅ የነበረው የቆዳ ህዋሳትን የመተካት ሄደት በየ 3 እና 4 ቀን መሆኑ
4. ያረጁ የቆዳ ህዋሳት በቆዳ ውስጥ መጠራቀማቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ።

#የሶሪያሲስ #በሽታን #የሚያባብሱ #ነገሮች
• ፀረ ወባ መድሐኒቶች
• ለደም ግፊት የሚታዘዙ መድሐኒቶች
• ጭንቀትና ውጥረት
• አንዳንድ የባክቴሪያ ኢንፊክሽን
• የቆዳ መቆረጥ፣ እከክና የተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች
#ሶሪያሲስ በሽታን መለየትና ማወቅ ቀላል ነው።በተለይ ሽፍታው፣ ቅርፊቱና ቁስለቱ በራስ ቅል ላይ፣ ጆሮ አካባቢ፣ ክንድና ጉልበት አካባቢ ከሆነ ይቀላል። ከቆዳ ቅርፊቱ ላይ ናሙና ወስዶ በላብራቶሪይ በማየትም ይታወቃል።

ህክምናው
======== ብዙ አይነት ህክምና አለው።
1. እድገቱን ለመቀነስ
2. እድገቱን ለመግታት
3. ማሳከኩን ለማስቆም
4. ደርቆ እንዳይሰነጣጠቅ ለማድረግ
5. ህመም እንዳይኖረው ለማድረግ
#ህክምናው በሽፍታው መጠን፣ በእድሜ ደረጃ፣ በሸፈነው የሰውነት ክፍልና በሌሎች መስፈርቶች ይወሰናል።
@ማንኛውም ሶሪያሲስ ያጠቃው ሰው የሚከተሉትን ነገሮች በቻለው መጠን በየቀኑ ቢተገብር ትልቅ ለውጥ ያገኛል።
1. ተጨማሪ የተቀነባበሩ የምግብ ግብአቶችን እንደ አሳ ዘይት፣ ቫይታሚን ዲና የተናጠ የወተት ተዋፅኦን መጠቀም ምልክቶችን ይገታቸዋል።
2. ሁል ጊዜ ቆዳ እንዳይደርቅ ማድረግ። እንደ አጠቃላይ ቢሮም ሆነ ቤተዎ ደረቅ አየር እንዳይኖረው ማድረግ ቢችሉና ቆዳዎትን ለስለስና ረጠብ ማድረግን አይርሱ።
3. የሚያጤሱ ከሆነ ያቁሙ። ማጤስ የበሽታውንየማጥቃት አቅም ይጨምርለታል።
4. አልኮል ተጠቃሚ ባይሆኑ ይመረጣል። አልኮል በሽታውን ያባብሳል።
5. በጤና ባለሙያ ለተመጠነና ለታዘዘ የፀሀይ ጨረር ቁስሉን ማጋለጥ። #አስታውሱ፡ በጤና ባለሙያ ካልታዘዘና እይታ ውስጥ ካልሆኑ አይሞክሩት።
6. ጭንቀትና ውጥረትን ይቀንሱ። ጭንቀት ምልክቱ በህክምና ቢጠፋ እንኳን እንድመለስና በሽታው እንድባባስ ያደርጋል።
7. ለብ ባለ ውሀ ሰውነተዎን ይዘፍዝፉት። ፈፅሞ ለስለስ ከማለት ያለፈ ወይም ሞቃት ውሀን እንዳይጠቀሙ። ለብ ካለው ውሀ ላይ ኢፕሰም ጨው፣ ኦላይቭ ዘይት፣ ሚኒራል ኦይልና ወተት መጨመር ይቻላል። ከነዚህ አንዱን ማለት ነው።
8. ሁል ጊዜ ጤናማ አመጋገብ ከቻሉ ይጠቀሙ። አመጋገብ ወሳኝ ነው። ቀይ ስጋ፣ የሚወጋ ዘይት፣ የተፈበረከ ስኳር፣ ሀይልና ሙቀት ሰጭ ምግብና አልኮልን ባይጠቀሙ ጥሩ ነው። እንዳይባባስና ባለበት እንድገታ ያደርጋል።
9. ማንኛውንም ሳሙና፣ ዶዶራንትና ሽቶ ከመጠቀም ይቆጠቡ። የሚስማማዎትን ሳሙና ይምረጡ። ወይም ሀኪመዎትን ያማክሩ።
#እንደ አጠቃላይ ችግሩ መቸ፣ እንደት፣ በምንና ለምን እንደሚባባስና እንደሚቀንስ ከህይዎት ተሞክሮም ማወቅ ይጠበቅበዎታል። ሀኪመዎትን በየጊዜው ማማከር፣ ጭንቀትንና ስለ በሽታው ማሰላሰልን መቀነስ እንድሁም የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ወሳኝ ነው።
እባከዎትን ሸር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱልን!!!!
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን።
https://t.me/jossiale2022
2.4K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:54:27


የዩቲዩብ ቻናላችንን ያላያችሁት ካላችሁ ግቡና እዩ። ደግሞም ሰብስክራይብ አድርጉ። ብዙ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች ሰብስክራይብ አድርገዋል። #እርስዎስ???
3.6K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), edited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:14:09 https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
1.5K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:39:52 #አቮካዶን_የመመገብ_ጥቅሞች_በጥቂቱ


➮ የኮሌስትሮል መጠን ይቀንሳል

አቮካዶ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር (betasisterol) በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘዉን የኮሌስትሮል መጠን እንደሚቀንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

➮ ለዓይናችን ጤና ጠቃሚ ነው

በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲየን (carotenoid lutien) ዓይናችንን ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚመጡ ሕመሞችን እንድንከላከል ይረዳል፡፡

➮ በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን ይቀንሳል

በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው (folate) ፎሌት በስትሮክ የመጠቃት ዕድልን እንደሚቀንስ የተደረጉ ጥናቶቸድ ያሳያሉ፡፡

➮ከካንሰር ይከላከላል

አቮካዶ የሚመገቡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው እንደሚቀንስና ወንዶችን ደግሞ ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል የመከላከል አቅም እንዳለው የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

➮መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል

አቮካዶ ተፈጥሮአዊ ከሆኑ የመጥፎ አፍ ጠረን መከላከያዎች አንዱ ነው፡፡

➮ለቆዳችን ጥቅም

የኦቮካዶ ቅባት በብዙ የውበት መጠበቂያዎች ውስጥ የሚገባና ለቆዳ ተስማሚ እና ጤናማነት ጠቃሚነት ያለው የፍራፍሬ ዓይነት ነው፡፡

ጤና ይስጥልኝ!
https://t.me/jossiale2022
#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
4.6K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), edited  06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:05:58
የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ 7 ምግቦች

እርጎ

አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክ እና እንዲቀበል ይረዳል፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ ይይዛል፤ ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶች እና መልእክት አስተላላፌዎች በተገቢው እንዲያድጉ ይጠቅማል።

አትክልቶች

አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት፣ እንደባሮ ሽንኩርት፣ እስፒናች፣ ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ።

ብሮኮሊን

ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል።

አቮካዶ

አስፈላጊ ቅባት ይይዛል ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል። ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል (ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል)። በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፌት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል።

አሳ

አሳዎች ኦሜጋ 3 የበለፀጉ በመሆናቸው የልጆች አእምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው ይረዳሉ።

እንቁላል

የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን (አሴታይል ኮሊን) እንዲመረት የሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል።

የተፈጨ አጃ

በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል፤ በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ሀይልን እንዲያገኙም ያደርጋል።

መልካም ጤንነት!!
https://t.me/jossiale2022
5.5K viewsYoseph Alebachew, edited  17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 23:48:12 #በቂ_ፋት_እያገኙ_እንዳልሆነ_የሚያሳዩ_ምልክቶች

ፋት ያለባቸው ምግቦች ብዙውን ግዜ በመልካም ጎኑ ስማቸው ሲነሳ አይሰማም። ነገሩ እንዳለ ሆኖ ግን ፋት ያለበት ምግብ መመገብ ብቻውን የሰውነት ክብደታችን ያለመጠን እንዲጨምር አያደርግም። በአግባቡ እስከተመገብን ድረስ።

ሰውነታችን በተፈጥሮው ፋት ይፈልጋል። ሰውነታችን የሚፈልገውን የፋት መጠን በአግባቡ ካልሰጠነው በጤናችን ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላል። ሰውነታችን በቂ መጠን ያለው ፋት ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት አምስቶቹ ዋነኞቹ ናቸው።

1. የቫይታሚን እጥረት (Vitamin deficiencies)

እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ዲ፣ ኢ እና ኬ (A, D, E & K)የመሳሰሉ የቫይታሚን አይነቶች በፋት የሚሟሙ (fat soluble vitamins) ይባላሉ። ሰውነታችን እነኚህን ቫይታሚኖች መጦ ለመጠቀም የፋት ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማግኘት ይፈልጋል። ይህ በማይሆንበት ግዜ የእነዚህ ቫይታሚኖች እጥረት ሰውነታችን ይገጥመውና ለሚከተሉት የጤና እክሎች ልንጋለጥ እንችላለን:-

በምሽት ለማየት መቸገር (night blindness)
የጸጉር ድርቀት (dry hair)
መሃንነት (infertility)
የጡንቻ ህመም (muscle pain)
ድብርት (depression)

2. የቆዳ መቆጣት (Dermatitis)

የኤን ሲ ቢ አይ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ፋት የቆዳ ጤንማነት ላይ ትልቅ ድርሻ አለው። በቂ የሆነ ፋት ካላገኘን ሰውነታችን ዴርማቲቲስ ለተባለው ለቆዳ መቆጣት በሽታ የመጋለጥ እድላችን ሰፊ ነው።

3. የቁስል በቶሎ ያለመዳን

በፋት እጥረት ምክንያት እንደ ቫይታሚን ኤ እና ዲ የመሳሰሉ ቫይታሚኖች እጥረት ሊከሰት ይችላል። ይህም እነኚህ ቫይታሚኖች በቁስል በቶሎ መዳን ላይ ያላቸውን ሚና ስለሚያሳጣን የቁስል በቶሎ ያለመዳን ችግር ሊከሰት ይችላል።

4. የጸጉር መነቃቀል

ፕሮስታግላንዲንስ (Prostaglandins) የተባሉ የፋት ሞለኪውሎች በጸጉር እድገት እና ጤናማነት ላይ ትልቅ ድርሻን ይጫወታሉ። በቂ ፋት ያለመመገብ ይህን ፋቲ ሞሎኪውል በበቂ መጠን እንዳናገኝ ስለሚያደርግ ለጸጉር ወዝ ማጣት እና የመነቃቀል ችግር ሊያጋልጠን ይችላል።

5. ተደጋጋሚ ህመም

በበቂ መጠን ፋት ያለማግኘት ሰውነታችን ሊኖረው የሚገባውን የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) ይጎዳል። ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅሙን ለማደበር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ፋት ነው። ይህም በመሆኑ በቂ ፋት አለመመገብ ደካማ የበሽታ መከላከል ስረዓትን በማዳከም በቀላሉ ለበሽታዎች የምንጋለጥበትን እድል ይፈጥራል።

ጤናማ ፋት ያላቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸው?

ፋት መመገብ ሲባል የግድ ጮማ ስጋ መቁረጥ ማለት አይደለም። በቀላሉ የፋት ይዘት ልናገኝባቸው ከምንችልባቸው ምግቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:-

አቮካዶ
እንቁላል
አሳ
ለውዝ
እርጎ
ኦሊቭ ኦይል

መልካም ጤንነት!!
#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

#ጎተራ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ቢሮ_ቁጥር_402

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093
5.5K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), edited  20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ