Get Mystery Box with random crypto!

#TRINITY_and_Salvation ከጥቂት ጊዜያት በፊት አንዳንድ ትምህርተ ስላሴን ከማይቀበሉ | የአዲስ ኪዳን ካህናት

#TRINITY_and_Salvation
ከጥቂት ጊዜያት በፊት አንዳንድ ትምህርተ ስላሴን ከማይቀበሉ የኑፋቄ አስተማሪዎች ጋር በአካል ተገናኝቼ ለማውራት እና ለመነጋገር ሞክሬ ነበር። እዚህ ግባ በማይባል አመክንዮ እና የመፅሀፍቅዱስ ጥቅሶችን እነሱ የሚፈልጉትን እንዲልላቸው በማስገደድ የተጠመዱ መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ። ስሁታኑ immature የሆኑትን ነፍሳት #በትጋት እያሳቱ በመሆናቸውም እጅግ አዝኛለሁ። ዳሩ ግን ሙሉ መፅሐፍ ቅዱስን አንብቦ ትምህርተ ስላሴን መካድ በሰይጣን Deceptive ሀሳብ ከመነዳት ውጭ ምንም ሊሆን እንደማይችል ግልጥ ነው። ትንሽ ነገር እንመልከት እስኪ

በሚያስደንቅ መንገድ #በዘመነ_ብሉይ የነበሩት ሶስቱ ታላላቅ አባቶችን ተመልክተን የስላሴን ምስጢር ህብረ አምሳል ገና በዘፍጥረት መፅሀፍ እናገኛለን።

#አብርሃም : የሚወደውን አንድ ልጁን ለመሰዋት ያልሰሰተ አብርሃም : "የሚወደውን አንድያ ልጁን ሳይሰስት(ለገዛ ልጁ ያልራራለት እንዲል) የሰጠንን" እግዚአብሔር #አብ'ን አያሳየንም??

#ይስሐቅስ ብትሉ : አባቱ ሊሰዋው በወደደ ጊዜ በሙሉ ፈቃደኝነት መታዘዙ " ይኸውም እስከመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ " የተባለውን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በምሳሌ ገለጠው።

#ያዕቆብስ በስጋ እስራኤላውያን ለሆኑት ነገዶች አባት የሆኑትን አስራሁለቱን በመውለዱ #በነፍስ_እስራኤላውያን( ሮሜ 9:6 , ገላ 3:7&29 , ገላ 4) ለሆኑት ክርስቲያኖች ሁሉ አባት የሆኑትን 12ቱን ሀዋሪያት የወለደውን መንፈስ ቅዱስን በህብረ አምሳልነት አያሳይምን??

ይሄ ምስጢር ድንቅ ነው : አብርሃም ልጁን ለመሰዋት እንዲሄድ እግዚአብሔር 3 ቀን የሚያስኬድ መንገድ መምረጡ አጋጣሚ አይደለም። ይልቁንም 3 ቀን ሙሉ በአብርሃም ህሊና ይስሃቅ እንደሞተ መቁጠሩ(Amazing passion) : ነገር ግን እግዚአብሔር ተው ሲለው እንደሞተ የቆጠረውን ልጁን ዳግመኛ ማግኘቱ : 3 ቀን በመቃብር የነበር : በትንሳኤ ሀይል ደግሞ የተነሳውን ጌታችንን እንዲያሳይ እንጂ...

በአዲስ ኪዳን ደግሞ እንመልከት (የድህነታችን ምሉዕነት በሚስጥረ ስላሴ መገለጡን)

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ጌታችን 3 ድንቅ ምሳሌዎችን አስተማረ #የጠፋው_በግ , #የጠፋው_ድሪም, #የጠፋው_ልጅ ;እባካችሁ አንብቡት

በመጀመሪያው ምሳሌ በዘጠናዘጠኙ ሳይረካ አንዲቷን በግ ለመፈለግ የሚጠመደው ሰው : በጎቹ በጉስቁልና ወዳሉበት ስፍራ መቶ ሞቶ ያዳነን : በግልም የፈለገን የጌታችን ምሳሌ ነው።( Jesus loves you personally ; not just peoples as general )
ከዛ ሲያገኛት በደስታ በትከሻው ላይ አድርጎ ያመጣታል።ሀሌሉያ

በሁለተኛው ምሳሌ አንዲት ሴት የጠፋውን ድሪም በመብራት ትፈልገዋለች። #ድሪም አንድ ሰራተኛ በቀን የሚከፈለው የብር ሳንቲም ነው። ያ ሳንቲም በትቢያ ውስጥ ሲወድቅ አንፀባራቂነቱ እና ውበቱ ይጠፋሉ። የሚደንቀው ሳንቲሙ ላይ ያለውንም #ምስል ለማየት ያስቸግራል። በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረውም ሰው እንዲሁ ነው። የእግዚአብሔር መልክ አይታይበትም። ግን #በመብራት ፈለገችው። ይሄ መብራት #የመንፈስ_ቅዱስ ምሳሌ ነው። ይሄ ሳንቲም እንዲገኝ ቀን ሙሉ ስራ ተሰርቷል : ዋጋ ተከፍሏል። ( የክርስቶስ የመስቀል መከራ የአምላክ ሰው መሆን ሁሉ ስለ እኛ የተከፈለ ዋጋ መሆኑን ያስታውሷል። ) ያን ውበቱን : ያንን አንፀባራቂነቱን : ያንን እግዚአብሔርን መምሰል የሚመልሰው መንፈስ ቅዱስ ነው።

በሶስተኛው ምሳሌ : ሀላችንም በምናውቀው በጠፋው ልጅ ታሪክም ገና ልጁ ከሩቅ ሲመጣ ሲያይ በደስታ ሮጦ ያቀፈው የአብ አባት ምሳሌ ነው።
የተሻለው ልብስ(የእግዚአብሔርን ፅድቅ 2ቆሮ5:21) የወርቁ ቀለበት
የታደሰ ልዩ ህብረትን( 1ዮሐ 1:3) : ጫማው በወንጌል አደራ መመላለስን ( ኤፌ 6:15) : የሰባው ጥጃ በክርስቶስ ያገኘናቸውን በረከቶች ያመለክታል።( ኤፌ 1:3)

“በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና #አባት ይባረክ።”
— ኤፌሶን 1፥3

እነዚህ ሶስቱ ምሳሌዎች የጠፋውን በመፈለግ እና በማዳን ስራ ውስጥ በሶስትነት ያለ እግዚአብሔር የሰራውን ስራ ያሳያሉ። #Trinity of Persons, in the unity of the divine essence. This unity of
essence, or nature, is asserted and secured, by their being said to be #one.

እወዳችኋለሁ። ተባረኩ

@untothelamb
@untothelamb
@untothelamb