Get Mystery Box with random crypto!

የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ክፍል ሦስት ቅዱ | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ክፍል ሦስት

ቅዱሳት መጻሕፍት

5.እግዚአብሔር ቃሉን በሙሉ ከብረዛ ለመጠበቅ ይሻልን? (ፍላጎት / ኒያ)

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን / ቁርአንም አዎን ነው ።

መ/ዳዊት 12፡6-7 በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

ኢሳ 14 ፡24 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።
በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች የሚመልሳትስ ማን ነው?

ማቴ 24፡35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

-----------------------------------

አል-ሒጅር 15፡9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

አልሷፍፋት 37፡3 & 7 ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ።….አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት።

6.እግዚአብሔር ቃሉን ከመለወጥና ከብረዛ መጠበቅ ይችላልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን / ቁርአንም አዎን ነው ።

ኢሳ 46፡9-10 እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።….በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ።

ማርቆስ 12፡24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?

ሉቃስ 21፡23 በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤
ዮሐ 10፡35 መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥

-------------------------------------

አል-አንዓም 6፡115 የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን ተፈጸመች፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡

ዩኑስ 10፡64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡

አል-ጂን 72፡26-28 (እርሱ) ሩቁን ሚስጢር ዐዋቂ ነው፣ በሚስጢሩ ላይ አንድንም አያሳውቅም። ….እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን፣ የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)።



join


በጌታ የሆናችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ መልእክት ለእናንተ ምናልባት ቀላል ልመስላችሁ ይችላል ።ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ወንድም ከባድ መልእክት አለው ። ስለዚህ share በማድረግ እንዲትተባበሩ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ !!

ለእናንተ በአንድ ደቅቃ ለተወሰኑ ሰዎች share ማድረግ ቀላል ነገር ነው ።ብሆንም የሚያመጣው ውጤት ከእኔ ጋር ለመንግሥቱ አግልግሎት መቆም መሆኑን እውቁ ውጤቱ ደግሞ የጽድቅ አክልል ነው ። ስለዚህ አስባችሁ ተባበሩልኝ !!

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል አራት

ይቀጥላል .........