Get Mystery Box with random crypto!

Jafer Books 📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ jafbok — Jafer Books 📚 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jafbok — Jafer Books 📚
የሰርጥ አድራሻ: @jafbok
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.36K
የሰርጥ መግለጫ

የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok
ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL
ለዌብሳይት www.jaferbooks.com

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-18 08:31:41
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ስድስት ኪሎ ካምፓስ በተዘጋጀው የመጽሐፍ ዐውደ ርዕይና ባዛር ላይ እንገኛለን ::

ዛሬ አራተኛ ቀኑ ነው ::

እስከ እሁድ ድረስ ይቀጥላል ::
1.9K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 17:12:51
በዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ የተዘጋጀው " ከሞት ባሻገር " የተሰኘው መጽሐፉ ሁለተኛው በመደብራችን ይገኛል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::
1.9K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 08:09:09
አዲስ የግጥም መፅሐፍ በገበያ ላይ
የነፍስ ጥምረት
መፅሀፉ  ስለ ሀገር ፣ቤተሰብ፣ጓደኝነት፣ጥልቅ ፍቅር እንዲሁም የተለያዩ ሀሳቦችን ያዘለ ነው።

ቄጠማ
 
እዘኑላት እስቲ ለቄጠማ ህይወቷ
አጭደው ሲዋቡባት ዝም በማለቷ
ጎዝጉዘው ሲረግጧት ሲዘሉባት ውለው
ጠርገው ይጥሏታል ጠውልገሻል ብለው ።
2.7K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 18:37:32
በዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ የተዘጋጀው " ከሞት ባሻገር " የተሰኘው መጽሐፉ ሁለተኛው በመደብራችን ይገኛል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::
2.8K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 18:32:31
በአድኃኖም ምትኩ የተደረሰው " አዎ ! እሱ ጋ ያመኛል " የተሰኘው መጽሐፍ በመደብራችን ይገኛል ::

"... አክሱም ወይ ላሊበላ አልያ ፋሲለደስ በስንት ቢሸጥ ያዋጣል ?? ታሪክስ ይሸጣል ? ...

... አቅም የሆነኝ ፣ የሕይወት ጣዕም ያልተማጠጠብኝ ትላንቴ ላይ ተተክዬ ነው :: ትናንትሽን ሽጪልኝ ነው የሚሉኝ :: እኔ ከትናንቴ ውጪ ምን አለኝ ? ... "

መጽሐፉ መደብራችን ይገኛል !!
2.7K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 18:22:36 " ወታደራዊ ካምፕ የመሰለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ልደት አዳራች AK 47 በታጠቁት የፀጥታ ኃይሎች ተወሯል፡፡ ድባቡ ያላስፈራቸው ለለውጥ ያጐፈሩት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ግን አሁንም ያሻቸውን ከመጠየቅ ወደ ኋላ አላሉም፡፡ አፍታም ሳይቆይ መድረኩ በሁለቱ ኃይሎች ፍጥጫ ወደ አስፈሪነት ተቀየረ፡፡ ሠይፉ ዮሐንስ እና ሶል ኤኮስ ባንዶች ግን ነገሩን የተረዱት አይመስልም፡፡ አሁንም ሙዚቃቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ ሰይፉ ሦስት ያህል ዜማዎችን በተከታታይ ካቀረበ በኋላ ተሾመ ተረኛ ሆኖ ወደ መድረኩ ብቅ አለ፡፡ ተማሪዎቹ “መሬት ላራሹ" የሚለውን መፈክራቸውን ትተው በኅብረት ተሼ! ተሼ! ተሼ! ወደ ማለት ዞሩ፡፡

የእነርሱን ድፍፈረትና አብዮተኝነት የተዋሰ ለመሆኑ ቅንጣት ታህል አልተጠራጠሩም፡፡ ለዚህ ደግሞ ባላባታዊ ሥርዓቱን ነቅፏል ተብሎ የተወራለት “ጋራ ሥር ነው ቤትሽ” ሙዚቃ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ ይህ ሥራ ራሱ ተሾመም እንደሚገልፀው በጊዜው የነበረውን የመደብ ልዩነት ወገግ አድርጎ ለማሳየት የተፃፈነው፡፡ ጋራው ባላባታዊ ሥርዓቱን ሲወክል በስንኞቹ ውስጥ ያለው ገጸ-ባሕርይ ደግሞ ታችኛውን መደብ ያስታውሳል፡፡

በእጆቼ እየዳሰስኩ እንዳላጫውትሽ
ሰው ከማይደርስበት ጋራ ሥር ነው ቤትሽ (2)
ዓይኔ ከሩቅ አይቶ ይረጫል እንባውን
በምን አቅሜ ችዬ ልምጣ ተራራውን

ተሾመ በዛ መድረክ ምስጋናውን ለማቅረብ ጎንበስ ብሎ ቀና ባለበት ፍጥነት ዝማሬው ተቀየረ፡፡ ፋኖ ተሰማራ የሚለውን መዝሙር እንዲያቀርብ የፈለጉ ተማሪዎች በጋራ ዜማውን በማቅረብ ይገፋፉት ያዙ፡፡መደማመጥ አዳጋች በሆነበት መድረክ መኻል የተገኙት ተማሪዎች ተሾመ ይሄን መዝሙር እንዲጫወተው መጠየቃቸውን ቀጠሉ፡፡

በጥቂቶች የተነሳው ሀሳብ የሁሉም ሆነና “ሶል ኤኮስ ባንድ” ይህን ብቻ እንዲያቀርብ አስገዳጅ ድባብ ተፈጠረ፡፡ በመንታ መንገድ መኻል የቆመው የቀበናው ተወላጅ ተሾመ ምትኩ ሥራውን ለማቅረብ አልደፈረም፡፡ መድረኩን ለቆ ቁልቁል ተንደረደረ፡፡ ተማሪዎቹም ጩኸት ማሰማታቸውን ይበልጥ ጨመሩ፡፡ ግራ የተጋባው ድምፃዊው ከፀጥታ ኃይሎች ተወካይ ጋር ስለ ሆኔታው መከረ፡፡ …"

" ጠመንጃና ሙዚቃ "
በይነገር ጌታቸው
የመጀመርያ ዕትም

መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::
2.2K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 18:22:35
1.8K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 17:26:53
ለታዳጊ ልጆችዎ የእንሊዝኛ በእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ይሹምቱላቸው ::

ባለቀለም ዕትመት
በቀለም ምስል የታገዘ
በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል
ጎላ ያሉ ፊደሎች

ምርጥ መዝገበ ቃላት ነው ::

አያምልጣችሁ ::
2.0K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 17:13:55
እንግሊዝኛ ቋንቋን ለማዳበር ለምትፈልጉ ፤  እንዲሁም የቋንቋ ትምህርት ቤት ላላችሁ ። ለቋንቋ መምህራን እጅግ አስፈላጊ መጻሕፍት አስገብተናል ::

@jafbok
2.1K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 07:48:58
" ፍኖተ መድሀኒት " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

መጽሐፉ ....

- የሰው ልጅ የሺህ ዘመናት ጉዞን በመድሀኒት በኩል ለማሳያት ይሞክራል፡፡

- የሰው ልጅ በሽታ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብሎ ያምን ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ አሁን ላይ እንዴት የዘረ መል ህክምና እንደደረሰ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

- የፍልስፍና ጥማት ካለብዎ፣ ከቀደምት የግሪክና የሮማ እና ከአረብ ፈላስፋዎች  ጋር ያስተዋውቃል፡፡

- መድሀኒት በዘመናዊ መንገድ ለማግኘት የሚያልፍባቸው ሳንይሳዊ መንገዶች በዝርዝር ያስቃኛል፤ የተመረጡ መድሀኒቶች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ ያመላክታል፤ የሰው ልጅ ለሳይንስ ያለውን ቁርጠንኝት ያደንቃሉ፤ይደማመሉ፡፡

-  መድሀኒቶች ለማግኘት ገፊ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ይፈተሻሉ፡፡ ምን አይነት ማህበራዊና ኢኮኖሚ ሁነት ስለነበር ነው መድሀኒቶቹ ሊገኙ የቻለው የሚለውን ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

- የፖለቲካ ጥማት ካለብዎ ሶሻሊዝም፣ ካፒታሊዝምና ዮጄኒክስ አስተሳሰብ/እንቅስቃሴ ከመድሀኒት ጋር ተላቁጠው ቀርበዋል፡፡ ከናዚ እስከ ታሊባን፣ ከከቴዎዶር ሩዝቬልት እስከ አዶልፍ ሒትለር፣ ከአዶልፍ ሒትለር እስከ ሙላህ ኡመር እና ኦሳማ ቢላደን ተቃኝተዋል፡፡

- መድሀኒት በተመለከተ የሚነሱ ሀይማኖታዊ እና ፖቲካዊ ሙግቶች/ክርክሮች፣ የሞራል ተጠየቆች በሚገባ ከታሪካዊና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ጋር ተሰናስለው ቀርበዋል፡፡

መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል ::
2.6K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ