Get Mystery Box with random crypto!

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሁዌዦንግ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለው | JOSIE TECH™💡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሁዌዦንግ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ በቴክስት ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ዙሪያ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ትብብር እንዲኖር ያለመ ነዉ፡፡

በስምምነቱ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት የተሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚህም በትምህርት እና ቴክኖሎጂ ትብብር አብሮ ለመስራት እንደሚያስችል በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

የትብብር ሥራው በአፍሪካ የጽህፈት ሥርዓቶች ላይ ጥናት እና ምርምር ለማድረግ የሚያስችል የጋራ የምርምር ቤተ ሙከራ በማቋቋም ኢትዮጵያን የዘርፉ ማዕከል የማድረግ ዓላማ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሁዌዦንግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አፍሪካዊ ጽሁፎችን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማግባባት የሚያስችለውን ዳታ የማልማት ተግባር ያከናውናል፡፡