Get Mystery Box with random crypto!

#ኢትዮጵያ የወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቀጣይ ላለባቸ | Jimmaa Abbaa Jifaar/ጅማ አባጅፋር እ/ኳ ክለብ

#ኢትዮጵያ

የወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቀጣይ ላለባቸው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል

ካነሷቸው ነጥቦች መካከል :-

√   ከእኔ በፊት ለነበሩት አመራር ትልቅ ክብር አለኝ ፣ ወደዚህ ሀላፊነት ስንመጣ የሪፎርም ጥናት አድርገን የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ተሰርቷል ።

√ የብሔራዊ ቡድን ግንባት ላይ ትኩረት ሰጥተን ሰርተናል ።

√ አስራ ሶስት አመት ተዘግቶ የነበረው ካፍ አካዳሚ መጠቀም መጀመራችን ለብሔራዊ ቡድኖቻችን ግልጋሎት ሲሰጥ ከፍተኛ ወጪን ቀንሷል ።

√ የካፍ አካዳሚን አሁን ካለበት በተሻለ ደረጃ ለማዘመን በመጪው አራት ዓመት ሰርቶ ለማስረከብ ዋነኛ አለማዬ ነው ።

√ በቀጣይ የአራት ዓመት ጉዟችንን ገምግመን ተቋማዊ ለውጥ ላይ እንሰራለን ።

√ አሁን ላይ ካለው የተሻለ የስፖንሰር ስምምነት ሊኖረን ይገባል ፣ እኛ ስንመጣ ተቋሙ ከነበራዊ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ የሚታወቀው በሽብር ነው ፣ አሁን ላይ ግን በመልካም ነገር ነው ።

√ ይህንን እይታ በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ እና ተጨማሪ ስፖንሰሮችን ለማምጣት በተሻለ እንሰራለን ።

√ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ ከስፖርቱ ባለፈ #ለሀገራዊ_ምርጫ ምሳሌ እንዲሆን እንፈልጋለን ።

√ ጉባኤው ምን እንደሚሰራ ያውቃል መራጩ 26 ሰዎች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው ያውቃሉ ።

√ የሴቶች ሊግ ፣ ሱፐር ሊግ እና ብሔራዊ ሊግ በቀጣይ የፊፋ ፕላስ ተጠቃሚ እንዲሆን እናደርጋለን ፣ ይህም የምስል መብቶችን ለመሸጥ ይረዳናል ይህንን ለማድረግ ስራዎች ተጀምረዋለል ።

√ ይህን ፕሮጀከት ለመስራት ከጣልያን ተቋም ጋር ከዓመታት በፊት ብንስማማ በወቅታዊው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል ።