Get Mystery Box with random crypto!

የእንስሳትን ቋንቋ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ለመረዳት ምርምሮች እየተካሄዱ ነው፡፡ እ | JOSIE TECH™💡

የእንስሳትን ቋንቋ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ለመረዳት ምርምሮች እየተካሄዱ ነው፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2017 ምስረታውን ያደረገው Earth Species Project የተባለ ተቋም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የእንስሳትን ዓለም የተግባቦት ምስጢር ለመፍታት ጥረት ላይ ነው፡፡

የተቋሙ ፕሬዚዳንት አዛ ራስኪን ከዘጋርዲያን ጋር በነበራቸው ቆይታ ማሽን ለርንኒግን በመጠቀም የእንስሳትን የመግባቢያ ሥርዓቶች በመፍታት ውጤቱን ማንኛውም ሰው እንዲጠቀምበት ተደራሽ የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መሰል ጥረቶች ጥንቃቄን በሚሻው እንስሶቹን በመከታተል እና በመመልከት ላይ የተመሠረቱ ነበሩ፡፡

ሆኖም እንስሳቱን በቅርብ መከታተል በሚችሉ አነፍናፊዎች (ሴንሰር) አማካኝነት የሚሰበሰበውን ግዙፍ ዳታ ለመተንተን ማሽን ለርኒንግን የመጠቀም ዝንባሌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም ምክንያቱ በቅርቡ በማሽን ለርኒንግ ዘርፍ የታዩ እጅግ አመርቂ ለውጦች መኖራቸው መሆኑን ተቋሙ ይገልጻል፡፡

መቀመጫውን በካሊፎርኒያ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ይህ ተቋም የሰው ያልሆኑ ቋንቋዎችን መረዳት የሰው ልጅ በምድር ሥነ-ምህዳር ላይ የሚያሳርፈውን ተፅእኖ ለመቀየር ያግዛል ብሎ ያምናል፡፡


   |||  - @josie_Tech - |||