Get Mystery Box with random crypto!

በስህተት የጣለውን ቢትኮይን በ13 ሚሊዮን ዶላር እያፈላለገ ያለው ግለሰብ ከ10 ዓመታት በፊት | JOSIE TECH™💡

በስህተት የጣለውን ቢትኮይን በ13 ሚሊዮን ዶላር እያፈላለገ ያለው ግለሰብ

ከ10 ዓመታት በፊት ነው። ጄምስ ሃዌልስ ያስቀመጠውን ቢትኮይን ረስቶ የኮምፒውተሩን የመረጃ ቋት (ሃርድ ድራይቭ) አውጥቶ ጣለው።

ጄምስ ተዝናግቶ የወረወረው ቢትኮይን ዘንድሮ ባለው ገበያ 184 ሚሊዮን ዶላር ሊያወጣ ይችላል።

ይህ የከነከነው ጄምስ ከዓመታት በፊት የጣለውን ቢትኮይን ሚሊዮን ዶላር ከፍሎ ሊያስቆፍረው አስቧል።

የሰውዬው ‘ሃርድ ድራይቭ’ ኒውፖርት በተሰኘችው የዩናይትድ ኪንግደም ከተማ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል።

ጄምስ ይህ ውድ ቁስ ከተገኘለት ከቢትኮይኑ 10 በመቶውን ቆንጥሮ ከተማዋን የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል ለማድረግ ቃል ገብቷል።

ነገር ግን የከተማዋ ምክር ቤት የቆሻሻ መጣያውን መቆፈር ሥነ-ምኅዳራዊ (ኢኮሎጂካል) ቀውስ ያስከትላል እያለ ነው።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (አይቲ) ባለሙያው ጄምስ ከዘጠኝ ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፤ 8 ሺህ ቢትኮይን ያቀፈውን ሃርድ ድራይቭ ጠርጎ የጣለው


Arada tech

   |||  -
@josie_Tech - |||