Get Mystery Box with random crypto!

ፑቲን የሰላሐዲን አል አዩቢ አፀደ ገላ ያረፈበት የመቃብር ሥፍራ ላይ ዓይኑን ተክሎ በትኩረት ይመለ | ISLAM IS UNIVERSITY

ፑቲን የሰላሐዲን አል አዩቢ አፀደ ገላ ያረፈበት የመቃብር ሥፍራ ላይ ዓይኑን ተክሎ በትኩረት ይመለከተው ይዟል። “ተነስና ግጠመን! ተመልሰን መጥተናል” የሚል ይመስል፡፡

ይህ ክስተት ታሪክን የኋሊት መለስ ብዬ እንድንቃኝ አደረገኝ።

★ የፈረንሣይ ወታደሮች በአንደኛው የዓለም ጦርነት ሻምን ተቆጣጥረው ወደከተማዋ በዘለቁ ጊዜ ጄኔራል ጉሩፎራ የሰላሐዲን አል አዩቢን ቀብር በእግሩ ረገጠና “ሰላሐዲን ሆይ! ከሞትክበት ተነስ እነሆ ዛሬ ተመልሰን መጥተናል በበይተል መቅዲስ ስር መንፈላሰስ ይዘናል” በማለት ፎከረ፡፡

★ የመስቀል ጦረኞች አንደሉስ ገብተው ሙስሊሞችን ካረዱ በኋላ የመስቀላዊያኑ መሪ አልፎንሶ የሐጂብ አል-መንሱር መቃብር ላይ ድንኳን ተክሎ የወርቅ አልጋ ላይ ተደገፈ። ከሚስቱ ጋር ለሳምንታት ያህል ተኛበት። እንዲህም አለ "ዛሬ የሙስሊሞችን ሐገር ተቆጣጠርኩ። መሻኢኾቻቸውን ስገድል ከፊቴ የቆመ ማንም አልነበረም። እነሆ በትልቁ ጦር መሪያቸው ቀብር ላይ ተኝቻለሁ" አለ።
እኛ ነን ታሪካችንን የዘነጋነው እነርሱ ፈፅሞ አልረሱትም።

★ የግሪክ ወታደሮች ቡርሳ ከተማን ሲቆጣጠሩ የጦር አዛዣቸው ሶፍሎክስ የኦቶማን ኢምፓየር መስራች ወደሆነው ዑስማን አልጋዚ መቃብር አመራ። ቀብሩን እየረገጠ ጮኸ “የትልቁ ጥምጣሙ ባለቤት ሆይ ተነስ! አንተ ዑስማን ሆይ ንቃ! የልጅ ልጆችህን ሁኔታ ተመልከት! የመሰረትከውን ኢስላማዊ ኸላፋ አፈራርሰነዋል። ሀገሩን በታትነነዋል። አቅም ካለህ ንቃና ተፋለመን" አለ።

በአላህ እምላለሁ የእነዚህ መቃብር ባለቤቶች ተነስተው ቢተነፍሱ አንዳቸውም በሕይወት ባልተረፉ።


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group