Get Mystery Box with random crypto!

#በክለባችን ዙርያ በዛሬዉ እለት በክለባችን የቦርድ አመራሮች፤ ደጋፊ ማህበር እና ዳጋፊዎች ጋር | Jimmaa Abbaa Jifaar/ጅማ አባጅፋር እ/ኳ ክለብ

#በክለባችን ዙርያ በዛሬዉ እለት በክለባችን የቦርድ አመራሮች፤ ደጋፊ ማህበር እና ዳጋፊዎች ጋር ዉይይት ያደረግን ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ዉይይት ያደረግን ሲሆን ክለባችንን በ2015ዓ.ም ከፍተኛ ሊግ ላይ በምን መልኩ አጠናክረን በቀጣይ 2016ዓ.ም ወደ ሊጉ ለመመለስ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በአግባቡ ስራዉን እንዲወጣ እናም ዉል ያላቸዉን ነባር ተጫዋቾች እና ዉላቸዉን ያጠናቀቁ ያማከለ ዉይይት አድርገናል፡፡

በዚህም መሰረት በቅርቡ የክለባችን የበላይ አመራሮች እና ቦርድ አባላት ያለፈዉን አመት ግምገማ በማከናወን በቀጣይ ሚሰሩ ስራዎች ዙርያ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ቀጥታ ክለባችንን የሚያጠናክሩ ስራዎችን በመስራት ክለባችንን ቶሎ ወደ ሊጉ ለመመለስ ታቅዶ ስራዎች ከወዲዉ መሰራት ተጀምረዋል፡፡