Get Mystery Box with random crypto!

+++/ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

+++/ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን "አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
=አቡነጨጌ ዩሀንስ አባቴ ያረጉልኝን ልመሰክር ነው ነፉሰጡር ሆኝ እህቴ ሰበላቸውን ሰጠችኝ እና በሰላም ይገላግልውኝ እያልሁ ሆዴን ፀበልውን ቀባሁን በህልሜ እቤቴ መጠው ካንዲትቀይሴት ጋር እየው ልጅሽን ሴት ልጅ ተቀበይን ብለው ሰጡኝ እናም በነጋታው ቀጠሮ ነበረኝ ስሄድ ዛሬ ትወልጃለሽ አልውኝ ሴትልጅ ወለድሁ በሰላም አማላጅነታቸው አይለየኝ አሁንም በደጃቸው ቆሜ ብዙ ነገር ለምኛቸዋለው ልመናየን ይስሙኝ ለመመስከር ያብቃኝ አሜን

=ሰላም ወንድሜ ጆኒ ምስክርነት ለመስጠት ነው ወለተሀዋርያት እባላለሁ ባለትዳር እና የ አንድ ልጅ እናት ነኝ።በትዳሬ ውስጥ ፈተና ገጠመኝ። ባለቤቴን ሴት መናፍስት በጣም አስቸገረችው፣ ተቸገርን አዳሩን እኔ ከጎኑ ተኝቼ ሲታገል ያድራል፣ ሲቸገር ያድራል።ከዚህ በፊት አባቴ ድንቅ ተአምራት ስላደረጉልኝ ዛሪም ተንበርክኬ አልቅሼ ለመንኳቸው አባቴ እጨጌ ዮሀንስ የለመንኳቸውን የጠየኳቸውን አልነፈጉኝም።ሁሉምነገር ሰላም ሆኖልኛል ሰላም ነን እልል ብላች አመስግኑልኝ።

=selam ....abate yohanis yadergulign lmemsker new kulaliten ke tilant jemro eyamemgn nbr ye abatachnin tsebel tetiche begdlachew teshsashche ahun dehna ngn Egziabher yimsgen.abune echuge yohanisn yesten yedingl mariyam lij yimsgen.

=በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አሜን ሰላም ጆኒ እኔ ተክለ ስላሴ እባላለው የአባታችን የፃድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ የተደረገልንን ለመመስከር ነው ሰሞኑ የወነ ሰዎች ገድላቸው ሰጥቼያቸው ስንት አመት ያስቸገሩ አይጦች ቤታቸው ሲገባ በሙሉ ጠፉ ሌላ ደሞ ሴትዬዋ ልጆቿ ይታመሙ ነበር በተለያየ ሱስ ይሰቃዩ ነበር አሁን ይህ ገድላቸው ቤታቸው ከገባ በዋላ ሁሉም ተስተካክሎዋል የእወነት እኔም በፃድቁ አባቴ አመሰገንኳቸው አሁን የፃድቁ አባታችን አምላክ መድሐኒያለም ስሙ የተመሰገነ ይሁን ፃድቁ ስማቸው የተመሰገነ ይሁን እኛም አሁን በእረፍታቸው መጥተን በረከታቸው እንድናገኝ መልካም ፍቃዳቸው ይሁን አሜን አሜን አሜን

=ሰላም ወንድሜ ዩሐንስ እንደምን አለህ። አባቴ አቡነ እጨጌ ዩሐንስ ዘፀገሮ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነበር። ዛሬ ት/ቤት ፈተና ነበረብኝ እንዲያቀሉልኝ ለመንኳቸው ፀሎትም አድርጌ ወጣው። እግዝአብሔር ይመስገን ቀሎኝ ሰርቻለው። ጥሩ እንደሚመጣም ተስፋ አለኝ። አደራ መስክርልኝ። በፀሎታቹ አስቡኝ

=ሰላም ጆኒ እንደምን አለህ ምስክርነት ለመስጠት ነበር ዳግም ለደጃቸው እንዲያበቁኝ ተማፅኛቸው ነበር ፈፅመውልኛል
አንድ ጓደኛዬ ቤት ውስጥ ከባለቤቷ ጋር ሰላም አልነበራትም የአባታችን የአቡነ እጨጌ ዮሀንስን ፀበል ምስል መልክአ እና እጣን ሰጠኋት አሁን ሰላም ሆነዋል እግዚአብሔር ይመስገን
የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ነበረብኝ በጣም እታመም ነበር ፈውሰውኛል
ስልክ ተበላሽቶ አሁን የምገዛበት ገንዘብ የለኝም እንዲሰራ እርዱኝ አልኳቸው ወዲያው ሰራ እግዚአብሔር ይመስገን
ሌላም የማውቃቸው ሰዎች ልጅ አልነበራቸውም ፀበል ሰጠኋቸው ምልክት አይተዋል መጨረሻውን አሳምረው ደግሞ ለመመስከር ያብቁኝ ሌሎችም የጠየኳቸው ነገሮች ነበሩ ፈተውልኛል እግዚአብሔር ይመስገን ምስጋና ይሁን ለአጋዝዕተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ የአናዥጋው ቅዱስ እግዚአብሔር አብን መድሀኒአለምን አባታችን አቡነ እጨጌ ዮሀንስን እናታችን ግፋት ማርያምን ሰሚነሽ ኪዳነምህረትን ቃጥላ ማርያምን ልደታ ማርያምን ቅዱስ ጊዮርጊስን ኤረር ባታ ማርያምን ፀበለ ማርያምን ጌቴሴማኒ ማርያምን አቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስን ቅዱስ ገብርኤልን ቅዱስ ሚካኤልን እና እናታችን ታቦር ማርያምን አመስግኑልኝ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን አንተም ጆኒ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅህ

=እንደምን ዋላችሁ የእግዚያብሄር ቤተሠቦች ዛሬም ደጋግሜ የፃድቁን እርዳታ እመሠክራለሁ። እናቴ እንቅፋት መቷት እግሯን አሟት ነበር ለፃድቁ ነግሬ መድሀኒት ወሥዳ ደህና ሆናለች። ሌላ ደግሞ አሁን በጣም የጨነቀኝ ነገር ነበር ሠላም አርጉት ብዬ። ጥሩ መልሥ ሠምቻለሁ። ፃድቁን ይሠጠን ሥላሤ ክብር ምሥጋና ይድረሠው።

=Selam joni lememesker new ebakeh adereselegn angete lay ende chert neger wetobegn neber ena abaten lemegn selke lay balew miselachew dabeshew neber ahun lewet alew
Ena degmo zare fetena neberebegn ena betam chenkogn neber endeferahut aydelem kebre mesgana le egziyabher yehun abate hulem yemiredugn kebre yederesachew

=Selam Jon endet nh meskernet lemstete nbr be 2/3 benberw guzo lay endalhed enkfatoch nbru neger gen hulunem chegeren le tsadiku setchachew hije nbr fetenaw yagatemegn sera bota nbr menm lifetalegn alchalem nbr besatu be magestu enkwan chigeru mnu gar endehone endalawk sera zeg nbr gen hulunem chegeren letsadiku setchachew dejachewn metaw negerkwachew hulunem neger segno sera segeba indiyastekakelulegn lemenkwachew tsadiku alasaferugnem segno segeba hulunem cheger fetulegn kechenket awtugne , kiber mesgana esachew lesten le dingel Mariya lj le Medhanialem yehun kiber mesgana le Embetachen yidresat kiber mesgana le abatachen echegie yeohanes yehun amen

=የኔ ፈጥኖ ደራሽ ጠርቻቸው አቤት ያላሉኝ ቀን የለም
1.ጓደኛየ በለሊት መንገድ ወጥቶ አጉል ቦታ የመኪናው መብራት ፍዝዝ ብሎ አላሳይ እንዳለው ነገረኝ እኔም ለአባቴ አደራ ምንም ሳይሆን አገሩ ይግባ እርስዎ ብርሀን ይሁኑለት ብየ ለመንኳቸው አላሳፈሩኝም በሰላም ደርሷል ለዛውም በደምብ እየታየው
2. እኔም ጉዞ ነበረብኝ በሰላም ገብቻለሁ
3. ጓደኛየ በድጋሚ ጉዞ ነበረበት መንገድ ላይ እረብሻ ስለነበር አባቴ ምንም ሳያሳዩ በሰላም እንዲያስገቡልኝ ነግሬያቸው በሰላም አስገብተውልኛል
4.ቀበሌ መሸኛ ላወጣ ሂጄ ፎቶ ያስፈልጋል ብለውኝ ደግሞ መብራት ጠፍቷል ሰውየው ደግሞ 9 ሰአት ላይ ኮስተር ብሎ ልዘጋ ነው አለኝ። ኧረ ባክህ መብራት ጠፍቶ ነው ትንሽ ታገሰኝ ነገ መንገደኛ ነኝ ብለው ብለምነው እምቢ አለ። ከዚያ ለአባቴ ዛሬ እንድንጨርስ አግዙኝ ብዬ ነግሬአቸው 10 ሰአት ላይ ፎቶ ይዤ ስሄድ አልዘጋም ጨራርሼ ተመለስኩ እግዚአብሔር ይመስገን። አባቴ ለኔ ለሀጢያተኛዋ በስራየ ለማላስደስት ለኔ ሳይቀየሙኝ ከጎኔ ናቸው ለምስክርነት ቃላት ያጥረኛል