Get Mystery Box with random crypto!

Firewall ምንድን ነው? ጥቅሙስ? ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ ባጭሩ የኮ | JOSIE TECH™💡

Firewall ምንድን ነው? ጥቅሙስ?

ኮምፒውተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ
ባጭሩ የኮምፕዩተር ቫይረስ ማለት ልክ እንደ ማንኛውም ፕሮግራም ሆኖ ግን አላማውና አሰራሩ ሌላ ኮምፕዩተር ለመበከል ነው።

ማንኛውም የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለቫይረስ ኢላማ ነው። የኮምፕዩተር ቫይረስ በግለሰብ፣ በድርጂቶች፣ በመንግስቶች፣ በነጋዴወች ወዘተ ይሰራል።

የሌላውን አበላሽተው ለመደሰትም ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች አሉ። የዚህንም ያህል የታመሙ ሰወች አሉ። ሁሉም የየራሱ አላማ አለው። የኮምፕዩተር ቫይረስ ውስብስብ ግን መጠኑ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጻር በጣም ትንሽ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ክብደቱና ይዘቱ ትንሽ ሆኖ ግን አደገኛ ነው።

አንቲ ቫይረስ፤ አንቲ ቫይረስ የተሰራው የኮምፕዩተር ቫይረስን ለመከላከል ነው። አሁን ከቅርብ አመታት ወዲህ እራሱ ዊንዶውስ አንቲ ቫይረስ(Windows Defender) በነጻ ለተጠቃሚው ይሰጣል። ሆኖም ግን ሌሎችም የሚሸጡ ነጋዴወች አሉ። ተጠቃሚው እራሱ የትኛውን አንቲ ቫይረስ መግዛት እንደሚፈልግ ይወስናል ማለት ነው። እንደጥራቱ ይለያያል።

የነጻ አንቲ ቫይረሶችም አሉ። በሰፊውና ባይነቱ ለመከላከል ግን የሚገዛው ይሻላል። ለማንኛውም ዊንዶውስ በየጊዜው ስለሚጠቃ አንቲ ቫይረስም ቢሆን ሁሉንም ጥቃት አይከላከልም። አንቲቫይረስ እየሰሩ የሚሸጡ ነጋዴወችም እራሳቸው ቫይረስ ይሰራሉ እየተባለ ይታማሉ።

ፋየርዎል ያልተፈቀደ የኮምፒዩተር ኔትወርክን በመጠቀም ከኮምፒውተር የሚገባንና የሚወጣን ያልተፈቀደ ግንኙነትን ለመከላከል የተነደፈ የደህንነት ስርዓት ነው።
 
ፋየርዎል ከኮምፒዩተር በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባውን እና የሚወጣውን የኔትወርክ ትራፊክ ይቆጣጠራል። 

ፋየርወል በእንግሊዘኛው እሳት የሚከላከል ግድግዳ እንደማለት ነው። ፋየርወል ከውጭ ወደ ኮምፒውተራችን በኔትወርክ አማካኝነት የሚገባን ቫይረስ መሰል የመረጃ በካይ፣ አጥፊ፣ ሰራቂ፣ ሰላይ ፕሮግራሞች እንዳይገቡ በመጠኑም ቢሆን የሚከላከል ሲሆን በጣም ጠቃሚና ለመረጃ ደህንነት አስፈላጊ የኮምፒውተር ማስተካከያ ነው።

ስለዚህ ኮምፒውተታችንን ከኢንተርኔት ጋር የምናገናኝ ከሆነ የኮምፒውተራችንን Firewall on ማድረግ ይጠበቅብናል ማለት ነው። ስለዚህ ለኮምፕዩተርም መከላከያ የሚሆን ፋየርወል አለ።

ለምሳሌ፣ የእርስዎ የግል ኮምፒውተር ፋየርዎል ከሌለው ወይም ፋየርውሉ ዝግ(Off) ከሆነ ቫይረሶች፣ ማልዌር እና ሰርጎ ገቦች(ሀከር) ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ።

ሁለት አይነት ፋየርወሎች አሉ። አንደኛው ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ጋር አብሮ እዛው ተጠቃሚው ያገኘዋል። (መጨረሻ ላይ ያለውን Step ይከተሉ) ለምሳሌ የዊንዶውስ ኮንትሮል ፓነል ላይ ሄዶ ፋየርወሉን እንደ አስፈላጊነቱ (ከፍተኛ ወይም መካከለኛ) መጠን ላይ መርጦ መቀስቀስ ይቻላል። የሚገዙ አንቲቫይረስ ፕሮግራሞችም የራሳቸው ፋየርወል አላቸው። ሌሎችም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ፋየርወል አላቸው።

የኮምፒውተታችንን ፈየርወል ለማስተካከል ቅደም ተከተል Windows 10, 8, 7: ላይ Control Panel > System and Security > Windows Firewall > Turn Windows Firewall on or off
1 the bubble next to Turn off Windows Firewall (not recommended) and then select OK.
2 To disable the firewall for private and public networks, select Turn off Windows Firewall (not recommended) in both sections.


Muhammad computer technology

   |||  -
@josie_Tech - |||