Get Mystery Box with random crypto!

እያለቀስክም ቢሆን የበሩ መከፈት ቢዘገይ እንኳን አትዘን፡፡ ዋናው ሳትሰለች በሩ ላይ ቆመህ መገኘት | ISLAM IS UNIVERSITY

እያለቀስክም ቢሆን የበሩ መከፈት ቢዘገይ እንኳን አትዘን፡፡ ዋናው ሳትሰለች በሩ ላይ ቆመህ መገኘትህ ነው፡፡ በሀይልና በተደጋጋሚ የተንኳኳ በር መከፈቱ ግድ ነው፡፡ እስልምናህን የምትወድ ከሆነ አላህ ይከፍትልሀልና ተስፋ አትቁረጥ፡፡ አላህ ይሰጥሀል፡፡ ውስጥህ ያለውንም ተስፋ ያድሳል፡፡ አል-ፈታሕ ብለህ በስሙ ጥራው፡፡ በርግጠኝነት ይከፍትልሀል፡፡


ነብዩ ሰዐወ በለሊት ተነስቶ ሚስቱንም ቀስቅሶ ሁለት ረከአ ለሰገዱት አላህ ይዘንላቸዉ ብለዋል፡፡
እናም ተኝቶ ድምፃችን ይሰማ እያሉ ከማንኮራፋት ተነስቶ ሚስትህ ጋር መስገድ አብራችሁ ዱአ ማድረግ ለዚህ ቅጥ ላጣ ዘመን መፍትሄ ነዉ፡፡

ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም ይሄን ማወቅ አለብን አላህ የትንኝ ክንፍ ለኔ ቦታ የላትም ብሎ እኛ ደስተኛ እንሆናለን ብለን ራሳችንን አናሳምን

አል ኢማም አር ራዚ ቆንጆ ልብስ መልበስ ይወዱ ነበር፡፡ አንድ ቀን ከመስጅድ ወጭ እያሉ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ጋር ተገናኙ፡፡ ሰውዬው የተበጣጠሰ ልብስ ነበር የለበሰው፡፡ ለኢማም አርራዚ እንዲህ አላቸው የናንተ ነብይ ይህች ዓለም ለአማኞች እስር ቤት ለከሐዲዎች ጀነት ናት፡፡› ይላል፡፡ ይህን የመሰለ ፀጋ ውስጥ እያለህ ከየትኛው እስር ቤት ውስጥ ነህ? እኔስ በየትኛው ጀነት ውስጥ ነኝ? አላቸው፡፡ ኢማም እርራዚም እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ በጀነት ውስጥ ካለው ድሎትና ፀጋ አንፃር እስር ቤት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በጀሃነም ውስጥ ለከሐዲያን ካዘጋጀው ቅጣት ደግሞ አንተ አሁን ያለህበት የችግር ኑሮ ጀነት ነው፡፡ አለው፡፡ ሰውዬውም ጥቂት ካስተነተነ በኋላ በርግጥም የናንተ መልእከተኛ የተናገረው እውነት ነው፡፡› አለና ሰለመ፡፡

ይህች ዓለም እስር ቤት መሆኗ፣ አላህ (ሱወ) ጀነትን ለኛ ማዘጋጀቱ፣ አኺራ በላጭና ዘላለማዊ መሆኗ ... ይህ ሁሉ አላህ (ሱ.ወ) እኛን ሊያስደስተን የፈለገ መሆኑ ያመላክተናል፡፡ _ ስለሆነም ጀነት ሊያስገባን ብሎ ይከታተለናል፣ ይጠብቀናል፣ በችግሮችም ይፈትነናል፡፡

በተጨማሪም ሲህርም ባይሆን ማንኛዉም ህመም ሲያጋጥመን ሀኪም ቤት ልሂድ ከማለት መጀመሪያ አላህ እንዲያሽረን እንማፀን

ዑሥማን ኢብን ጦለሐ የሚባል ሰሐባ ነብዩ (ሰዐወ) ዘንድ መጣና የአላህ መልእተኛ ሆይ!!! ሰውነቴ ውስጥ ህመም ይሰማኛል፡፡ አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰዐወ)  በአላህ (ሱ.ወ) መካከል ያለው ግንኙነት የጠበቀ እንዲሆን ፈለጉ፡፡ እናም በሚያምህ ቦታ ላይ እጅህን አኑርና ሶስት ጊዜ ቢስሚላህ በል፡፡ ከዚያም ሰባት
ጊዜ አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸር ማ አጂዱ ወኡሓዚሩ፡፡" በል አሉት፡፡ ሰሐባውም እሳቸው እንዳሉኝ አደረኩኝ፡፡ ህመሙም ለቀቀኝ፡፡ በአላህ እምላለሁ ከዚያ ቀን ጀምሮ ለቤተሰቤና ለማውቀው ሰው ሁሉ ከማስተማር ወደኋላ አላልኩም፡፡› ብሏል፡፡


ታማሚም አስታማሚም አላህ ፅናቱን ጥንካሬዉን ይስጠን...እኛም ለዲናችን ጠቃሚ ለሰዉ የምንተርፍ ያድርገን
ለሰዉ ክፋት መጥፎ የምናስብ ሰዎች እባካችሁ ቶብቱ በሰዉ ደስታ ለምን እንደኛ ይቸገር እንላለን??
ክፉዉን ማዳመጥ ማየት የክፋት መጀመሪያ ነዉ
ክፋት በሰዉ ባህሪ ዉስጥ አብሮ የተፈጠረ ሳይሆን ክፋትን ማስወገድ ባለመቻሉና ዉጫዊ ተፅእኖዉን መቋቋም ስላቃተዉ የመጣበት ነገር ነዉ፡፡
ህይወት ወጪዉን የማትሸፍን ንግድ ነችና በእሷ ስኬትን በሀራም በጠንቋይ በሳሂር እገዛ እጨብጣለሁ ብለህ አትሰብ እናም በሰዉ ስቃይ ሀዘን ለቅሶ መደሰት ምን የሚሉት ህሊና ነዉ ?? አላሁ የስቱርና አላህ ከመጥፎ ባህሪ አመል ይጠብቀን


አላህ ሆይ ከደጋሚዎች ከሳሂሮች ተንኮል ጠብቀን...ምቀኛን ቀናተኛን ከጎናችን አርቅልን..ስቀዉ ከሚጎዱ የቅርብ ሰዎች ጠብቀን ያረብ...
ሲህር የተየደረገብን የታመምን ወይ ሲህር ተደርጎብን ሳናቅ ብዙ አመታት ፈጅቶ ከረፈደ ያወቅን አልሀምዱሊላህ ከረፈደም ማወቃቸዉን ...እንደ አጋጣሚ ያለወቅን ካለ አላህ አሳዉቀን ያረብ
ጠንቋይ ቤት ለሚሄዱትም ሂድያ ስጣቸዉ...

  ኢላሂ  ለዲነል ኢስላም  የምንጠቅም ባንጠቅም እንኳኝ በኛ እንዳይሰደብ የምንሆን ጀሊሉ ያድረገን
አንዳንዴ በማህበራዊ ሚዲያ ሙስሊሞች አለቅጥ ወንጀል ፈሳድ ላይ ተጥለቅልቀዉ የሌላ ሀይማኖት ወይም አንዳንድ ኢስላም ሲደፈር የሚቆጫቸዉ እህት ወንድሞች ሙስሊም አይደለሽ እንዴ ብለዉ ሰመከሩ
የማምለጫ ዘዴ አለች...እኔ ሙስሊም ነኝ ችግር ካለብኝ እኔን እንጂ እስልምናየን አትናገሩ ብለዉ ኮስተር ሲሉ ይታያሉ ይገርመኛል እነሱ ኢስላምን እያሰደቡ እስላምን አትሳደቡ እያሉ ቀጭን ኢስላምን አትንኩብኝ እያሉ የዉሸት ተስፋ ይዘራሉ...ተስፋ ጥሩ ቁርስ ቢሆንም መጥፎ እራት መሆኑን አንዘንጋ 
እናም በሚዲያ ላይ ሙስሊም ሁነን ጅልባብም ጀለብያም ለበስንም አለበስንም በኛ ኢስላም ሊሰደብ ሊመዘን አይገባም እኛ በኢስላም ሀይማኖት ማዕቀፍ ዉስጥ ነን አማኝ ነን ካልን ሙስሊም ተብለናል ...አማኝ ሙስሊም ባንሆን እንኳ ህሊናችን የሚሰራ ሰዉ እንሁን... አረ ሰዉ ሰዉ እንሁን እባካችሁ...ኢስላም በኔም በአንተም በእኛም በእናንተም እየተሰደበ እየተዋረደ ነዉ...አላህ ዲነል ኢስላምን እኔ ነኝ የምጠብቀዉ ስላለ ነዉ እንጂ በእኛ ስራ ቢሆን አፍርሰን ትቢያ አመድ አርገነዉ ነበር
ኢንሻ አላህ እያሉ ከመሾለክ ዝም ብሎ በምሉላስ አሏሁ አክበር እያሉ ሙስሊምን ከመጉዳት ያለችንን ትንሽየ ኢማን አላህ ያድስልን፡፡አላህ ጠንካራ የማይበገር ኢማን ይስጠን

#ዉድ የተከበራችሁ  አንባባዎች በ➊➎ part ስለሲህር ድግምት አይነጥላ ..ስለትዳር ስለስንፈተ ወሲብ በሁሉም ባሉት ቸግሮች ትኩረት አድርጌ አቅሪቢያሁ
የሰዉ ልጅ ነኝ እሳሳታለሁ ከኔ በላይ እዉቀት ያላችሁ እዚህ ቦታ ተሳስተሀል በሉኝ  edit ማድረግ እችላለሁ edit አሁኑ ላድርግ ከወር ቡሀላ edit ማድረግ ስለማይቻል ...ብዙ ሰዉ እያነበበዉ ሼር እያደረገዉ ስለሆነ ...ግን የተዘጋጀዉ ከመፅሀፍ እና ከሀዲስ ከሚያቁ ጠይቄ ስለሆነ እስከ አሁን በአስተያየት መስጫ አስተካክል የተባልኩት የለኝም፡፡ በአስተያየት ስሰጡ ሳነባቸዉ  በሲህር ተለክፈዉ የነበሩ እና በይፋ  ያደረገባቸዉ ሰዉ እየነገረን ነዉ ያሉኝ አሉ  ፡፡
ወደ 5 የሚሆኑ አስተያየቶች እኔን ካላገባሽ መቼም አታገቢ ብለዉ ከወንድየዉ ተነግሯቸዉ  እንዳላገቡ በተጨማሪ  አንዷ አግብታ ኒካሁ ታስሮ ሳይቆዩ እንደተፋታች የነገረችኝ አለች ...ሌሎቹ ይሄን ፁሁፍ ሲያነቡ ራሳቸዉን ፈትሸዉ ሩቃ ሊጀምሩ እንደሆነ አሳዉቀዉኛል...እናም በተለይ በትዳር ላይ የተተበተበ ጉድ ከባድ ነዉ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ

ለ15 ቀን በ15 ክፍል የቀረበዉን ፁሁፍ ሀምሌ 1 ጀምረን ሀምሌ 15 2015 ጨርሰናል ፡፡ባለመሰልቸት ባለመታከት አንብባችሁ ስለጨረሳችሁ ጀዛችሁን አላህ ይክፈላችሁ ለምን እኔም እናንተ ባነበባችሁበት ራሳችሁን በፈተሻችሁበት አጅር ስለማገኝ እናንተም ባነበበባችሁት እኔም ባዘጋጀሁት ተጠቃሚ ያድርገን፡፡

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ
  #ተ.......... #ፈ.......... #ፀ........... #መ

አንብባችሁ ምን ተረዳችሁ?
ምን አስተያየት አላችሁ?
እዚህ ላይ ይፃፉ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ከፁሀፉ ያልገባችሁ ያልተዋጠላችሁ ካለ