2022-02-13 13:45:43
ዱንያን …………………
________
#ነቢያችን_ሰ_ዐ_ወ በቤታቸው እሳት ሳይነድ (ምግብ ሳይበስል) ቀናት ያልፍ ነበር። ብዙ ጊዜያት እንደተራቡ ወደ መኝታቸው ተጉዘዋል።
አንድ ቀን #ዑመር_ረ_ዐ ወደ #ነቢዩ_ሰ_ዐ_ወ ቤት መጡ። ወደ ውስጥ ሲገቡም #ነቢዩ_ሰ_ዓ_ወ ከቴምር ቅጠል በተሰራ ፍራሽ ላይ ተኝተው ነበር።
ደረቆቹ የቅጠል ጠርዞች በውድ #የነቢያችን_ሰ_ዐ_ወ ሰውነት ላይ ሰንበሮችን አውጥተዋል።
በአንድ ጥግ ትንሽ ዱቄትና ውሃ አዩ። ከነዚህ ነገሮች በቀር በቤት ውስጥ ፈፅሞ አንድም ነገር የለም።በዚህ ወቅት ታዲያ መላው አረቢያ #በነቢያችን_ሰ_ዐ_ወ አስተዳደር ስር ነበረች።
#ዑመር_ረ_ዐ እጅግ ደነገጡ። እምባቸውንም ማቆም አልቻሉም። #ነቢያችን_ሰ_ዐ_ወ " #ዑመር ሆይ!! ለምን ታለቅሳለህ? "ሲሉ ጠየቁት።
#ዑመርም_ረ_ዐ እንዲህ ሲሉ መለሱ :-
"እንዴት አላለቅስ #የአላህ_መልዕክተኛ !! የሩም እና የፋርሺያ ንጉሶች በምቾት ሲንደላቀቁ #የአላህ_መልዕክተኛ_ሰ_ዐ_ወ ከቴምር ዛፍ ቅጠል በተሰራ ደረቅ ፍራሽ ላይ ይተኛል!!! "
#ነቢዩ_ሰ_ዐ_ወ እንዲህ አንዲህ አሉት :-
" #ዑመር ሆይ!! ቄሳርና የፋርስ ንጉስ በዚህ ዓለም ይደሰቱ፤ ለኛ ግን የቀጣዩ ዓለም ደስታ በቂያችን ነው! ።"
ቀጥለውም :-
"ይህ ዓለም ለኔ ከቶ ምን ያደርግልኛል!
የእኔ እና የዚህች ዓለም ግንኙነት እንደ በጋ መንገደኛ ነው!! ከዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ መልሶ እንደሚጓዘው ።
( :- ቲርሚዚ ) #ሰለላሁ_ዓለይሂ_ወሰለም
https://t.me/islamic_wallpeper
552 views10:45