2022-05-24 11:17:38
ቀላል ይሆናል!
አብዛኛው ጊዜ ለማድረግ በጣም ትክክለኛው ነገር ከባዱ ነው፤ ከባዱን ለማድረግ ፍቃደኛ የሆኑት ብቻ ናቸው የደስታን ጥግ የሚያዩት። ከአልጋ በጠዋት መነሳት ቀላል አይደለም፤ ቁምነገር የሞላው ምንም የማያስቅ መፅሀፍ ቁጭ ብሎ ማንበብ ቀላል አይደለም፤ አታላይ በበዛበት አለም በሀቅ ለፍተህ ሀብታም መሆን ቀላል አይደለም፤ ቀላል ቢሆንማ ሁሉም ያደርገው ነበር እኮ።
ቀላሉን ከመረጥክ ህይወት ከባድ ትሆናለች፤ ከባዱን ካደረክ ህይወት ቀላል ትሆናለች። ወዳጄ እስክትለምደው ነው እንጂ አሁን ከባድ የመሰለህ ነገር ሁሉ በሂደት ቀላል ይሆናል።
2.1K views08:17