Get Mystery Box with random crypto!

ከእነሱ አንዳንድ የምሰማዉም አለ....እስኪ በመጀመሪያ የራሳችንን እንወቅ ሙስሊም መስለዉ የሚሸዉዱ | ISLAM IS UNIVERSITY

ከእነሱ አንዳንድ የምሰማዉም አለ....እስኪ በመጀመሪያ የራሳችንን እንወቅ ሙስሊም መስለዉ የሚሸዉዱት  ጥንቃቄ እናድርግ የሌላዉ ይደርሳል...ብቻ በፀበል
ይለቀናል ባላችሁ ሂዳችሁ የብስ ህመም ጨምራችሁ እንዳትመጡ ....
እነሸህ ተብየ ጫት ቅመዉ ወይ በዛር የሚያስለቅቁ ይሄ በቀላል ቋንቋ 90% እርግጠኛ ሁኑ ለጅን ይገብራሉ ትልቁ ጉልበተኛዉ ጂን ለትንሹ ቀላል ነዉ ...ሲያጎራ ሲጮሁ ሰምታችሁ ከሆነ በጣም ለአቅል ይከብዳል ሲለፈልፉ በእነሱ አድርጎ ይወጣል፡፡
አንዳንዴ ዛር ያለበት እያጨበጨበ እየጨፈረ ሲያስለቅቅ ያየሁት አሉ ጅኑ አጨብጭብ ጨፍር ብሎት ወላሂ በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡ ግን ይሄ ለጅን ግብር ነዉ ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም ልጅን ይይዛል፡፡
የሀሉም መፍትሄ ቁርአን ብቻ


    አይንናስ(ቡዳ) ..ሲህር..ጂን ብዙዎቻችን ላይ ያለ ይመስለኛል ለምን ብዙሀን ሙስሊሞች ከዲናችን  የተዘናጋን ስለሆነ ራሳችንን ቆም ብለን ብናይ  ጥሩ ነው.....ብዙዎቻችን
የጠዋት ማታ ዚክር ማድረግ አቁመናል
ቁርአን ስልክ ከመጣ ቡሀላ የምንቀራ በጣት የምንቆጠር ነን ሁሉም በስልኩ ቁርአን አዝካር አለ ያንን ለመቅራት ነይቶ ስልኩን ሲነካካ ወደ ማህበራዊ ሚዲያላይ ነዉ የሚወስደን፡፡ ግን አስተዉለናል?? በፊት ስልክ ሳይመጣ እኮ ለቁርአን ያለን ፍቅር ዚክር ለማድረግ ያለንን ጉጉት የተለየ ነበር ግን አሁን ማን ነዉ ቁርአንን አክብሮ ገልጦ የሚቀራዉ??የሚሻለዉ በስልክ ቁርአን መቅራት ብናቆም የተሻለ ነዉ እናም
የኛ ከቁርአን መዘናጋት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳለፍ ከዲን የመዘናጋት ስለሆነ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ
በማህበራዊ ሚዲያ በTG..Whatsap..facebok..instgram ወዘተ የምናደርገዉ profile pictur ፎቶ ለአይን ናስ(ቡዳ) መበላት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምን ጀሊሉ ሲፈጥር ማስጠሌ ብሎ የፈጠረዉ የለም ግን የሰዉ አይን የፈለገዉን ቆንጆ የፈለገዉን ማስጠሌ አድርጎ ይስላል፡፡ profile ስታደርጉ እራሱን ወይ እራሷን እንደ ማስጠሌ የምታይ ዉይ ሲያምር ወይም ዉይ ስታምር ሊሉ ይችላሉ እናም profile ከማድረግ እንጠንቀቅ

በtiktok ላይ video የምፓስቱም የሰዉ አይን ሰለባ ስለምትሆኑ መጠንቀቁ አይጎዳም...እስኪ እኔ ብዙም ግንዛቤዉ የለኝም በtiktok የሚታወቁ ሰዎች ትዳር አላቸዉ የላቸዉም? ካላገቡ መቼም የሚታዩት ቆንጆ ናቸዉ እንዴት አላገቡም?
መጀመሪያ በሚዲያን የቀረበ ራሱን ጨረታ ያወጣ በሀራጅ ተከስሮ ነዉ የሚሸጠዉ ጨረታ እቃ ያሸነፈ ነዉ በሀራጅ ይገዛል ኦዲት ሲደረግ ይወድቃል
በመቀጠል ግን የሰዉ አይንም(ቡዳ) ችግር ሊሆን ይችላል
ያለቅጥ የተካበደ ሰርግ ብራይድ ማድረግ በሰዉ አይን የመበላት አቅሙ ሰፊ ነዉ ለምን በዚህ በኑሮ ዉድነት ባለበት ዘመን የሚበላ የሚጠጣ ቤት ኪራይ መክፈል በአቃቃተበት ዘመን ያለቅጥ ደስታ በደሀ እምባ መቀለድ ነዉ የእናንተን ሰርግ ደሀ ሲያየዉ ወይ የበላችሁበት ወይ የጠጣችሁበት ምግብ ላይ ወይ የለበሳችሁት ልብስ ላይ አይኑ ያርፋል እናም የተቸገረ ሰዉ ቀልብ አይን ከባድ ነዉ ፡፡
በተጨማሪ በዚህ ወንዱ ብር ማስተዳደሪያ ሴት ደግሞ ባል ባጣችበት ዘመን በሚዲያ ሰርጋችሁ ተካብዶ ሲያዩት ወንዱም ወይኔ ትንሽ ኑሮኝ በነበር ሴቷም እድለኛ  ነች የሚያምር ባል አግብታለች ባይባል ጥሩ ነዉ የሰዉ አይን ከባድ ነው፡፡

የተወራለት በሚዲያ የታዩ ሰርጎች ብዙዎች ፍች ተፈጥሮ ደብቁኝ ደብቁኝ እያሉ ነዉ እናም ሁሉም በልክ ይሁን

ልጅ ሲወልዱ በደስታ prpfile pictur ማድረግ ይሄ ደግሞ በጣም ከባድ ነዉ ልጅ ያጣ ያላገባ ባለበት ዘመን ማሻ አላህ ሳይሆን አይኑ አፍንጫዉ መልኩ እናቱን ወይስ አባቱን በሚባልበት ዘመን profile ባይደረግ ባይ ነኝ፡፡

ከሰዎች የተለየ ልብሶችን መልበስ እና ቀን በቀን መቀያየር ይሄም ልብስ ያጡ አይኖች ላይ ትኩረት መግባት ነዉ ፡፡ ዱንያ ነዉ መብላት መጠጣት መልበስ ነዉ ማለት ቡሀላ ምነዉ ባልበላሁ ባልጠጣሁ ባለበስኩ ከማለት ሁሉን በልክ ማድረግ እና በዚክር በቁርአን መንቀሳቀስ ነዉ

   በሰዉ ህይወት ቀንታችሁ በማወቅም ባለማወቅም ያሰራችሁ ካላችሁ ጉዳቱ ለተደረገበትም ለእናንተም ጭምር መሆኑን አትዘንጉ የተዉበት ጊዜዉ ገና ነዉ ወደአላህ እንመለስ ...እኛ የምናምፀዉ በወንጀል ድንበር የምናልፍበት ጌታችን ቅርብ ሁኖ እያየን እንደሆነ አንዘንጋ....
ጌታችን አሏህ ሱወ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይለናል
“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፣ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፣ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ለምመሩ፡፡ ይከጀላልና፡፡” (አል-በቀራህ፡ 186)

ታዳ ለምን እኛ የሰዉንም የራሳችንን ህይወት ለማበላሸት ደጋሚዎች ደብተራዎች ጠንቋይ ቤቶች እንሄዳለን??
የምንመቀዉን ሰዉ የሰጠዉ አላህ ለምን ለእኛስ ስጠን ብለን ወደ ጠንቋይ ከመሄድ ወደ ጀሊሉ እጃችንን አንዘረጋም??

በሐዲሥ አልቁድሲይ እንደተዘገበው አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- የሰው ልጅና አጋንት በሚገርም ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ እፈጥራለሁ  የሚመለከው ሌላ ነው፡፡ ሲሳይ እሰጣቸዋለሁ የሚመሰገነው ሌላ ነው:: መልካም ነገር ሁሉ ከኔ ወደ ባሮቼ ይወርዳል፤ የነሱ መጥፎ ነገር ወደኔ ይወጣል፡፡ ከነርሱ የተብቃቃሁ ሆኜ ሳለ በእዝነቴ ወደነርሱ እወደዳለሁ፡፡ እነርሱ ግን ከኔ ፈላጊ ድሆች ሆነው ሳሉ ወንጀል በመሥራት በኔ ለመጠላት ይሠራሉ፡፡ ለኔ ቅርብ የሆኑት እኔን የሚያወሱት ናቸው፡፡ እኔ   የምወዳቸው እኔን የሚታዘቡት ናቸው፡፡ ወንጀል የሚሠሩትን ከእዝነቱ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም፡፡ በተዉባ ወደኔ የሚመለሱትን እኔ ወዳጃቸው ነኝ፡፡ ቢያምፁም አካሚያቸው እኔ ነኝ፡፡ በችግርና መከራ የምፈትናቸው ከነውር ላፀዳቸው ነው፡፡ ተውባ አድርጎ ወደኔ የሚመለስን ሰው ገና ሩቅ እያለ እቀበለዋለሁ፡፡ ከኔ ዞር ብሎ የሄደውን በቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ፡፡ ከኔ ውጭ ሌላ አምላክ አለህ እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው?› እለዋለሁ፡፡
በተጨማሪ

አላህ ለነብዩ ዳወድ እንዲህ አለ፡- ዳውድ ሆይ! ለኔ ጀርባቸውን የሰጡ ሰዎች (ወደኔ በመመለሳቸውና ተፀፅተው በመምጣታቸው) ለነርሱ ያለኝን ጉጉት ቢያውቁ ኖሮ ለኔ ከሚኖራቸው ጉጉት የተነሳ በቀለጡ ነበር፡፡ ዳውድ ሆይ! ይህ ለኔ ጀርባቸውን ለሰጡ ሰዎች ያለኝ ፍላጎት ነው፡፡ ፊታቸውን ወደኔ ላዞሩ ሰዎች እንዴት የሚሆን ይመስልሀል?
አላህ እንዲህ እያለ ይወቅሰናል
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳፅና ከቁርአንም ለወረደዉ ልቦቻቸዉ ሊፈሩ ጊዜዉ አልቀረበምን??
አላህ እየወደደን ወደኔ ቅረቡ እያለ ይለምናል እኮ
እናም ያለፈዉ ስህተት ከነበርን ቶብተን ወደ አላህ እንመለስ ያስደረግንም ካለን በሰዉ ህይወት አንጫወት ላንጠቀም ነገር ሲህሩ ድግምቱ እንዲፈታ እንዲቆም ማድረግ አለብን፡፡
ህሊና ላለዉ ሰዉ  ሲህር አስደርጎ የተደረገበት ሰዉ ሲሰቃይ ሲቸገር ሲታመም እንዴት አቅላችን ይሸከመዋል??
እንዴት ሰዉ እንዳያገባ ተደርገ የእሱ ወይ እሷ አግብቶ መዉለድ እንዴት እኛን ሊያናድደን ይችላል??ብቻ አሁንም የተዉበት በሩ ክፍት ነዉ ወደ አላህ እንመለስ


#ክፍል
ይቀጥላል.....


አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ
T.me/Aisuu_bot

ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group