Get Mystery Box with random crypto!

፨ሰላም ወንድም ዮሐንስ! ሰኔ 11 በተደረገው ጉዞ አቡነ ወእጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ሄጄ ባመጣሁ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨ሰላም ወንድም ዮሐንስ! ሰኔ 11 በተደረገው ጉዞ አቡነ ወእጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ሄጄ ባመጣሁት ጸበላቸውና እምነታቸው ; ጆሮው እየመገለ ሲያመው የነበረዉን ህጻን ልጄን ደባብሼው ስለዳነልኝ ምስክርነት ለመስጠት ነው ይህንን መልእክት ያስተላለፍኩት። ጻድቁ ለኔ ያደረጉትን የቸርነት ስራ ለሁሉም ያድርጉላቸው። አሜን። ዮሐንስ ወልዴ እባላለሁ።

፨~በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! ምስክርነት ለመስጠትነው

** አምላከ አቡነ እጨጌ ዬሀንስ ምስጋና ይድረሳቸውና

ቅዳሜ 30/11/14 ነው የወንድሜ ልጅ በጣም አመመው ይንቀጠቀጣል ሙቀቱን ስንለካው 38.5 ሆነ ትኩሳቱ እየጨመረ መጣ በጣም ደከመብን ተደናገጥን መዋጥ አይችልም ቶንሲል አመመው ::
የፃዲቁ ን ፀበል ልጄ አሻሸችው ወዲያው 5 ደቂቃ ሳይሞላው ተነስቶ ድኖ መጫወት ጀመረ ::

ይሄው አሁን 24ሰአት ሞላው ፍፁም ጤነኛ ነው
የኔ ፈጥኖ ደራሽ ምስጋና ይድረሳቸው! ለኔ እደደረሱልኝ ለእናተም ይድረሱላችሁ! አመስግኑልኝ የኔ አባት ተመስገን!

፨ሰላም ጆኒ እንደምን አለህ ምስክርነት ለመስጠት ነበር ፥ እግሬን አሞኝ ተማፅኛቸውና በግፍት ማርያም ፀበል ተዳብሼ ፈውሰውኛል
፥ አንድ ማናገር የምፈልገው ሰው ነበር ጥሩ ያልሆነ ነገር ትናገረኛለች ብዬ ፈርቼ ከፊቴ ቀድመው አስተካክሉልኝ ብዬ ተማፀንኳቸው ስደውልላት በጥሩ ሁኔታ አናገረችኝ መጨረሻውን ያሳምሩልኝ
፥ የሰው ብር ነበረብኝ እስካገኝ እና እስክከፍል እንዳይጠይቁኝ እርዱኝ አልኳቸው ሳይጠይቁኝ እንዳገኝ እና እንድከፍል ረድተውኛል
፥ በስራ ቦታ ቋንቋ እንዳልቸገር ረድተውኛል
፥ ስራ ረፍዶብኝ ምንም እንዳይሉኝ አድርገውልኛል ትራንስፖርትም ተቸግሬ እንዳገኝ አድርገውኛል
፥ እንድ የማስገባው ዶክመንት ነበር የጎደለው ነገር ነበር ምንም ሳይሉ እንዲቀበሉኝ እርዱኝ አልኳቸው ምንም ሳይሉ ተቀብለውኛል ሌሎችም ያስጨነቁኝ እና የጠየኳቸው ነገሮች ነበሩ ፈተውልኛል እኔ እና ቤተሰቤን ጠብቀው ለዚህ ቀን አድርሰውናል አሁንም ይጠብቁን አሁን ላይ አንድ የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ ስለ ጉዳዩ የተለያየ ህልም እያየሁኝ ነው ግራ ገብቶኛል ጨንቆኛል ይህን ነገር እስከመጨረሻው ፈተውልኝ ደግሞ ለመመስከር እንደሚያበቁኝ አምናለሁ ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ምስጋና ይሁን ለአጋዝዕተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ የአናዥጋው ቅዱስ እግዚአብሔር አብን መድሀኒአለምን አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሀንስን እናታችን ግፋት ማርያምን ሰሚነሽ ኪዳነምህረትን ቃጥላ ማርያምን እናታችን ቅድስት አርሴማን ልደታ ማርያምን ቅዱስ ጊዮርጊስን አቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ዮሀንስን ኤረር ባታ ማርያምን ፀበለ ማርያምን ጌቴሴማኒ ማርያምን ቅዱስ ገብርኤልን ቅዱስ ሚካኤልን እና እናታችን ታቦር ማርያምን አመስግኑልኝ እልልልልል ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን አንተም ጆኒ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅህ ዳግም ለደጃቸው ያብቁኝ የረሳሁት ነገር ካለ ይቅር ይበሉኝ

፨ሰላም የ እግዚያብሔር ቤተሰቦች የ ድንግል ማርያም የ አስራት ልጆች::
አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ያደረጉልኝ ተአምር
~ቤት ውስጥ በረሮ ያስቸግረኝ ነበር ለ እርሳቸው ነገርኳቸው አሁን የለም::
~ከ ባለቤቴ ጋ በግ ልንገዛ ወጥተን ሁለታችንም አንችልበትም እና አቡነ እጨጌ ይቅደሙልን ብዙ እንዳንደክም ብየ ነገርኳቸው አንድ ሰው ጋ ብቻ ተነጋግረን ገዛን::
~ወርሀዊ የ እርገግዝና ክትትሌ መልካም እንዲያደርጉልኝ ነግሬያቸው ነበር በ ጥሩ ሁኔታ ጨርሠውልኛል የኔ ደግ አባት :: እርሳቸውን የ ሠጠን አምላክ የተመሠገነ ይሁን ::እኔን ሀጢያተኛዋን የሠሙ እናንተን ይስሟችሁ::

፨selam wendme jhony abate lene yaregulgnen lememskr nber abaten betam amot hospital endehede tengrogn abate klalun yargult bye kelal honoletal tseblachewn eytetam ahun teshlotal yegubet sb teblo nber leabate ena lekatlawa negest ledengl maryam ngeriyachew teshlotal sersam akumo nber amot befetari fekad bembetachn amalajnet beabune echge erdata wedesraw temlsual chersew ymarut beakal meskralew ledjachew yabkugn
2. Wendme wedko leabate kfu endayasmun endishalew bye nber kber yegbachew teshlotal
3. Ebet west ቅዠት eyaschgern nber leabate ngeriyachew ahun fetsmo selamawi enklf new mentegnaw
4.enem telant denget amogn abate marugn bye seleadnoachewnena melkachewn erase lay aderge betam teshlognal yne abat kawekuachew jmro beydekikaw selmterachew reschew yalmeskrkut kale yekr belugn erson abat argo yesten cheru medaniyalm kber na mesgana yegbaw lembetachn dengl maryamem keberna mesgana ygbat lemlaktoch lhulum tsadkanena semeatat kebrna mesgana yegbachew

፨ሰላም ዩሐንስ እንደምን ሰነበትክ ምስክርነት ለመስጠት ነው ሐምሌ 29,2014 አቡነ እጨጌ ዩሐንስ ያደረጉት ታምር ይህ ነው በዕለቱ ስልጠና ስለነበረኝ ተዋክቤ ነዉ ከቤት የወጣሁት መንገድ ላይ ስደርስ የ አመቱ አቡነ እጨጌ ዩሐንስ መሆናቸው አስታውሼ ሻማ ሳላበራ እንኳን እያልኩ በፀፀት ዋልኩ ማታ ወደ ቤት ስመጣ የ ስምንት አመቱ ልጄ ካለወትሮ ተኝቶል እንዴት ተኛ ብየ ስጠይቅ ቤት ወስጥ የተበጠሰ የልብስ ማስጫ ገመድ አግኝቶ ታንቆ ባጋጣሚ የምታግዘኝ ልጅ ደርሳ አትርፋዋለች አባቴ በዕለተ ቀኖት ከዚህ ከባድ ሀዘን ስላወጡኝ ምስጋና ይድረሶት ክብርና ምስጋና ለ መድሐኒአለም ለ እናቱ ለ ድንግል ማርያም ለ አባቴ ለ አቡነ እጨጌ ዩሐንስ .ፈተና በዝቶብኛልና በፀሎት አስቡኝ ወለተስላሴ ብስራተመላክ ወልደማርቆስ ወልደፃዲቅ ሐይለእየሱስ ብላችሁ ከነቤተሰቦቸ አስቡኝ።

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን ሰላም ጆኒ ምስክርነት ለመስጠት ነው፡፡ መቼም አባቴ አቡነ እጨጌ እንደማይሰለቹኝ አመነቴ ነው በሁሉ ነገሬ ውስጥ የእሳቸው ስም ሳልጠራ አልውልምና፡፡ ከዘህ በፊት እግሬን አሞኝ አልድን ብሎ የእርሳቸውን እምነት፣ ጸበልና ምስላቸውን በማድረግ አሁን ደህና ነኝ አሁንም ጨርሰው እንዲምሩኝ እለምናለሁ፤ ሌላው ደሞ ልጄን እኔ የመረጥትኩት ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ ሞላ ተብዬ በጣመ አዝኜ ነበርና እርሳቸውን ጠይቄ ያጣሁት ነገር የለም በሶስተኛው ቀን በእርሳቸው አማላጅነት ይኀው ዛሬ ተቀብለውኛል፤ ክብር ምስጋና ለመድሐኒአለም በእለተ ቀናቸው ነገሮቼ ሁሉ መስመር ይዘውልኛል፡፡

፨ሰላም አንድ የማቀው ልጅ ሽፍቶች አግኝተውት ወግተውት ነበር ይሞታል ተብሎ ፈርቼ ነበር አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ለምኛቼው ነበር ልጁም ድኖ ቤት ተመልሷል ክብር ምስጋና ይግባው ለአባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ