Get Mystery Box with random crypto!

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት (ክፍል–2) የሁለተኛው እለት ተግባር እሱም ከ | ኢስላማዊ እውነታ

የሐጅ ተግባራት አፈፃፀም እለት በእለት

(ክፍል–2)

የሁለተኛው እለት ተግባር
እሱም ከዙል–ሒጃ ወር ዘጠነኛው የዓረፋ–ቀን ነው።
ፀሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ዓረፋ ይጓዛል። የዙህርና የዓስርን ሰላቶች ሁለት ሁለት ረከዓ በማድርግ አሳጥሮ እንዲሁም አስቀድሞ በዙሁር ሰላት ወቅት ይሰግዳል። ፀሐይ ከአናት ከመዘንበሎ በፊት እዚያ ከደረሰና ከገራለት የሰላቱ እና የኹጥባው ስነ–ስርአት እሰኪጠናቀቅ ነሚራ በምትባለው አሁን መስጂድ በተሰራበት ቦታ ያርፋል።
ከሰላት በኋላ ፀሐይ እሰክትጠልቅ ያለውን ጊዜ ለዚክር እንዲሁም ወደ ቂብላ አቅጣጫ በመዞር እጆችን ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመዘርጋት ለሚፈፅመው የዱዓእ ስነ–ስርአት ያውለዎል።
ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሙዝደሊፋ ያቀናል። መግሪብን ሶስት ዒሻን ሁለት ረከዓ አድርጎ እዚያ ሲደርሰ ይሰግዳል። ጎህ እሰከሚቀድ ድረስም ለሊቱን በዚያው ያሳልፋል።
ጎህ ከቀደደ በኋላ የፈጅር ሰላትን ይሰግዳል ከዚያ በኋላ በደንብ መንጋቱ እስኪታወቅ ድረስ ያለውን ጊዜ ለዚክር እና ዱዓእ ያውለዎል።
ከዚያም ፀሐይ ከመውጣቶ በፊት ወደ ሚና ጉዞ ይጀምራል።

ይቀጥላል…

ለሌሎች በማስተላለፍ የመልካም ስራ አጋር ይሁኑ… አላህ ያግራልን!

ጣሀ አህመድ

https://t.me/tahaahmed9