Get Mystery Box with random crypto!

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት (ክፍል–4/ የመጨረሻው ክፍል) የአራተኛው እለት ተግ | ኢስላማዊ እውነታ

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

(ክፍል–4/ የመጨረሻው ክፍል)

የአራተኛው እለት ተግባር

እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ አንደኛው ቀን ነው።

በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል። የመጀመሪያው ከዚያም መካከለኛው ከዚያም ጀምረተል–ዓቀባ ላይ እያንዳንዱ ጉድጓድ ላይ ሰባት ሰባት ጠጠሮችን በማከታትል እና እያንዳነዱን ጠጠር በሚወረውርበት ጊዜ "አላሁ አክበር " በማለት ይሆናል። ጠጠር የመወርወር ተግባሩ የሚሆነው ጸሐይ ከአናት ከተዘነበለች በኋላ ነው። ከዚያ በፊት መወርወሩ አይፈቀድም።
ከመጀመሪያው እና መካከለኛው የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓድ በኋላ ዱዓእ ለማድረግ መቆም ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
አስራ ሁለተኛውን ለሊት ሚና ውስጥ ያድራል።

የአምስተኛው እለት ተግባር


እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሁለተኛው ቀን ነው።

በአራተኛው እለት እንዳደረገው ሁሉ በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
ተቻኩሎ በአስራ ሁለተኛው ቀን ከሚና መውጣት ከፈለገ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይወጣል ወይም እስከ አስራ ሶስተኛው ቀን መዘግየት ከፈለገ በዚያው ያድራል።

የስድስተኛው እለት ተግባር


እሱም ከዙል–ሒጃ ወር አስራ ሶስተኛው ቀን ነው።
የዚህ እለት ተግባር ሚና ላይ የዘገዩትን ሰዎች ብቻ ነው የሚመለከተው።

ከዚህ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት በፈፀመው መሰረት በሶስቱ የጠጠር መወርወሪያ ጉድጓዶች ላይ ጠጠር ይወረውራል።
ከዚያ በኋላ ሚናን ለቆ ይወጣል።
የመጨረሻው ስራ ጠዋፈል—ወዳዕ (የመሰናበቻ ጠዎፍ) ይሆናል። እርሱም ወደ ሀገሩ ሊመለስ ሲል የሚያደርገው ነው።

ተፈፀመ

አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!

ጣሀ አህመድ

https://t.me/tahaahmed9