Get Mystery Box with random crypto!

Share በማድረግ በረከት እናግኝ አንብቡት! 'እግዚአብሔር ሆይ! ለመቀበል መስጠትን አስተምረኝ ሲ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

Share በማድረግ በረከት እናግኝ አንብቡት!
"እግዚአብሔር ሆይ! ለመቀበል መስጠትን አስተምረኝ ሲሉ ሰምታችኋል።"
"ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃል?እናንተ ግን እኔን ሰርቃችሁኛል።እናንተም የሰረቅንህ በምንድን ነው?ብላችኋል በዐሥራትና በበኩራት ነው።ሚልክ 3÷ 8 ፥10." በማለት ከዐሥር አንዱን የእግዚአብሔር ድርሻ መውሰድ መሆኑን በግልጥ ተናግራል።
ወዳጆቼ በሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት ምዕራፈ ቅዱሳን[ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ]ገዳም!ገዳሙ ምንም መሬት የሌለው ሲሆን ለጠበል እና ለመባርክ የሚመጡ ምዕመናን አዳራሽ ማረፌያ ለመስራት ገዳሙ ቦታ አልነበረውም ፤በገዳሙ አካባቢ ያለው ምዕመን ወረዳውን (መንግስትን)በመጠየቅ መንግስትም ምላሹን በመስጠት የመሬት ግምት ካሳ የሚሰጥ (4,281,951.06)ገዳሙ እንዲከፍል ስለተጠየቀ በሃገርም በውጭም ያላችሁ የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ልጆች ወዳጆች እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ እርዱ ዐሥራታችሁን ስጡ፤ለመስጠት ለመርዳት እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነው፤ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ብድር ነው ዋጋ አለው።
"ሰው የእግዚአብሔርን ድርሻ በመስጠት ሲያስባርክ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ይባርካል" ዘዳ 26÷13
"በስውር የሰጥኸውን በግልጥ ይከፍልሃል።" ማቴ 6÷ 3
"ከማገኝው ሁሉ አስራት አወጣለሁ።" ሉቃ 18 ÷12
"ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር አንዱን እሰጣለሁ"ዘፍ 28÷ 22
" ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኝው ሁሉ ዐሥራት ታወጣለህ"ዘዳ 14÷22
"አብርሃም ለመልከ ጼዴቅ ዐሥራትን ሰጥቶታል።"ዘፍ 14÷20
"ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 4÷7 ከሌላው ያላገኝኸውን ከሌላ በልግስና ያልተሰጠኸው የራስህ የሆነ ምን ሀብት አለህ?ሲል" ሁሉ ነገራችን ሰውነታችን ዕውቀታችን ጉልበታችን ገንዘባችን ሁሉ .....ከእግዚአብሔር የተሰጠን መሆኑን ያስረዳናል።
"ዐሥራት መክፈል መስጠት እግዚአብሔር ባርክልኝ ብሎ አስባርኮ መመገብ ማለት ነው"
አገልግለን ሰርተን ደሞዝ ተቀብለን በአንድም በሌላም እግዚአብሔር የሰጠንን ዐሥራቱን ድርሻውን በመስጠት ብናስባርከው ትንሹን አበርክቶ :ቤታችንን በበረከት ሞልቶ:በደስታ በእርካታ አምላካችን ያኖረናል ማለት ነው።
በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እንናተ ራሳችሁ
በተሸለመው ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
ትን.ሐጌ 1፥4
Account name-Tegero Abune Echuge Yohannes(ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ)
Account no-1000199224054
SWIFT CODE-CBETETAA
Commercial Bank of Ethiopia(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ለበለጠ መረጃ፦0911190212/0911481388
-ፃዲቅን በፃዲቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን በረከት
ይወስዳል። ማቴ 10፥41
-እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል። ማቴ 10፥40
- እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን
ስራ እሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህ የሚበልጥ ያደርጋል።
ዮሐ 9፥12
-የአለም ብርሃን ናችሁ!
-ቅዱሳን በአለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን 1ቆሮ6፥2
-የቅዱሳን ጸሎት በሥራዋ እጅግ ታላቅ ኃይል ታደርጋለች።
ያቆ5፥14-19
-ከመረጥኩት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ። 88(89)፥3
- እናንተን የሚቀበል እኔ ይቀበላል፡ነብይን በነብይ
ስም የሚቀበል የነብዩን ዋጋ ይወስዳል።ፃድቅንም
በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል።
ምንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴ 10፥40-42
ጻድቁ በምልጃቸው ሃገራችንን ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጡን።ቃልኪዳን፤ጣባቂ ያላት ሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም የማትሆነው ቀድሞ የነበራች ከሁሉም የተለየች ሃገራችንን የቃልኪዳኑዋ አስራት ሃገር እምየ ቅድስተ ቅዱሳን ንጽህተ ንጹሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አስታርቃን በሃገራችን ያለውን ርሃብ ታጥፋልን ህዝቦቿን ትጠብቅልን።አሜን!!!
ቦታው፦ሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን መስመር መንዝ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣ አርባሃራ መድሃኒዓለም፣ እመጓ ቅድስ ኡራኤል፣ይገም ቅዱስ ሚካኤል፤እሳቷ ጽዬን ማርያም፣ዳስ አባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 12ሃዋርያት ገዳም መሄጃ ከአዲስ አበባ 195ኪሜ እንደተጓዙ "መዘዞ ከተማ"እንደደረሱ ከመዘዞ ከተማ የ1ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ ባዕለወልድ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ገዳም።
የገዳሙ ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ!
ለበለጠ መረጃ/# 0911190212/# 0911481388
Fb-(Johnny Aleme)