Get Mystery Box with random crypto!

፨ጸበሉ(ያለምንም ጥርጥር የታመመ ሰው የሚድንበት)የታመመ ሰውናበተለያየ መንፈስ የሚሰቃይና በሰንሰለ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

፨ጸበሉ(ያለምንም ጥርጥር የታመመ ሰው የሚድንበት)የታመመ
ሰውናበተለያየ መንፈስ የሚሰቃይና በሰንሰለት የታሰረ ሰው ከ1-3ቀን ተከታታይ ጸበላቸውን ቢጠመቅ በ3ተኛው ቀን ላይ የሚድንና የሚሞት መሆኑን በጸበላቸው ይለያል፤ምልክት ያሳያል።

ከሰማይ የወረደው መስቀላቸው ከቤተመቅደሱ ሲወጣ ደመና ወርዶ እንደ ጥላ ይጋርደዋል፤ሲገባም ደመናው እያየነው ይበተናል በተለይበልደታቸው በህዳር29ቀን።ከዚህ ከጸበላቸው ባህር ውስጥ ከሰማይ የወረደው መስቀላቸው፣መቋሚያቸው፤ልብሳቸውናየእጅ መስቀላቸው ወጥቷል።

፨ አቡነ እጨ ዮሐንስ ዘጠገሮ፨፦ሰው ሆነው ከመዕላክት የተደመሩ የእሳት ክንፍ የተሰጣቸው እስራኤላዊ ጻድቅ ሲሆኑ የድንግል ማርያምን ጡት የጠብ መና ብቻ እየተመገቡ 500ዓመት የኖሩ መንዝንና ይፋትን ሃገሪ ነው የሚሉት ገድላቸው ላይ። ፀሐይን፣ጨረቃንናደመናን በእጃቸው እየያዙ የጸለዩ አባት ናቸው።

ይህ ጠገሮ ጸበላቸው ሲሆን በዚህ ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ድንግል ማርያም ከሁሉም ነገደ መላዕክት ጋር ከሐዋርያት ከነበያት ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር ወርዶ የረገጠው ያረፈበት የባረከው ቦታ ጸበል ነው ይህ ጠገሮ ገዳም.ከዚህ ከማይጎለው ጸበላቸው ባህር ሲሆን ጥልቀቱ የአካባቢው ሰዎች የ15 የሞፈር ርዝመት ማለት 45ሜትር አካባቢ ነው ይላሉ!

ከዚህ ባህር ውስጥ የአባታችን የአቡነ እጨ ዮሐንስ ከሰማይ የወረደላቸው መስቀል፣የእጃቸው መቋሚያ፣ገድላቸው፣ደረቅ አፈር፣የእጃቸው መስቀልና ልብሳቸው ከዚህ ከምታዩት ጸበላቸው ባህር ውስጥ ወጥቶ በዚህ ገዳም ይገኝል/።ገና ወደፊት ግዜው ሲደር ብዙ የሚወጡ ግን የታዩ ታቦቶች፣የወርቅ ከበሮ እና የወርቅ ዙፋንዎችናየተለያዩ ቅርሶች እንደሚወጡ አባቶች ይናገራሉ።ጸበሉም ከምታዩት ባህር ሳይጎል በአሸንዳ ወጥቶ ህዝበ ክርስቲያኑ በገድላቸው፣ ከሰማይ በወረደው መስቀልና የወርቅ መቋሚያቸው እየተዳበስ እንዲጠመቁ ይደረጋል።አቡነ ተክለሃይማኖት ቀጥሎ እጨጌ የሆኑ፤በስማችው ዝናብ፣ብርድንና ውርጭን የሚገዝቱባቸው ትልቅ አባት ናቸው።ህዳር 29ተወልደው፥ሐምሌ 29ያረፉበት
ቀን ነው።በአላቸውም 29 ከባዕለ ወልድ ጋርና ወራዊ በዓላቸውም ነው።በዚህ በጠገሮ ገዳማቸው የእጃቸው መስቀላቸው ከቤተመቅደስ ሲወጣ መስቀሉ ላይ ብቻ ቀስተ ደመና እና ደመና ወርዶ እንደ ዥንጥላ ተዘርግቶ መስቀሉን ይከተልና መስቀሉ ተመልሶ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ የወረደው ደመና ሲበተ የሚታይበት አስደናቂ ገዳም ነው።

[ቃልኪዳናቸው]፦ገዳሜን የረገጠ ፣መባ የሰጠ፣ገድሌን ያሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ቤተክርስትያኔን የረዳ ያሰራ የሰራ፣10ትውልድ እምረዋለሁ ልጅ እንቢ ያለው መሐን ቢሆንም ልጅ እሰጥዋለሁ፣የክርስትያን ማደርያ በሆነች ገነት(ደብረ ጽዬን)በብርሃን ቦታ አስቀምጠዋለሁ፤በገዳሜ ያረፈ መንኩሴ ከሆነ በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤በገዳሜ መጥቶ ያረፈ አይሁድም አረማዊም ቢሆን ያላመነ ያልተጠመቀም ቢሆን በገዳሜ ቢያርፍ እንደ መቃብሬ ጎለጎታ እንደተቀበር አድርጌ እቆጥርለታለሁ ይቅር እለዋለሁ ብሎ ጌታች መደሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ሰጥቶቸዋል።

ገድሌን በቤቴ ያስቀመጠ፦ እርኩስ መንፈስ፣ አጋንት ፣ቸነፈር ና ወባ በሽታ አይነካውም እንዲሁም መላኢከ ጽልመት አይነኩትም።

ገዳሙን ሐምሌ28/29 አዘጋጅቷል__
መነሻ_ሐምሌ 28
መመለሻ____ሐምሌ 29 ተባርከን መመለስ።

፨ሐምሌ 28/29 ታላቅ በዓል ንግስ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ዕረፍታቸው ሐምሌ 29 ነው።

፨ሐምሌ 28/29 የአመቱ የመጨረሻ ጉዞ ሲሆን ጸበሉ በክረምቱ ምክንያት ከጥንትም ጀምሮ ሐምሌ 29 የጻድቁ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ዕረፍት ዕለት የሚዘጋ ሲሆን፤ጸበሉ ተባርኩ መስከረም 29/2015 የጻድቁ መስቀላቸው መቋሚያቸው ወጥቶ ጸበላቸው ጋር ሄዶ ተባርኮ የመጠመቅበት ዕለት ነው።
ለበረከቱ ያብቃችሁ!

ቀድማችሁ ቁረጡ የመኪና እጥረት ስላለ እስከ !25/11/2014 ድረስ ትኬቱን ይቁረጡ በጉዞው ዕለት ትኬት አይኖርም።
እውነት የሄደ ሁሉ የሚድንበት በእጃቸው መስቀልና በመቋሚያ መዳበስ እረ መታደል ነው እምነት ይህ ነው።

ለበለጠ መረጃ#0911190212/0911481388!
አዘጋጅ ፦ጠገሮ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርሥያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ።!

[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ መዘዞ ከተማ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ በቤት መኪና በማንኝውም መሄድ ይቻላል።ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ የ2ሰዓት የእግር ጠገሮ እጨ ዮሐንስ ያስኬዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን!

አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like
+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431

+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME

+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme
+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5

+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/
...