Get Mystery Box with random crypto!

Gaius Ministry

የቴሌግራም ቻናል አርማ gaiusministry — Gaius Ministry G
የቴሌግራም ቻናል አርማ gaiusministry — Gaius Ministry
የሰርጥ አድራሻ: @gaiusministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

#Gaius Ministry #youth center #spreading the gospel of the lord Jesus Christ #christian living #Christian fellowship
Follow us in:-
YouTube https://bit.ly/2R3U
Instagram gaius_ministry
Website http://gaiusministry.org/
Facebook Gaius Ministry

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-03 07:23:07 ጌታ ከገጠመኜ ያስተማረኝን ላካፍላችሁ........

የምኖርበት ሰፈር ያው እንደማንኛችንም አካባቢ ከፍተኛ የውሃ ችግር አለ። እና ጭራሽ ሰሞኑን ወር አልፏታል ውሃ ከመጣች።( ውሃን ያያችሁ ....... ያው መልሳችሁን አውቀዋለሁ " አላየንም !" ነው።)

ታድያ አማራጭ ስላጣን 2 ባለ 20 ሊትር ጀሪካኖችን ገዝተን በየቀኑም ይሁን እልፍ እያልን እንደአጠቃቀማችን ውሃ ይዘን መግባት የሰርክ ተግባራችን ሆኗል እኔና ሚስቴ።

ታድያ መኖርያችን 4ኛ ፎቅ በመሆኑ የህንጻው ጥበቃ በሸክም ይረዳናል። በቃ ደግሞ ሸሪካችን ስለሆነ ገና ብቅ ስንል እኔንም ባለቤቴንም ጠጋ ብሎ " ውሃ አመጣችሁ እንዴ?" ይልና ሁለቱንም አፈራርቆ በፈገግታ በታጀበ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ያደርስልናል። የኛ ድርሻ አንዱን አድርሶ እስኪመጣ ሌላኛው ጋር መጠበቅ ነው። በቃ ይህ ከወር ያለፈ ግንኙነት ነው....... ወዳጅ ሆነናል.... ተግባብተናል.... አንዳንድ ነገር ልናግዘው እንሞክራለን..... ውሃ ሲያደርስ ደግሞ የኪስ ነገር ጣል እናረግለታለን። ተገቢ ብለን ምናስበውንም አንዳንዴም ያቅማችንን ከፍ ልናረግለት እንሞክራለን።

ታድያ ትናንት ወድያ ምሽት እኔ ነበርኩ ውሃ ይዤ የመጣሁት...... እና ጥበቃው ወዳጄ ዳርጌ (ስሙ ነው) እንደወትሮው ጠጋ አላለኝም። ባይኔ ብፈልገውም አጣሁት። ለካ ህንጻው ጥግ ነገር ላይ ብርድልብሱን ተከናንቦ ተኝቷል። አሳዘነኝ! ትንሽ ብርድም ካፍያም ነገር ነበር። ጠራሁት እና ውሃ ማምጣቴን ነግሬ እንዲያደርስልኝ ጠየኩት። ገና ዞር እንዳልኩ ምስኪን ዳርጌ " እሺ" ብሎ ምንም ሳያቅማማ አንዷን ጀሪካን ወደ ትካሻው ከፍ ነገር አድርጎ እንደ ወትሮው ለመሸከም ሲል አምልጦት ኖሯል። ብቻ የሆነ ነገር " ደፍ ፣ ዧ" ሲል ድንግጥ ብዬ ስዞር ክው ብሎ ለማንሳት ይንተፈተፋል። ቲቪ የጣለ ነው ሚመስለው........ ለማገዝ ጠጋ ብዬ ሳይ የሆኑ ቦታዎች ጀሪካኑ ጨርመት ብሏል። በስጨት እንደማለት ቃጣኝ.... በውስጤ " ቀስ አይልም እንዴ?! ምን እዚህ....." አይነት ተሰምቶኛል። ጀሪካኑን ልገዛ ስል ዋጋው አስገርሞን ከሚስቴ ጋር በስልክ የነበረን ንግግር እና ግርምት ትዝ አለኝ። ዳርጌ አበሳጨኝ!!! ብቻ ዋጥ ነገር አድርጌ አይዞህ ምናምን ብዬ አሸካከምኩት እና አንዷን እንዲያደርስ ልኬ ሌላውን ይዤ መጠበቅ ያዝኩ።

ከዛ ያው ጌታ ከክስተቶች ብዙ ያስተምረኛል እላችሁ የለ?!....... መዓት ሃሳብ ይዥጎደጎድ ያዘ!

ሲጀምር ፕላስቲክ ጀሪካን ነው...... ተሰባሪ አይደል?! ሲቀጥል ቢበላሽ እንኳ ያን ያህል እኔን የሚጎዳኝ አይደለ.... ደግሞ ዳርጌ ስንት ግዜ ነው ያገዘኝ! ፈገግ እያለ! አንዳንዴ ክፍያ ጭራሽ አልቀበልም እያለ! ቢከብደኝ አደል እንዴ የእርሱ እርዳታ ያስፈለገኝ?!

መልስ ብዬ ማሰላሰል ያዝኩ ...... ጌታን አሰብኩት!

ስንት ግዜ ነው ስከሰክስ የታገሰኝ!!!! ያውም ጀሪካን ያልሆነ! ገና ከመነሻው እንደማንም የሰው ልጅ በጨለማ ስልጣን የነበርኩትን በልጁ ደም አጥቦ ቀድሶ ልጁ ያረገኝ። እንደ እኔ ያለውን ታማኝ አድርጎ ቆጥሩ አገልጋዩ ያረገኝ። ከዛም በኃላ በብዙ መውጣት መውረድ ፣ ከፍታ ዝቅታ፣ መውደቅ መነሳት የታገሰኝ!!!!!!!!!!!!!!!

ከስንት ወጥመድ የታደገኝ!

እንደገና እድል እየሰጠ እዚህ ያደረሰኝ!!!!!!!!!

ደሞ እኮ እርሱ እንደኔ ጥበቃውን እንደፈለኩት አቅም አጥቶ አጋዥ አስፈልጎት አይደለም።

ፍቅሩ እንጂ!!!!! ምህረቱ እንጂ!!!!! ጸጋው እንጂ!!! እሺታው እንጂ!!!!!

ጭራሽ እርሱ እኮ እንደኔ የኪስ ሳንቲም ሳይሆን ህይወት ቀድሞ የሰጠኝ ነው:: በእርግጥ ኑሮዬም በእርሱ ነው።

ኦው ይኽ ሁሉ ያሰብኩት ዳርጌ ከ4ኛ ፋቅ እስኪወርድ ነው። ግን በእንባ ታጠብኩ!

ሁለተኛውን ጀሪካን ፈገግ ብዬ አሸከምኩት.......

እሺ እንግዲህ ወዳጆች ምን ትላላችሁ!!!!!!

በሉ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ልሰነዳዳ.....መልካም እሁድ!!!
211 views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:22:59
188 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 15:06:36 ወዳጆች ሆይ እንጠብቃችኃለን.......

መምጣታችሁ እርግጥ የሆነ በውስጥ መስመር ብታሳውቁን ዝግጅታችንን ለማመቻቸት ሰለሚያግዘን በውስጥ መስመር ብታገኙን መልካም ነው።
229 views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 15:06:20
225 views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 08:23:11 ስለሆነ ሰው እርግጠኛ ሆነህ ዘመንህን ሁሉ መመስከር አትችልም..... ቢቀየርስ?!

ስለሆነ ሁኔታ ሽንጥህን ገትረህ እድሜ ዘመንህን መናገር አትችልም ቢለወጥስ?!

ስለምንም ነገር ሁልግዜ ሁሉ ቦታ ደፍረህ እንዲህ ነው ብለህ መናገር አያስተማምንም!!!!!!!!!!!

ግን ስለ እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ይቻላል!!!!!!

አይለወጥ አይለዋወጥ!!!!!
አይቀየር አይቀያየር!!!!!!
ዙፋኑን ሚቀናቀነው የለ!!!!!!
ኃይሉ ይቀንስ ይሆንተብሎ አይሰጋ!!!!!!
ጸባዩ ይቀየር ይሆን ተብሎ አይታሰብ!!!!!!

ኧረ ያንተ ያለህ!!!!!!!!! ምንኛ መታደል ነው የእርሱ ባርያ መሆን!!!!!!!

እንኳንም የህን የምስራች ማብሰር ዋና ስራዬ ሆነ!!!!!!

በጭራሽ አላፍርበትም!!!!!!!!!!!!!!
337 views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 08:22:58
252 views05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 23:14:43 የመጨረሻ ማስታወቅያ!!!!

ምዝገባ ሰኞ ሰኔ 27 የመጨረሻው ቀን ነው።

ሐምሌ 4 ሰኞ በይፋ ይጀምራል።

ስለምን እየተነገረ ነው ካላችሁ ይኸው የከዚህ ቀደሙ ማስታወቅያ.....

ጋይዮስ ሚኒስትሪ ከምስረታው አንስቶ ሲያደርግ እንደነበረው በ2014ም የሁለት ወር የወጣቶች ስልጠና በላፍቶ ማዕከል አዘጋጅቷል። ስልጠናው:-

1. የቲያትር እና ስነጽሁፍ ፣ ኪ ቦርድ ፣ ጊታር ፣ ቮካል
ሲሆን እነዚህን ስልጠናዎች መውሰድ የሚፈልግ በሙሉ በየዕለቱ ከእነዚህ ስልጠናዎች በፊት በጋራ የሚሰጠውን በልዩ ልዩ ርእሶች ላይ መጽሀፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ስልጠና መውሰድ ግዴታ ይሆናል።

ይህ ሰኞ ፣ እሮብ እና አርብ ከ 8:00 እስከ 11:00

2. መሰረታዊ የመጽሀፍ ቅዱስ አጠናን እና አፈታት ከሌሎች ጠቃሚ ተያያዥ ርዕሶች

ይህ ማክሰኞ ፣ ሐሙስ ፣ ቅዳሜ ከ 8:00እስከ 11:00

ፍላጎት ያላችሁ በውስጥ መስመር ተመዝገቡ

ሁሉም ስልጠና ክፍያ የለውም።
325 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 23:14:41
242 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 17:38:33 ማር 5:36 " ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው።"

የምኲራብ አለቃው ኢያኢሮስ ብላቴናው ብትታመምበት መፍትሄ ፍለጋ ጌታ ኢየሱስ ጋር መጥቶ " እንድትድን፣ በህይወት እንድትኖር መጥተህ ዳሳት ፈውሳት " የሚል ተማጽኖ በማቅረብ ከጌታ ኢየሱስ ጋር ጉዞ ወደ ቤቱ ይጀምራል። በመንገድ ላይ 12 ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረ ሴት ፣ ባለ መድኃኒተኞች ጋር በሙሉ ሄዳ ፈውስ ሳይሆን የገንዘብ ማለቅ የገጠማትና የባሰባት ሴት ፣ ብነካው እፈወሳለው ብላለች እና ነክታው የደምዋ ምንጭ ቆመ፤ መዳንዋንም በሰውነቷ አወቀች። በዚህ ግዜ ጌታ ምንም እንኳ ደቀመዛምርቱ ይሕ ሁሉ ግፍያ እያለ ማን ነው የነካኝ ትላለህ ቢሉትም ለየት ያለ አንካክ ተነክቶ ነበር እና ኃይል ከውስጤ ወጣ አለ። እንግዲህ በዚህ መሃል ነው የኢያኢሮስ ቤተ ሰዎች ከቤት መጥተው " መምህሩን አታድክመው ፤ ብላቴናዋ ሞታለች " ብለው ያረዱት። በዚክ ግዜ ጌታ መነሻ ላይ ያስፈርኩት ጥቅስ ላይ ያለውን ለኢያኢሮስ ያለው።

የዛሬ ምሽት መልዕክቴ..........

ኢየሱስ የታመመ ብቻ ነው የሚፈውሰው ያለው ማን ነው? ቢሞትስ አያስነሳውም?

ትኩረት መርዶ ከሚነግረን ሰው እና ሁኔታ ሰብስበን እና ዘወር አድርገን በእምነት እርሱ ጋር ልጥፍ ማለት!

ከእርሱ ወደየት ይኬዳል?!!! አሁን ኢያኢሮስ ኡኡኡ እያለ ጌታን ትቶ ወደ ቤቱ ቢገሰግስ ምን ሊፈይድ?!
አልቅሶ ሊቀብር እንጂ!!!

ባክህ የነገሩ መፍትሄ ያለው ጉዳዩ ጋር ሳይሆን ኢየሱስ ጋር ነው!!!!!!!!

ጉዳዩ ጋር ሄደህ ከመራኮት እርሱ ጋር መጣበቅ ይሻላል!!! ባይሆን ምሪት ተቀብለህ አብረህ ከጌታ ጋር ትንቀሳቀሳለህ!!!!!!!!!!
399 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 17:38:26
246 views14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ