Get Mystery Box with random crypto!

𝗧𝗵𝗲 𝗝𝗮𝗰𝗼𝗯𝗶𝘁𝗲 𝗔𝗽𝗼𝗹𝗼𝗴𝗲𝘁𝗶𝗰𝘀

የቴሌግራም ቻናል አርማ jacobite_apologetics27 — 𝗧𝗵𝗲 𝗝𝗮𝗰𝗼𝗯𝗶𝘁𝗲 𝗔𝗽𝗼𝗹𝗼𝗴𝗲𝘁𝗶𝗰𝘀 𝗧
የቴሌግራም ቻናል አርማ jacobite_apologetics27 — 𝗧𝗵𝗲 𝗝𝗮𝗰𝗼𝗯𝗶𝘁𝗲 𝗔𝗽𝗼𝗹𝗼𝗴𝗲𝘁𝗶𝗰𝘀
የሰርጥ አድራሻ: @jacobite_apologetics27
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 805
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተከፈተው ለሙስሊም ወገኖቻችን መልስ መስጫ እንዲሆን ታስቦ ነው ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 20:13:54 «ዩኑስና ዓሳው...»

የቁርኣን ተርጓሚዎችን እጅግ ግራ ካጋቡ አንቀጾች አንዱ በሱረቱል አንቢያ (21) እና ሱራ አል-ሷፋት (37) ላይ የሚገኘው የዩኑስ ታሪክ ነው።

«የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ። ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡»
-21:87-88

ኢብኑ ከሲር ፣ ኢብን ዐባስ ፣ አስ-ሱዩቲና ሌሎች ተርጓሚዎችን ጨምሮ አብዛኞቹ ሙስሊም ሊቃውንት የዩኑስ የቁጣ ምንጭ እንዲገስጻቸው የተላከላቸው የነነዌ ሕዝብ ንግግሩን አልሰማ ማለታቸውና ይልቁንም በእርሱ ላይ አካላዊ ጥቃት ለማድረስ መሞከራቸው እንደሆነ ይስማማሉ። የቁርኣን ደራሲ ግን በዚህ አያበቃም። ዩኑስ ከአሏህ ፍቃድ ሳያገኝ ከነነዌ ሕዝብ በንዴት እንደሄደና በዚህም አሏህ እንደቀጣው የነገረን ሙሐመድ በሱራ አል-ሷፋት (37:139-148) ደግሞ ዩኑስ ወደ ነነዌ ሕዝብ ከመላኩ በፊት በባሕር እንደሰጠመና ከዓሳው ሆድ ከወጣ በኋላ ወደ ነነዌ ሕዝብ እንደተላከ ይነግረናል።

ዩኑስ ወደ ነነዌ ሕዝብ የተላከው ከመስጠሙ በፊት ነው ወይስ በኋላ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የተቸገሩት ሙፈሲሮች ይህን የቁርኣን ግጭት ለመሸፈን ብዙ ዓይነት ማብራሪያዎች አቅርበዋል። ዩኑስ ወደ ነነዌ ሕዝብ ከመሄዱ በፊት ነው የሰጠመው የሚሉ ቡድኖች በአንቀጹ መጀመሪያ የተገለጸውን የዩኑስ ንዴት ማብራራት ሲቸገሩ ዩኑስ ወደ ሕዝቡ ከመሄዱ በኋላ ሰጠመ የሚሉት ደግሞ በሱራ አል-ሷፋት (37:148) የተገለጸው የዩኑስ ወደ ነነዌ ሕዝብ መላክ ትርጉም ሊሰጣቸው አልቻለም። ዩኑስ ሁለት ጊዜ ወደ ነነዌ ሕዝብ ተላከና ወደ ሁለት የተለያዩ ሕዝቦች ተላከ ያሉም አልጠፉም። እነዚህ ሁሉ ማብራሪያዎች ግን በቀጥተኛ የቁርኣን ንባብ የማይደገፉና አንቀጹን ከማብራራት ይልቅ አላስፈላጊ የታሪክ ማርዘም ውስጥ የሚገቡ ናቸው። የቁርኣን ደራሲ ስለሚናገረው ታሪክ ትክክለኛ ቅደም-ተከተልም ሆነ ትልም ደህና እውቀት እንዳልነበረው ግልጽ ነው።

@Jacobite_apologetics27
169 viewsTinsae, edited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:13:37
158 viewsTinsae, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:39:55በእንተ ማርቆስ 16:9-20

ክፍል ፬

ከዚህ በፊት በነበሩት ሶስት ክፍሎች የማርቆስ ወንጌል መደምደሚያ ክፍልን ታሪካዊነት የሚተቹ ሰዎች የሚያቀርቡትን ደካማ ሙግትና እነዚህ አካላት ከሚጠቅሷቸው ጽሑፎችና ምስክሮች ብዙ ዓመታት ቀድመው የኖሩ አባቶች ስለ ክፍሉ ታሪካዊነት የተናገሩትን ምስክርነት አይተናል።

በትችት አቅራቢዎቹ የሚነሱት ዋነኛ "ማስረጃዎች" ታዲያ ኮዴክስ ሳይኔቲከስና ኮዴክስ ቫቲካነስ የተሰኙ ሁለት እደ-ክታባት ናቸው። እነዚህ ቅጂዎች በአንጻራዊነት ጥሩ የሚባል የጽሕፈት ጥራትና እድሜ ስላላቸው የማርቆስ ወንጌል ማገባደጃ ክፍልን አለመያዛቸው የክፍሉን ታሪካዊ አለመሆን ያሳያል የሚለው ሙግት ደጋግመን የምንሰማው ነው። ይህ ድምዳሜ ግን ፈጽሞ ከእውነታ የራቀ መሆኑን መገንዘብ አይከብድም።

በመጀመሪያ እነዚህ ሁለቱ እደ-ክታባት የተጻፉት በአራተኛ ክፍለዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው። ከዚህ በፊት እንዳየነው ደግሞ ሄሬኔዎስና ዮስጢኖስን ጨምሮ ሌሎች ብዙ አባቶች የማርቆስ ወንጌልን የመጨረሻ ክፍል እንደሚያውቁ እርግጥ ነው። ታዲያ እነዚህ አባቶች በሙሉ ከሁለቱ ኮዴክሶች ብዙ ዓመታት በፊት መኖራቸውን ልብ ይሏል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ሁለቱ ኮዴክሶች ክፍሉን ባይዙ እንኳን የምናወራለት ክፍል ከዚያ የቀደመ እድሜ ስላለው የእደ-ክታባቱ ሙግት የማርቆስ ወንጌል ማገባደጃ ክፍል አለም-አቀፋዊ ተቀባይነት እንዳልነበረው ከማሳየት ውጪ ምንም አያረጋግጥም።

ከዚህ ባለፈ ግን የኮዴክስ ቫቲካነስ ጸሐፊ እንኳን ክፍሉን ያውቀው እንደነበር የሚያሳይ አጻጻፍ ተጠቅሟል። በዚህ እደ-ክታብ ውስጥ ጸሐፊው በምስሉ እንደምትመለከቱት ጽሑፉን በሶስት ረድፎች የገለበጠ ሲሆን የማርቆስ ወንጌል አልቆ የሉቃስ ወንጌልን መጻፍ ሲጀምር ግን አንድ ረድፍ ከግማሽ ክፍት ቦታ በመተው ነበር። ይህ ደግሞ ጸሐፊው በእርግጥም ክፍሉን ያውቀው እንደነበርና የእደ-ክታቡ ባለቤት ልክ መስሎ ከታየው ክፍሉን በራሱ እንዲጽፍበት ምርጫ እየሰጠው እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ምንም እንኳን በሌሎች ክፍሎችም ተመሳሳይ ክፍት ቦታዎች ብናገኝም እነዚህ ክፍተቶች ግን የራሳቸው ማብራሪያ ሊቀርብላቸው የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ አንዱ ክፍት ቦታ መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ አልቆ መዝሙረ ዳዊት ሲጀምር የሚገኝ ሲሆን ይህ ክፍተት ግን መጽሐፈ ዕዝራ በሶስት ረድፍ ተጽፎ መዝሙረ ዳዊት ግን በሁለት ረድፍ በመጻፉ ጽሐፊው የአጻጻፍ ቅርጹን ለመለወጥ እንዲያመቸው የግድ ክፍት ቦታ መተው ስላስፈለገው የተፈጠረ ነው። ከዚህ ባለፈ ክፍት ቦታው ከሞላ ጎደል የማርቆስ ወንጌል 16:9-20 ን ለመጻፍ የሚበቃ መሆኑ በራሱ ጸሐፊው ክፍተቱን ለዚሁ ዓላማ እንደተወው የሚያሳይ ነው።

አስቀድመን እንዳልነው ይህ የማርቆስ ወንጌል ክፍል ከማንኛውም እጃችን ላይ ካሉ እደ-ክታባት የቀደመ የአባቶች ምስክርነት ያለው ነው። ካሉን በሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት ውስጥ ክፍሉን ያልያዙት እደ-ክታባት ብዛት ሶስት ብቻ መሆኑ ደግሞ ከረጅሙ የማርቆስ ወንጌል ማገባደጃ ይልቅ ቁጥር ስምንት ላይ የሚያልቁ ቅጂዎች እጅግ ያልተለመዱ እንደነበሩ የሚያሳይ ነው። ይህ ደግሞ ለማርቆስ ወንጌል ማገባደጃ ክፍል ከረጅም እድሜ በተጨማሪ አለም-አቀፋዊ ተቀባይነትን የሚሰጥ ነው።

Reference

-Authentic; The Case for Mark 16:9-20 by James snapp Jr.

@Jacobite_apologetics27
264 viewsTinsae, edited  10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:39:37
244 viewsTinsae, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:20:02 ቁርኣንን ጊዜ ሰጥቶ ያነበበ ሰው በተደጋጋሚ እንደሚለው "ግልጽ መጽሐፍ" ሳይሆን ግራ የተጋባ አጻጻፍና ሰዋሰው የተከተለ መሆኑን በሚገባ ይረዳል። አንዳንዴ ጥቅሶቹ እጅግ ውስብስብ ከመሆናቸው የተነሳ ማን እንደተናገራቸው እንኳን ማወቅ አዳጋች የሚሆንበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በሱራ ዩሱፍ ላይ ዩሱፍ ከጌታው ሚስት ጋር መዘሞትን እምቢ በማለቱ ምክንያት በውሸት ክስ እንደታሰረ የቁርኣን ደራሲ ከተናገረ በኋላ 12:51 ላይ ሚስትየው እንደተጸጸተችና የእርሱን ንጽሕና እንደመሰከረች ይነግረናል።

«...የዐዚዝ ሚስት፡-«አሁን እውነቱ ተገለጸ፡፡ እኔ ከነፍሱ አባበልኩት፡፡ እርሱም ከእውነተኞቹ ነው» አለች፡፡»(12:51)

ከዚህ ቀጥሎ የሚመጡት ሁለት ጥቅሶች ግን ተናጋሪያቸው ማን እንደሆነም ሆነ ለማን እንደተናገረው ማንም አያውቅም። አረብኛው ከሞላ ጎደል ሲተረጎም እንዲህ ይላል-

«ይህም በድብቅ እንዳልካድኹት አሏህም የከሃዲዎችን ተንኮል እንደማያቀና እንዲያውቅ ነው። ራሴንም ከስሕተት አላጠራም ፤ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በቀር ነፍስ ሁሉ በመጥፎ ነገር አዛዥ ናትና። ጌታዬም በጣም መሃሪ አዛኝ ነው።»(12:52-53)

የተወሰኑ ሙፈሲሮች ተናጋሪው የዐዚዝ ሚስት እንደሆነችና "እንዳልካድኹት" ያለችው ዩሱፍን መሆኑን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እንዳልካድኹት ያለችው ባሏን መሆኑን ይናገራሉ።[1] ሌሎች ደግሞ ተናጋሪው ዩሱፍ እንደሆነና "እንዳልካድኹት" ያለው ጌታውን መሆኑን ሲያመለክቱ አልካድኹትም ያለው አሏህን ነው ያሉም አሉ። አንዳንዶች እንደውም ተናጋሪው ዐዚዝ እንደሆነና አልካድኹትም ያለው ዩሱፍን እንደሆነ ያስባሉ። ኢብኑ ከሲር ሙሉ ንግግሩ ከላይኛው ጥቅስ የቀጠለ ስለሆነ የሴትየዋ ንግግር ነው ሲል ኢብን ዐባስ ደግሞ ሙሉ ንግግሩ ጅብሪል ወደ ዩሱፍ በተላከ ጊዜ ዩሱፍ የተናገረው ነው ይላል። የተሰጡትን ብዙ ማብራሪያዎች ስንዘረዝር መዋል እንችላለን ፤ እውነታው ግን ጥቅሱ የድርጊቱን ባለቤት ለማወቅ በማያስችል መልኩ የተወሳሰበ ነው። ኢማም አል-ቁርጢቢም ይህንን ስለተረዱ ይመስላል ወደ ስድስት ግምታዊ መላምቶችን ያስቀመጡት። ቁርኣን እንዲህ ግልጽ ካለመሆኑ የበለጠ የሚገርመው ግን ከየትኛውም የጥንት መጽሐፍ በተለየ ስለ ግልጽነቱ መደስኮሩ ነው።

[1] ተፍሲር አል-ቁርጡቢይ ቅጽ 11 ገጽ 375

@Jacobite_apologetics27
513 viewsTinsae, 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:19:47
339 viewsTinsae, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:12:18
ጠያቂ:- ለምንድነው የመጽሐፍ ቅዱስ እደ-ክታባት ውስጥ ባገኘሃቸው የገልባጮች ስህተት ምክንያት የክርስትና መሰረታዊ ትምህርቶች ችግር ውስጥ ይገባሉ ብለህ የምታምነው?

ባርት ኸርማን:- መሰረታዊ የክርስትና ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ እደ-ክታባት ውስጥ ባሉ ልዩነቶች ምክንያት ችግር ውስጥ አይገቡም።

@Jacobite_apologetics27
387 viewsTinsae, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:12:09 ሙስሊም ወገኖች "ኢየሱስ አልተሰቀለም" የሚለውን አፈታሪክ ታሪካዊ መሰረት ለማስያዝ ከሚሞክሩበት መጽሐፍ አንዱ "ሁለተኛው የታላቁ ሴት ድርሰት"/Second treatise of the great Seth የሚለው መጽሐፍ ይጠቀሳል። "ዓለምን የፈጠረው እውነተኛው አምላክ አይደለም" እና "ክርስቶስ ስጋ የለበሰው ከሌላ ሰው ቀምቶ ነው" በሚሉ አስቂኝ አፈታሪኮች የተሞላው ይህ መጽሐፍ ግብጽ ውስጥ በ 1945 ከተገኙት የናግ ሃማዲ እደ-ክታባት አንዱ ሲሆን ከአርባ እስከ ሰባ የሚደርሱ ገጾች አሉት። በዚህ የኖስቲክ መጽሐፍ ውስጥ ማንነቱ ያልታወቀው ደራሲ (የሴት ስም ራሱ ከርዕሱ ውጪ አልተጠቀሰም) ኢየሱስ እንዳልተሰቀለና በእርሱ ቦታ የቀሬናው ስምዖን የተባለ ጎልማሳ እንደሞተ ይተርካል። ምንም እንኳን ይህ አስተምህሮ ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ግን አይደለም። ባሲሊደስ የተባለ የእስክንድርያ ኖስቲክ ይህ መጽሐፍ ከተጻፈበት ጊዜ (አብዛኞቹ የታሪክ ምሁራን የናግ ሃማዲ እደ-ክታባት በሶስተኛ ክፍለዘመን እንደተጻፉ ያምናሉ) በፊትም ይህንን ማስረጃ ቢስ ኑፋቄ ያስተምር ነበር።

ይህ መጽሐፍ ታዲያ የዘመኑን ኖስቲኮች እምነት ለማወቅ ካልሆነ ስለ ክርስቶስም ሆነ ስቅለቱ የሚጨምርልን አዲስ ነገር የለም። መጽሐፉ የተጻፈው በሶስተኛ ክፍለዘመን ከመሆኑ ባለፈ በእስክንድርያ መጻፉ የዐይን እማኞች ዘገባ ላይ የተመሰረተ የመሆኑን ዕድል ዜሮ ያደርጉታል።[1] የዚህ መጽሐፍ ከግብጽ ውጪ የትም አለመገኘቱ ደግሞ አካባቢያዊ (local) ጽሑፍ እንጂ ሰፊ ተቀባይነት ያልነበረው መሆኑን ማሳያ ነው።

[1] Bart D. Ehrman.(2003) Lost scriptures. Oxford University press.p.82.

@Jacobite_apologetics27
397 viewsTinsae, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:11:51
358 viewsTinsae, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 00:06:38 ቁርኣንን ስናነብ አንድ መሰረታዊ ትምህርት እናገኝበታለን ፤ እርሱም ያልተጠና ኩረጃ ውጤታማ እንደማይሆን ነው። በአስራ አንደኛው ሱራ (ሱራ ሁድ) ላይ የቁርኣን ደራሲ በከፊል ከዘፍጥረት የገለበጠውን የሉጥን ሕዝቦች ለማጥፋት ስለተላኩት መላእክትና ስለ ኢብራሂም መስተንግዶ እንዲህ ሲል ይተርካል።

«መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡ ሚስቱም የቆመች ስትኾን ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በያዕቁብ አበሰርናት።»
-11:69-71

ዘፍጥረት ላይ እንደምናነበው የሳራ ሳቅ በትልቅ ዕድሜዋ ልጅ ትወልጃለሽ በመባሏ በተሰማት ያለማመን ስሜት የመጣ ነው።(ዘፍጥረት 18:12) የቁርኣን ደራሲ ግን የክስተቶቹን ቅደም ተከተል ገልብጦ ሳራ ልጅ ስለመውለዷ ከመስማቷ በፊት እንደሳቀች ከመናገር አልፎ ለምን እንደሳቀችም ምንም ግልጽ ምክንያት አያስቀምጥም። ይህ ሁኔታ ሙስሊም የቁርኣን ተርጓሚዎችን በእጅጉ ግራ ያጋባና እርስ በርስ ያለያየ ነው። ኢማም አልጠበሪ ብቻ "መላእክቱ ምግብ መብላት ስላልቻሉ ሳቀች" እና "በሉጥ ሕዝቦች አለማወቅ ሳቀች" የሚሉ ምክንያቶችን ጨምሮ ሊሆን ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውን ወደ ስድስት ምክንያቶች ያስቀምጣል።(Jamai al bayan volume 12 p.473-475) ኢብን ዐባስ የሳቀችው የኢብራሂምን መፍራት አይታ ነው ሲል አስ-ሱዩቲ ደግሞ የሉጥ ሕዝቦች መጥፋት አስደስቷት ነው ይላል። ልጅ በማግኘቷ ተደስታ ነው ያሉም አልጠፉም።

ይህ ግራ መጋባት የመጣው የቁርኣን ደራሲ ታሪኩን በሚገባ ባለመረዳቱ ምክንያት ነው። የሳራ ሳቅ የመነጨው በዚህ ዕድሜሽ ትወልጃለሽ በመባሏ በተሰማት የግርምት ስሜት መሆኑን ያልተገነዘበው ሙሐመድ ሳራ የመውለዷን ብስራት ሳትሰማ በፊት እንደሳቀች ይነግረናል። ይህ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ሙፈሲሮቹም ግራ እንዲጋቡ አድርጓል። ቁርኣን የሰው ድርሰት ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ሙስሊሞች ንቁ!

@Jacobite_apologetics27
446 viewsTinsae, 21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ