Get Mystery Box with random crypto!

#የወንዶች_የሽንት_ቱቦ_ላይ_እጢ_ማደግ (BPH) ============================== | Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )

#የወንዶች_የሽንት_ቱቦ_ላይ_እጢ_ማደግ (BPH)
==============================
@ይህ ችግር የአባትህ/ሽ፣ የወንድምህ/ሽ፣ የአጎትህ/ሽ ወይም የአያትህ/ሽ የመሆን እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። በቀናነት መረጃውን ሸር ሲያደርጉ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ሰዎችን ከችግር ለመገላገል አንድ እርምጃ ጀመራችሁ ማለት ነው።
============
• ከሽንት ከረጢት ሽንትን ተቀብሎ ወደ ውጭ በሚለቀው ቱቦ ላይ ፕሮስቴት(prostate) የሚባል የተፈጥሮ እጢ በትቦው ቀኝና ግራ ላይ ይገኛል።

• ችግሩ በወንዶች ላይ ብቻ የሚፈጠር ነው። ምክንያቱም እጢው ያለው ወንዶች ላይ ብቻ ስለሆነ ነው።

• እድሜ እየጨመረ ሲሄድ በተለይ ከ45 አመት በኋላ ቢያንስ ከ5 ወንዶች 3ቱ ላይ ይከሰታል። እድሜ ሲገፋ ፀጉር እንደሚሸብት፣ ጥፍር እንደሚያድግ፣ ቆዳ እንደሚያሸበሽብ ሁሉ ይህ እጢም መጠኑ ይጨምርና ያብጣል።
• እብጠቱም ቱቦውን በመጫን ይዘጋዋል። ሽንት ከሽንት ከረጢት እንዳይዎጣ ያደርጋል።ይህ ደግሞ በሽንት ከረጢት ላይ፣ በሽንት ቱቦ እና በኩላሊት ላይ ችግር ይፈጥራል።

#ምልክቶቹ
• ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትና መጣደፍ
• የሚሸናው ሽንት አጣዳፊና ትንሽ መሆን
• ሽንቱ እየተጠባጠበ መውጣትና ማስማጥ
• በተለይ የሽንት መምጣት ድግግሞሽ ማታ ማታ መጨመር
• እየቆየ የሽንት ሙሉ በሙሉ መውጣት አለመቻል
• የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን መታየት
• ለመሽናት መቸገር
• የሽንት ጋር ደም መታየት ናቸው።

#የዚህ ችግር ዋና ምክንያት የእድሜ መግፋት ብቻ ነው። ችግሩ እንድጀምርና እንድነሳሳ የሚያደርጉ ነገሮች ግን አሉ።
እነርሱም ፦
• እድሜ
• በቤተሰብ ተደጋጋሚ ተከስቶ ከነበረ
• የስኳር በሽታ
• የልብ ችግር እና
• ውፍረት ናቸው።
#ህክምናው
• በቀላሉ እንደ ደረጃው ይታከማል።
1. በመድሀኒት
2. በባለሙያ በሚሰጡ ምክሮችና
3. በቀዶ ህክምና

#ካልታከመ ሊፈጠር የሚችለው
• ሽንት መሽናት አለመቻል
• የሽንት ትቦ ኢንፌክሽን
• የሽንት ከረጢት ላይ ጠጠር መፈጠር
• የሽንት ቱቦ መጎዳት እና
• የኩላሊት መጎዳት ናቸው።
#ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች መልዕክቱን ያጋሩልን። ለተጨማሪ መረጃም ያማክሩን። ሁልጊዜ ዝግጅ ነን። በዚህ የቴሌግራም ሊንክ ገብተው የፈለጉትን የጤና መረጃ ያግኙ። ቤተሰብ ይሁኑ።
https://t.me/jossiale202
#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093