Get Mystery Box with random crypto!

** የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ በትምህርት | Jigjiga University, Ethiopia

**

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁሉም የሀገሪቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል።

በታቀደው መሰረት ዩኒቨርሲቲያችን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል። ዩኒቨርሲቲው ተፈታኝ ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው የሚያስፈልጓቸውን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አዘጋጅቶ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና መላው የዩኒቨርሲርሲቲው ማህበረሰብም ለተፈታኝ ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል እያደረገላቸው ነው።
ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በደህና መጣችሁ!

**

Jigjiga University, following the decision made by the Ministry of Education to hold 12th grade national exams in all public universities of the country, the university has been working to be fully ready for administering successfully this exams.

As per the plan, the University has completed the preparations for the reception of those students who will take the 12th grade national exam. The University prepared for this students all different services that they will use during their stay in the campus and even during the exam.

The administration and the entire community of Jigjiga University are welcoming warmly all the students taking this exam.

Welcome to Jigjiga University!

#JJU
Follow us on:
Telegram: https://t.me/jjueth
Twitter: https://twitter.com/jjuethiopia

Contact us:
Info@jju.edu.et
https://www.jju.edu.et