Get Mystery Box with random crypto!

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌሮች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁለገብነትን ተከትሎ ዘርፉን ለማ | JOSIE TECH™💡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌሮች

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሁለገብነትን ተከትሎ ዘርፉን ለማበልፀግና ብዙኃንን ተሳታፊ ለማድረግ ተቋማት እና ግለሰቦች የቴክኖሎጂውን ሶፍትዌሮችን በነጻ ያቀርባሉ፡፡ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ከሚገኙት መካከል ሁለቱን ለዛሬ እናስተዋውቃችሁ፡፡

1.ቴንሰርፍሎው/ TensorFlow
ይህ ሶፍትዌር የማሽን ለርኒንግ ሞዴሎችን ለማሰልጠን እና ለማበልፀግ በስፋት ግልጋሎት ላይ ይውላል፡፡ በተጨማሪም ዳታዎችን በማጠናቀር የትንበያ መላምቶችን ለማዘጋጀት የላቀ አቅም ያላቸው ቁጥርን ማስላት የሚያስችሉ ክምችቶችን ይዟል፡፡

ቴንሰርፍሎው ድምፅን እና ምስሎችን ለሚለዩ የተለያዩ መተግበሪያዎች የጀርባ አጥንት መሆኑ ይነገራል፡፡
ድሮፕቦክስ፣ ኢቤይ፣ ትዊተር፣ ኡበር እና ኢንቴልን የመሳሰሉ ትላልቅ ተቋማት ሳይቀሩ ይህንን ሶፍትዌር ጥቅም ላይ በማዋል ይታወቃሉ፡፡

2. አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን / IBM Watson
አይ.ቢ.ኤም ዋትሰን በተቋማት የሚደረጉ ጥናት እና ምርምሮችን እንዲሁም ግኝቶችን ለማፋጠን የተሻለ አቅምን መፍጠር እንደሚችል ይነገርለታል፡፡ ብዙ ተቋማት ሶፍትዌሩ የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ዳታቸውን ለማጥናት፣ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለማሰባሰብ፣ ስለ ስራቸው ጥልቅ እይታን ለማግኘት እና ቀጣይ የስራ አፈጻጸማቸውን በቀላሉ ለመተንበይ አገልግሎት ላይ ያውሉታል፡፡

በትምህርት፣ በጤና ጥበቃ፣ በፋይናንስ፣ በትራንስፖርት እንዲሁም በኃይል ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት ሶፍትዌሩን አገልግሎት ላይ በማዋል ውጤት አግኝተውበታል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ሶፍትዌር በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን ይጠቁማሉ፡፡


   |||  - @josie_Tech - |||