Get Mystery Box with random crypto!

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት (ክፍል–3) የሶስተኛው እለት ተግባር እሱም ከዙል–ሒጃ | ኢስላማዊ እውነታ

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

(ክፍል–3)

የሶስተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስረኛው የዒድ ቀን ነው።

ሚና ሲደርስ ወደ ጀምረተል—ዓቀባ በመሄድ "አላሁ አክበር " እያለ በማከታትል ሰባት ጠጠሮችን ይወረውራል።
ሀድይ ወይም የመቃረቢያ መስዋእት ካለው ያርዳል።
ፀጉሩን ይላጫል ወይም ያሳጥራል።

እነዚህን ተግባራት በመፈፀሙ የመጀመሪያ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል—አወል) ይከሰትለታል። በመሆኑም ከግብረ—ስጋ ግንኙነት ውጭ በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩ ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
ወደ መካ መሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህ ማድረግ፦
ወደ መካ ይሄድና ጠዎፈል— ኢፋዷህን (የሐጅ ጠዎፍን) ያደርጋል። ሙተመቲዕ (በሐጅ ወራት ዑምራን ፈፅሞ በዚያው ጉዞ ሐጅን የሚያደርግ) የሆነና እንዲሁም ሙተመቲዕ ባይሆንም በመጀመሪያ የመግቢያ ጠዎፉን ሲያደርግ አሰከትሎ በሰፋና መርዎ መካከል ሰዕይ ያላደረገ ከነበረ የሐጅን ሰዕይ ያደርጋል።
በዚህ ተግባሩም ሁለተኛ ደረጃ መፈታት (ተሀሉለል አስ–ሳኒ) ይከሰታል። በመሆኑም የግብረ—ስጋ ግንኙነትን ጨምሮ ሌሎቹም በኢህራም ላይ በመሆኑ የተነሳ ክልክል ሆነውበት የነበሩበት ነገሮች ሁሉ ይፈቀዱለታል።
ወደ ሚና በመመለስ አስራ አንደኛውን ሌሊት በዚያ ያድራል።

ይቀጥላል…

ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ… አላህ ያግራልን!

*ጣሀ አህመድ

https://t.me/tahaahmed9