Get Mystery Box with random crypto!

፨፨ምስክርነት _++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨፨ምስክርነት
_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን "አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
፨በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ጆኒ እንደምን አለህ?ለኔ አባቴ እጨጌ ዩሀንስ ያደረጉልኝን ተአምር ዳግም ለመመስከር ነው!!!

ፋይናል ፈተና እና ዲፌንስ በጥሩ ሁኔታ አሳልፋኝ ብዬ ተማፅኛቸው ነበር በሁለቱም ቀን ስእለ አድኖአቸውን ይዤ እባኮትን እርዱኝ ብዬ አልኩኝ። ክብርና ምስጋና ለቅድስተ ቅዱሳን ለንፅሒተ ንፁሀን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ይሁን ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ይሁን ዛሬ በጥሩ ውጤት ዲፌንስ አቅርቤያለሁ መጨረሻውን ያሳምሩልኝ። አመስግኑልኝ ሌላም የጠየኳቸው ነገር ስላለ መጨረሻውን ያሳምሩልኝ ።

፨Hi jonny mesekerent lemeset neber. Tilant Lijochen timehert lemasemezegeb yemegebeya fetena neber enam lijochem betam techenqew neber ye abune echgen mesle siel dertwa lay adergew gebu egezeabeher yimesgen huletum alefew temezegebewelegnal enem mesekeralhu beye neber abatachen kiber mesegana yideresachew ellllllll.

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ያረጉልኝን ለመመስከር ነው በደጃቸው ለሰባት ቀን ለመቆየት ፈተናዎች ቢገጥሙኝም በአባቴ በአቡነ እጨጌ ዮሐንስ እርዳታ በሰላም በደጃቸው ቆይቼ ፈውስን በረከትን ሰላምን አግኝቻለሁ።
ለእኔ እንደደረሱ ለእናንተም ይድረሱላችሁ! አሜን

፨endemn aleh jhon mskrenet lset new ebakh adrselegn sera botaye lay tlk chgr getmogn betam techenke neber abate abune echege yohannesen endiastekaklulgn lemgneachew eyetestekakelelign new esachew yaderegulgn bzu new ahunm mljachew ayleyen kibir le enatna lju amen

፨በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ሰላም ወንድሜ ጆኒ አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ያደረጉልኝ ተአምር ይህ ነው 1=የባለቤቴ አለቃው በጣም አስቸጋሪ ነበረና አባቴ ፀባዩን አስተካክሉለት ብዬ ለምኛቸው አሁን ሌላ አለቃ ተቀይሯል አዲሱ አለቃ ደግሞ በጣም መልካም ሰው ነው 2=ከእህቶቼ ጋር ለሁለት አመት ተጣልተን ተኮራርፈን ነበር ዛሬ እርቅ አድርገን ሰላም ወርዷል እልልልልልል

፨ሰላም ወንድሜ ,እመቤቴ ቃጥላ ማርያምና ፃድቁ አቡነ እጨጌ ዩሀንስ ያደረጉልኝን ልመሰክር ነበር ይለመንኳቸውን ፈፅመውልኛል 1,በለተ ቀናቸው የምስራች አሰሙኝ 2,አሁንም በለተቀናቸው የተደረገብኝ ነገር ካለ ጠቁሙኝ ብዬ ከባኞ ቤት ውስጥ በፌስታል የተጠቀለለ አፈር የሚመስል ነገር አስገኝተውኛል 3, ልጄን ከጆሮ ደግፍ በሽታ ምረውልኛል 4,ክፍለ ሀገር በሰላም ደርሼ ተመልሻለው 5,ብሬን አስመልሰውልኛል እልልልልልልልል ብላቹህ እሳቸውን ለሰጠን ለልዑል እግዚአብሔር እና ለቅድስት ድንግል ማርያም እና ለፃድቁ አቡነ እጨጌን እመስግኑልኝ

፨Wondim jony indet aleh ye abaten misikirinet liset new andit wolad betam techenka abaten terawachew fetnew dersew beselam gelageluat yend fetno derash abat amesginilign wondime!

፨ሠላም የሗንስ እንደምን አለህ ምሥክርነት ለመሥጠት ነበር አምላኬ ሆይ ሥለ አባቴ ይሗንስ ምንተነግሮ ያልቃ ለዘጠነኛ ጊዜ ነበር በ2አመት ውስጥ የመጣሁት አሁን ማለትም 11/29/2014እሚገርመው 9 ጊዜም ተደርጓልኛል እናም የሁኑ ልዩ የሚያደርገው እደተመለሥኩ በ30እቁብ እጠብቅ ነበር አልቅሸ ነግሬአቸው ነበር ስእላቸውን ከቤት ስወጣ ዛልይዝ ወጣሁ ከዛ ስደርስ ስአት ገና ነበር ከዛ ስራ ቦታ ገብቸ የለጠፍኳቸውን ልጨ በደረቴ ይዠ በቃ ዛሬ ይህ የሚያስፈራው አይንወት የኔ አቁብ ላይ ይረፍ አልኩ አመላክ ይመሥገን በቸርነታቸው በግ አለ ገረመኝ ችግሬን አለሉልኝ ተመስገን እልል በሉልኝ አሜን አሜን አሜን ለኔ የደረሠ ለናንተም ይድረሣችሁ ቦታውን ለማታቁ ሒዳችሁ ድንቅ ታምራቱን እንድታዬ አባቴ ፈቃዳቸው ይሁን ተመሥገን ተመሥገን ተመሥገን

፨+ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ሰላም ወንድሜ ጆኒ የፈጣሪ ስሙ የተመሰገነ ይሁንና አቡነ እጨጌ ዮሐንስን በጨነቀኝ ሰአት ሁሉ የምጠይቃቸውን ፈጥነው ምላሽ ይሰጡኛል አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤቴ ሰላም ጠፋ ከባለቤቴ ጋርም መግባባት አልቻልንም ፀባዩ ተቀያየረ ብዙ የለፋሁበት መስዋዕት የከፈልኩበት ትዳሬ አደጋ ላይ ነው የምናገረው ቃላቶች ሁሉ ለሱ አይመቸውም ከሰው ጋርም እንዳልገናኝ ከቤት እንዳልወጣ ነው የሚፈልገው ግራ ገብቶኛል አቡነ እጨጌ ዮሐንስ አረጋግተው ወደቀድሞው ሰላማዊ ህይወቴ እንዲመልሱልኝ በፀሎት አስቡኝ እሳቸውን ጠይቄ ሁሌም ምላሽ አገኛለሁ ልጅ ባለመውለዴ ነው ብዬ ጭንቀት ሊገለኝ ነው አባቴ ፃዲቁ ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ልጅ እንዲሰጡኝ እጠይቃቸዋለሁ እህተ ዮሐንስ ብላችሁ በፀሎት አስቡኝ አንተም ወንድሜ ያገልግሎት ዘመንህ ይባረክ አሜን

፨በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ስሜ ወለተ ወልድ ይባላል፤ አቡነ እጨጌ ዮሃንስ ያደረጉልኝን ምስክርነት ለመስጠት ነው፡፡ በአካል ገዳሙ ድረስ ለመምጣት አስቤ ባይሳካልኝም፣ ምስክርነት ለመስጠት ይህን እድል ስላገኘሁ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡

ከሶስት አመት በፊት ፈጣሪ ልጅ እንዲሰጠኝ ለቅዱሳኑ (በተለይም ለቅዱስ ገብርኤል፣ ለአቡነ ኪሮስ፣ ለቅዱስ ሩፋኤል፣ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ለአቡነ እጨጌ ዮሃንስ) ተስዬ ነበር፡፡ ፈጣሪም በቅዱሳኑ ምልጃ ፀሎቴን ሰምቶ ከአንድም ሁለት ልጆች ሰቶኛል፡፡ ቅዱሳኑን አመስግኑልኝ፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ ቦርሳዪ ከብዙ ዶክመንቶች ጋር ተሰርቆብኝ ነበር፣ በጊዜው ለአቡነ እጨጌ ዮሃንስ ቦርሳዬን ካስገኙልኝ ምስክርነት ለመስጠት ተስዬ ነበር፡፡ ቦርሳዬም ከነሙሉ ዶክመንቱ በጻድቁ ተአምር ከአንድ ቀን በኋላ ተመልሶልኛል አቡነ እጨጌ ዮሃንስን አመስግኑልኝ፡፡

በቦታው ተገኝቼ እንድመሰክር ደግሞ የልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ይሁን፡፡ የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሃንስ ምልጃና ረድኤት አይለየን፡፡

፨=በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱምላክ አሜን አባታችን አብነ እጨጌ ዩሀንስ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው አባታችንን በ ትንሹም በትልቁም ነገር ነው የምጠራቸው ሁሌም የጠየቁኳቸውን ነገር ያደርጉልኝል አሁን
1.ጓደኛየ ፈተና ተፈትኖ እንዲያልፍ ነግሬያቸው በጥሩ ዉጤት አልፏል
2.ሀይለኛ ጉንፋን ይዞኝ ቀላል አድርጉልኝ ብያቸዉ በትንሽ ቀን እየተሻለኝ ነዉ
3.የጠየኳቸው ብዙ ነገር ተሳክቶልኛል እግዚአብሔር ይመስገን
4.ሌላም የጠየኳቸው አለ የውጭ ኘሮሰስ እየጠበቁ ነው እንዲሳካልኝ በፀሎታቹ ፍቅርተ ማርያም ብላችሁ አስቡኝ የረሳዉት ካለ አባቴ ይቅር ይበሉኝ
ለተደረገልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ ለአባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ እልል ብላችሁ አመስግኑልኝ