Get Mystery Box with random crypto!

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡- ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ፡፡እግዚአብሔር | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡-
ሰላም ጆኒ እንዴት ነህ፡፡እግዚአብሔር ይመስገን መልካሙ ወይም ገብረማሪም እባላለሁ ምስክርነት ለመስጠት ነበር፡፡የአክስቴ ልጅ ፍቅረማሪያም ጥላሁን የተባለ የ12 ዓመት ልጅ በድንገት ሆዴን አመመኝ ብሎ ሶስት የተለያዩ ሆስፒታሎች ምርመራ አድርጎ በመጨረሻ የትርፍ አንጀት ሆኖበት በአፋጣኝ ቀዶ ጥገና ማድረግ አለበት ተብሎ በጣም ደንግጠን ነበር፡፡እናም ወላጅ እናቱ በጣም ተጨንቃ ስለነበር ሆስፒታል ፀበሉንና ስዕል አድኖውን በመውሰድ ከቀዶ ጥገና በፊት ተቀባብቶ ስዕል አድኖውንም ይዞ እንዲገባ አድረገን የነበረ ቢሆንም ነርሷ ማዕተብህንና ስዕል አድኖውን አውልቀህ መግባት አለብህ ሲባል አይቻልም አላወልቅም በማለት ስዕል አድኖውነም ሳልይዝ አልገባም በሚል ሲያለቅስ ቀዶ ጥገና የምትሰራው ዶክተር ችግር የለም በማለት ስዕል አድኖውንም ደረቱ ላይ ለጥፋለት ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተደርጎለት ድኖ ከሆስፒታል ሊወጣ ችሏል፡፡በዕለቱም ለፃድቁ አባታችን እጨጌ ዮሃንስ ህክምናውን በተሳካ ሁኔታ እንዲደረግለት በመለመን ከተሳካለ ምስክርነት እንሰጣለን ብለን ተስለን ስለነበር አባታችን ፃድቁ እጨጌ ዮሃንስ ያደረጉልንን ተዓምርና ምልጃ እንዲታወቅልን ይህንን ምስክርነት ሰጥቻለሁ፡፡የእኛን ልመና ሰምተው ችግራችንን ለፈቱልን አባታችን እጨጌ ዮሃንሰ ምሰጋን ይሁን፤እኛን እንደሰሙ እናንተንም ይስሟችሁ፡፡

፨በስሜ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቤቱ ከንፈሮቼን ክፈት፥አፌም ምስጋናህን ያወራል። መዝ 50:15
መንፈሳዊ ሠላምታዬ ይድረስህ ጆን እንዴት ነህ? አባታችን ሁልጊዜ ጠርቻቸው አሳፍረውኝ አያውቁ፤ ምልጃቸው ከሁላችን ጋር አይለየን።
* ከነበርኩበት ወደ ሌላ ስፍራ ቤት እየቀየርኩ ዕቃ ጫኝና አውራጅ ሠራተኞች ብዙ ገንዘብ ይጠይቃሉ ካልተስማማህ ይጣላሉ ብለውኝ እንግዳም ስለነበርኩ በውስጤ አባቴ እርዱኝ ብዬ ተማጽኛቸው ትንሽ አንገራግረው አንተ ስለሆንክ እንጂ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ አንለቅም ብለውኝ በሠላም ተለይተውኛል።
አባታችንን የሰጠን ቅድስት ሥላሴ ምስጋና ይድረሳቸው ምስጋና ለወላድተ አምላክ ምስጋና ለአባታችን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨ጆኒ እንዴት ነህ? ምስክርነት ለመስጠት ነው የእህቴ ልጅ ወደ ላይ እያለውና ትኩሳት አሞት ነበር እኔም ለአባታችን ማሩልኝ ብዬ ለመንኳቸው አባቴ ክብር ይግባቸው በጣም ደህና ሆኖልኛል። እግዚአብሔር ይመስገን። ወንድሜ መስክርልኝ አደራ አመሰግንሀለሁ።

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን የአቡነ እጨጌ ዬሐንስ ምስክርነት
1. ዛሬ መሬት አስተዳደር ጉዳይ ነበረኝ እናም አባታችን አቡነ እጨጌ ዩሐንስን በሰላም ጉዳዬን እንድፈፅም ከደህና ሰውም ጋር እንዲያገናኙኝ ተማፀንኳቸው ። አባታችን ከመልካም ሰው ጋር አገናኙኝ ።ጉዳዬንም እንደሚጨርሱልኝ እርግጠኛ ነኝ። ሁሌም ስማቸውን ስጠራ ፈጥነው ይደርሱልኛል።
2. አንድ በጣም ያስጨነቀኝ ጉዳይ ነበር አባታችን እኔ በፈለግኩት መንገድ ሁሉን ቦታ አስያዙልኝ።
ቅዱስ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው። አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ፍፁም ፈጣን አባት ናቸው እጅግ አመሰግናለሁ ።

፨፨፨፨ቀጣይ ጉዞ የጻድቁ አባታችን/አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ/ መስከረም ፳፰/፳፱(28/29)
++++ በክረምቱ ምክንያት ጸበሉም ሰለሚሞላ ዝግ ነው እስከ መስከረም 28/1/2015 ድረስ።
ጉዞ

መስከረም፳፰|፳፱ 28~29/2015
ለበለጠ መረጃ የገዳሙ ኮሚቴ፦..
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969
4/0901002929

በጻድቁ አባታችን 500 ዓመት በያዙት መስቀላቸውና መቋሚያቸው እንዳበሳለን፤ ገድላቸው እንዳበሳል ፣ እንባረካል፣እንሳለማል ።የድንግል ማርያም ልጅ ፈቅዶላችሁ ገዳሙ ለመርገጥ ለመባረክ ያብቃችሁ
ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።ቃልኪዳን፤ጣባቂ ያላት ሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም የማትሆነው ቀድሞ የነበራች ከሁሉም የተለየች ሃገራችንን የቃልኪዳኑዋ አስራት ሃገር እምየ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አስታርቃን በሃገራችን ያለውን ርሃብ ታጥፋልን ህዝቦቿን ትጠብቅልን።አሜን!!!

ቦታው፦ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ ባዕለወልድ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም።

የገዳሙ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ!
ለበለጠ መረጃ/# 0911190212/# 0911481388
Fb-(Johnny Aleme)

++ ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ወራዊ በዓል!
++++ ወር በገባ 29
++++ልደታችሁ ህዳር 29
++++እረፍታችሁ ሐምሌ 29
++++ፍልሰት አጽማቸው መጋቢት 18
ሐገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ፍቅር አንድነትን ይሰጡን ።አሜን
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431
+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME
+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5
+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/?utm_medium=copy_