Get Mystery Box with random crypto!

ሀሰተኛ ዜና ምንድነው? ሀሰተኛ ዜናዎችን እንዴት መለየት ይቻላል? በበይነ-መረብ ላይ የምናገኛቸ | JOSIE TECH™💡

ሀሰተኛ ዜና ምንድነው? ሀሰተኛ ዜናዎችን እንዴት መለየት ይቻላል?

በበይነ-መረብ ላይ የምናገኛቸው ዜናዎች ወይም መረጃዎች ሁሉ እውነት አይደሉም፡፡ ታዲያ በበይነ-መረብ ያገኘናቸዉን መረጃዎች ተገቢውን ማጣራት ሳናደረግ እኛም መልሰን ለሌሎች የምናጋራ ከሆነ የበለጠ በርካታ ሰዎች መረጃውን እንዲያምኑ እድል እንፈጥራለን፡፡

ሃሰተኛ መረጃዎች ሰው ጆሮ ሲደርሱ እውነትን የያዙ መረጃ እና ዜናዎች መስለው አንዲደርሱ መጀመሪያ የተፈጠረ ነገር ይኖራል፡፡ በመሆኑም በበይነ-መረብ ላይ የምናገኛቸውን መረጃዎች ከማጋራታችን በፊት ትክክለኝነታቸውን እናረጋግጣለን? የሚለዉ ጥያቄ ወሳኝ ነዉ፡፡

የሃሰተኛ ዜናን ለመስራት ደግሞ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ይደረጋል፡፡ በዚህ ዉስጥ ሁለት ዓይነት የሀሰት ዜናዎች መጥቀስ ይቻላል፡-

1. ሰዎችን ትክክለኛ ያልሆኑ ነገሮችን እንዲያምኑ ወይም ድረ-ገጾቻቸውን እንዲጎበኙ ሆን ተብሎ እና ታቅደው የሚሠራጩ እና

2. ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ያልሆኑ ነገር ግን በተወሰነ ደረጃ እውነታን በመያዝ ለህብረተሰቡ የሚሠራጩ የሀሰት ዜናዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ለፕሮፓጋንዳ ዓላማ፣ ለውግንና ወይም ስለእውነታው ሰዎች የተሳሳተ ምስል እንዲኖራቸው የሚፈጠሩ የሀሰት ዜናዎችን አሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በርካቶች ብዙ ማጋራቶችን(share) ለማግኘት እነዚህን ትክክለኛነታቸው በአግባቡ ያልተረጋገጡ ታሪኮችን በየዕለቱ ይፋ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

መረጃዎቻቸውም ተቀባይነት እንዲያገኙ የተለያዩ ፎቶግራፎችንና ፊልሞችን በረቀቀ መንገድ ኤዲት በማድረግ፣ ሀሰተኛ ድረ-ገጾችን በመክፈት እና እውነተኛ የሚመስሉ ታሪኮችን በመፍጠር ያሰራጫሉ፡፡

በተለይም ማህበራዊ ሚዲያዎች እነዚህን የሀሰት ዜናዎች በቀላሉና በፍጥነት ለማሰራጨት እየዋሉ ሲሆን በውጤቱም የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተሉ ይገኛል፡፡

ለሀሰት ዜናዎች ተጋላጭ ላለመሆን ለሚከተሉት ጉዳዮች ትኩረት ልንሰጥ ይገባል፡-

- ታሪኩ በሌላ ታማኝ ምንጭ ተዘግቧል?
- በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን ወይም በጋዜጦች ላይ ወጥቷል?
- ስለ ጉዳዩ የዘገበ ተአማኒነት ያለዉ ተቋም አለ?
- መረጃው የተገኘበት ድረ-ገጽ ተአማኒ ምንጭ ነው? /ይህ ማለት በእውነተኛ አካውንት ወይም ስያሜ ጋር ተመሳስሎ የተፈጠረ ገጽ አለመሆኑን ማረጋገጥ)፤
- የድረ-ገፁን አድራሻ በመረጃ ማፈላጊያው ላይ ስንመለከተው እውነተኛ ይመስላል? /ለምሣሌ
gov.et, /
- በታሪኮቹ ውስጥ የቀረቡት ፎቶግራፎች ወይም ቪዲዮች ሲታዩ ምን ያህል ተዓማኒነት ያላቸው ናቸው?
- ታሪኩ ምን ያህል ለእውነታው የቀረበ ነው?
ከላይ ለጠየቅናቸዉ ጥያቄዎች በአንዱ እንኳ ምላሻችን "በፍጽም" የሚል ከሆነ ዜናውን ከማጋራታችን በፊት ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡


   |||  - @josie_Tech - |||