2022-07-04 09:44:12
☞ #የሴት ፈተና ኢስላምክን እንዲህ ሊያስጥልክ
ይችላልና ተጠንቀቅ **
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺍﻋﻈﻢ ﺍﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻨﻘﺺ ﺍﻳﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ
በሚስር(ግብፅ) ከተማ ውስጥ መስጂድን በአዛን
በሰላት አጥብቆ የሚይዝ አንድ ሰው (ሙዓዚን) ነበር። በርሱም ላይ ጥሩ መታዘዝ እና የኢባዳህ ብርሃኖች ይታዩበት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ መናራህ
ወጣ፡ ታዲያ አዛን ላይ ሆኖ ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ አንዲትን እንስት ይመለከታል ከመቅፅበት
በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቃል ፡
በፍጥነትም እርሷ ወዳለችበት ቤት ይሄድና ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች
#እርሱም፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው
የምፈልገው
#እርሷም ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"
ብላ ጠየቀችው
#እርሱም፡- ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን
መሰባሰቢያ ይዘሺዋል አላት
#እርሷም፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ
ልልህ አልችም አለቸው
#እርሱም፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት
#እርሷም ፡- አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ
(ክርስቲያን) ነኝ አባቴ ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም አለችው"
#እርሱም፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት፡
#እርሷም ፡-እንደዛ ያደረግክ እነደሆን (ክርስቲያን ከሆንክ) እኔም ፍቃደኛ ነኝ (አገባሀለሁ)
ከዚያም ይሄ ሰው እርሷን ለማግባት ሲል ነሳራ
(ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት ተቀመጠ
ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ
ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወደቆ ወዲያኑ # ህይወቱ_አለፈች ፡:
እርሷንም ሳያገኝ እስልምናውን አጥቶ በኩፍር
ላይ ሞተ ። (አል፡ዳኡ ወ’ደዋአ ሊኢብኑ አል፡ቀይም ገፅ 167)
ሰዓይድ ኢብኑ ሙሰየብ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ይል ነበር፡ <<አላህ ሱብሀነ ወተዓላ አንድንም ነብይ አላከም፡ሸይጣን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ>>
(መውሱዓቱ ኢብኑ አቢ ዱንያ ቅጽ 4 ገፅ 540)
አል-ሀሰን ኢብኑ ሳሊህ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ሲል ይናገራል፡ <<ሸይጣን ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፡አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፡እኔ በአንቺ
የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ ደግሞም ባንቺ
ከወረወርኩ አልስተም፡እንቺ የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፡አንቺ የኔ የጉዳዬ መልክተኛ ነሽ>>
(መውሱዓቱ ኢቡኑ አቢ ዱንያ ቅፅ 4 ገፅ 539)
ለወንድ ልጅ ከባዱ ፈተና የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ ፈተና በኋላዬ አልተውኩም
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)
--------------------
mohammed ebnu seid
-----------------------------
በቴሌግራም ይ ላ ሉን!
➢
@Lewetatoch_mekir
https://t.me/Ethio_Suna_Media
https://t.me/Ethio_Suna_Media
399 viewsAbu Umar Ibnu Sadik, 06:44