Get Mystery Box with random crypto!

የአልትራሳውንድ መሣሪያን ለመተካት ያለመው ፈጠራ የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች | JOSIE TECH™💡

የአልትራሳውንድ መሣሪያን ለመተካት ያለመው ፈጠራ

የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች በታማሚዎች ሰውነት ላይ በቀላሉ የሚለጠፍ እና የሰውነትን የውስጥ አካላት ምስል በጥራት ማሳየት የሚችል መሣሪያ ማበልፀጋቸው ተነገረ፡፡

ፈጠራው በጤና ተቋማት የሚገኘውን የአልትራሳውንድ መመርመሪያ መሣሪያ የፖስታ ቴምብር በሚያክል ተለጣፊ ቁስ በመተካት የታማሚዎችን ልብ፣ ሳምባ እና ሌሎች ውስጣዊ አካላትን አሁናዊ ምስል በተሻለ ጥራት ለመመልከት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በኢንስቲትዩቱ ድረ-ገጽ በወጣው መረጃ መሠረት ይህ ቆዳ ላይ የሚለጠፍ ቁስ የአልትራሳውንድ መሣሪያዎች ስራቸውን በሚከውኑበት መንገድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለአርባ ስምንት ሰዓት ያለማቋረጥ ምስሎችን ማቅረብ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

መሣሪያው በበጎ ፈቃደኞች ላይ በተደረገ ሙከራ የግለሰቦቹን ዋና ዋና የደም ቧንቧዎች፣ ልብ፣ ሳንባ እና ሌሎች ውስጣዊ የሰውነት አካላትን አሁናዊ ምስል ጥራት ባለው መልኩ ማቅረብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ ባለው የተመራማሪዎቹ ንድፍ ከመሣሪያው የተንፀባረቁ የድምፅ ሞገዶችን ለመተርጎም ከሌላ መሣሪያ ጋር ማገናኘት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ፈጠራውን ገመድ አልባ በማድረግ ለማንኛውም ሰው ተደራሽ ይደረጋል ተብሏል፡፡