Get Mystery Box with random crypto!

የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ክፍል ሁለት ቅዱ | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ክፍል ሁለት

ቅዱሳት መጻሕፍት

3.እግዚአብሔር ቃሉን በተለይም በአይሁድ አማካይነት ለሰዎች አስተላልፏልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን /ቁርአንም አዎን ነው ።

ሮሜ 3፡1-2 እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው?

ሮሜ 9፡4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፡፡

------------------------------

አል-ዐንከቡት 29፡27 ለርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፤ በዘሩም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፍን አደረግን፤ ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው፤(2) እሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው።

አል-ጃሢያህ 45፡16 ለእስራኤል ልጆችም መጽሐፍንና ሕግን፣ ነቢይነትንም በእርግጥ ሰጠናቸው፤ ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው በአለማት ላይም አበለጥናቸው።

4.እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚገኙት ነቢያት ተዓምራትን እንዲያደርጉ ኃይልን በመስጠት ከእርሱ የተላኩ ስለመሆናቸው ማረጋገጫን ሰጥቷልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን /ቁርአን አዎን ነው ።

ዘጸአት 10፡2 ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደ ፈርዖን ግባ አለው።

ዮሐ 14፡11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ

ዕብ 2፡4 እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።

----------------------------

አል-በቀራህ 2፡92 ሙሳም በታምራቶች በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከዚያም ከበኋላው እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) ያዛችሁ፡
አሊ-ዒምራን 3፡49 ወደ እሥራኤልም ልጆች መልክተኛ የደርገዋል፤ (ይላልም) ፡-እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር መጣኋችሁ። እኔ ለናንተ ከጭቃ አንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ፤ በርሱም እተነፍስበታለሁ፤ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይሆናል። በአላህም ፈቃድ ዕዉር ሆኖ የተወለደን፥ ለምጸኛንም፥ አድናለሁ፤ ሙታንንም አስነሳለሁ። የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ዉስጥ በእርግጥ ታምር አለበት።

አሊ-ዒምራን 3፡183 እነዚያ ለማንኛዉም መልክተኛ እሳት የምትበላዉ የሆነን ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ ላናምን አላህ ወደኛ አዟል ያሉ ናቸዉ፤ መልክተኞች ከኔ በፊት በታምራትና በዚያም ባላችሁት (ቁርባን) በእርግጥ መጥተዉላችኋል፣ እዉነተኞች ከሆናችሁ ታድያ ለምን ገደላችኋቸዉ? በላቸዉ።



join


በጌታ የሆናችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ መልእክት ለእናንተ ምናልባት ቀላል ልመስላችሁ ይችላል ።ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ወንድም ከባድ መልእክት አለው ። ስለዚህ share በማድረግ እንዲትተባበሩ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ !!

ለእናንተ በአንድ ደቅቃ ለተወሰኑ ሰዎች share ማድረግ ቀላል ነገር ነው ።ብሆንም የሚያመጣው ውጤት ከእኔ ጋር ለመንግሥቱ አግልግሎት መቆም መሆኑን እውቁ ውጤቱ ደግሞ የጽድቅ አክልል ነው ። ስለዚህ አስባችሁ ተባበሩልኝ !!

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል ሦስት

ይቀጥላል .........