Get Mystery Box with random crypto!

በሕዋ ቀዶ ጥገና ለመከወን በዝግጅት ላይ ያለው ሮቦት ሚራ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሮቦት በአውሮፓ | JOSIE TECH™💡

በሕዋ ቀዶ ጥገና ለመከወን በዝግጅት ላይ ያለው ሮቦት

ሚራ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሮቦት በአውሮፓውያኑ 2024 በዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣቢያ በመገኘት ከሰው ልጅ አካል ጋር በሚመሳሰል ሕብረ ሕዋስ ላይ የቀዶ ጥገና ሙከራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተነገረ፡፡

በኔብራስካ ዩኒቨርሲቲ እየበለፀገ የሚገኘው የዚህ ሮቦት ዋና ዓላማ ያለማንም እርዳታ ቀላል የሚባሉ ቀዶ ጥገናዎችን መከወን እንደሆነ ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡

በዚህም ወደፊት ወደ ማርስ በሚደረጉ ረዥም ጉዞዎች የጠፈር ባለሞያዎች ቀላል የቀዶ ጥገና ቢያስፈለጋቸው ወይም በአደጋ ጊዜ ወደሰውነታቸው የገቡ ስለቶችን ለማውጣት ሮቦቱ መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎቹ ያስረዳሉ፡፡

ዘንግ መሰሉ MIRA (miniaturized in vivo robotic assistant) ሮቦት አንድ ኪሎግራም የሚጠጋ ክብደት ሲኖረው፤ በዘንጉ መጨረሻ ቁሶችን ለመጨበጥ እና ለመቁረጥ የሚያገለግሉ ሁለት ጫፎች አሉት፡፡

በምርምር ሂደቱ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየው የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ሂደቱን ለማገዝ መቶ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለዩኒቨርሲቲው መለገሱ በዘገባው ተመላክቷል፡፡