Get Mystery Box with random crypto!

ፀሀይ ስለ አስደናቂዋ ፀሀይ ትንሽ ነገር ልበላችሁ እስኪ ስለ Universe አስገራሚ እውነቶች | የአዲስ ኪዳን ካህናት

ፀሀይ
ስለ አስደናቂዋ ፀሀይ ትንሽ ነገር ልበላችሁ እስኪ

ስለ Universe አስገራሚ እውነቶች ማወቅ : የህዋ ዘመናዊ ሳይንስን ማጥናት የአምላኬን አስደናቂ ጥበብ የማይመረመር ችሎታውንም እየተረዳሁ ሀሴት እንዳደርግ ስለሚያደርገኝ በመጠኑ interested ነኝ ሳይንሱን ለመመልከት።

ከፀሀይ መጠን ብንጀምር : መጠነ ቁሷ እጅግ ታላቅ ነው። #ፕላኔቶች ሁሉ ተደምረው የፀሀይን 0.1 ፐርሰንት ብቻ ይደርሳሉ። ከምንኖርባት መሬት ጋር እንኳን ብናወዳድራት የመሬትን 300,000 ዕጥፍ ይሆናል። ምን ያህል ግዝፈት እንደሆነ መሳል እንኳ ከባድ ነው።

ተፈጥሮዋ እንዲሁም ዑደቷ ፍፁም ውስብስብ እና ሰፊ በመሆኑ ልዝለለውና ስለ ማያልቀው የሀይል ምንጯ ትንሽ ልዳስስ

ፀሀይ በአንድ ቅፅበት(with in one second) 390000000000000000000000000(3.9×10^26) ጁል ጉልበት ታመነጫለች። በዚሁ በ 1 second 600 ሚሊዮን ቶን ሃይድሮጅንን ወደ ሂሊየም የምትቀይር ሲሆን የዚህ ጉልበት መጠን ሲሰላ #100_ሚሊዮን_ኒውክለር_ቦምብ
ጉልበት ያህል በ second ታመነጫለች ።

በጣም የሚደንቀው ለ6 ሰከንድ የምታወጣው ጉልበት ቢሰበሰብ የምድርን #ውቅያኖስ ውሃ ሁሉ #ማትነን ይችላል። የ3 ደቂቃ ጉልበቷ ደግሞ ቢሰበሰብ የመሬት የላይኛውን ንጣፍ (crust) ማቅለጥ ይችላል።

በአንስታይን "special theory of relativity " ባለው ህጉ መሰረት E=mc^2 መሰረት ቁስ አካሏ ወደ ጉልበት ሲቀየር ነው ወይ በሚል ጥናታቸውን የጀመሩ ሳይንቲስቶች ፀሀይ hydrogen fusion በሚባለው አካሄድ ፀሀይ ሃይድሮጅንን እያቀጣጠለች ወደ ሂሊየም በምትቀይርበት ጊዜ ይሄንን ታላቅ ሀይል ታመነጫለች በማለት አስቀምጠዋል።

ሌላም ብዙ ይላሉ : ነገር ግን መንገዱ ምንም ሆነ ምንም እኔን የሚያስደንቀኝ እግዚአብሔር ይህቺን ታላቅ ፍጥረት በቅፅበት መፍጠሩ ቅዱሱ መፅሀፍም ለዚህ ታላቅ ክስተት ከጥቂት መስመር በላይ አለማባከኑ የእግዚአብሔር የሀይልና የጥበቡን ታላቅነት ማሳየቱ ነው።

ዘፍጥረት 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤
¹⁵ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፤ እንዲሁም ሆነ።
¹⁶ እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።

ከዚህ ክስተት በላይ ድህነታችን የተፈፀመበት የወንጌሉ ሂደት የእግዚአብሔር ታላቅ ሀይል እንደተገለጠበት ቅዱሱ መፅሀፍ ይነግረናል።

ኤፌሶን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸-¹⁹ ይህም #የልባችሁ_ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ #የኃይሉ_ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤
²⁰-²¹ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ #የብርታቱ_ጉልበት_ይታያል፤

ሌላው #ፀሀይ አሁን ከምድር ያላት ከፍታ 93 million miles (149,598,000km) ነው ።

እና #አሁን ካላት ከፍታ ትንሽ #ከፍ ወይም ትንሽ #ዝቅ ብትል ፍጥረት sustain ማድረግ አይችልም። ይጠፋልም።

#ግና ከፍም ሳትል ዝቅም ሳትል #ቀጥ አድርጎ የያዛት ጌታዬ ኢየሱስ ነው ። በስልጣኑ ቃል ሁሉን ደግፎታል ክብር ለስሙ ይሁን።

“እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።”
— ቆላስይስ 1፥17

“እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን #በስልጣኑ_ቃል_እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”
— ዕብራውያን 1፥3

ይሄን ውጥንቅጡ የወጣውን የምድሬን ሰለምና የቤተክርስቲያን ከከፍታዋ መዝቀጥ ተመልክ በሁሉን ቻይ ክንዱ ደግፎ ቀጥ እንዲያደርገው በስሙ ፀሎቴ ነው።

ልጥፉን share እወዳችኋለሁ ተባረኩ

@untothelamb
@untothelamb
@untothelamb