Get Mystery Box with random crypto!

ኢስላማዊ አለም እና ግጥም☪️

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_poem_ss — ኢስላማዊ አለም እና ግጥም☪️
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_poem_ss — ኢስላማዊ አለም እና ግጥም☪️
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_poem_ss
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.57K
የሰርጥ መግለጫ

አሰላሙ አለይኩም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች
🦋 በየሳምንቱ ቅዳሜ ግጥሞች
🦋ኢስላማዊ አባባሎች
🦋የኸሊፋዎች ንግግሮች
🦋 አስተማሪ መልክቶችን ይለቀቃሉ!
"ስለ ሁሉም ነገር
አልሀምዱሊላህ"
For any comment
@Sumii67

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 22:12:36
የአራቱ ኸሊፋዎች ታሪክ በቃላሉ ማግኘት ይፈልጋሉ?? እንግድያዉስ
የነሱን ታሪክ ማግኘት ከፈለጉ ከታች የነሱን ታሪ በየ ክፍሉ እናስቀሚጥላቹኋለን እናንተ እሱን ሲቲጫኑ ቀጥታ ወደ ታሪኩ ጋር ይወስዳቹኃል።
የሁሉም የ4ኸሊፋዎች ታሪክ ከ1 እክከ 5 ክፍል ነው።የአንዱን ኸሊፋ ታሪክ ከነካችሁት ወደ አንድ ክፍል ነው የሚወስዳቸው ክፍል ,2,3,4,5 ወደታች እየሄዳችሁ ፈልጉት ለአስተያየት @Isehac
33 views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 21:39:04
ፈገግ በሉ ፈገግታ ሱና ነው

ባልና ሚስት ነበሩ ባል ለይል ይሰግዳል ሚስት ግን አንቅልፋ ትወዳለች፡፡ ባል በሰንት መከራ ነው ፈጂር እንድትሰግድ የሚቀሰቅሳት፡፡
አንድ ቀን በጣም ተበሳጨና ሲቀሰቅሳት እንቢ አለችው ፡፡ በሌላኛው ቀን ለይል ሰግዶ ከጨረሰ በኅላ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያረቢ ከእኔ ጋር ሰላተል ለይል የምትቆም ሚስት ዳረኝ ብሎ ዱአ ሲያደርግ

የሰማችው ሚስቱ ...... See more

ሙሉውን ለማንበብ ከስር See more ሚለውን ይጫኑ
ማሳሰቢያ:–ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም ተለቋል።ገብታቹ ማየት ነው።ሌሎች ታሪኮችም ለማግኘት ከስር open ሚለውን ይንኩ።

ሙስሊም አይዋሽም ውሸት ሀራም ነው

See more
124 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 08:24:42
አዞኖ ለቀረበ ሁላ ብሶት አይወራም

ሊናዳምጥ የሚገባ እጅግ ልብ የሚነካ ምርጥና እና አስተማሪ ምክር ነው። አዳምጡት!! | አዳምጠው ሲጨርሱ SAHRE •Join• ማድረግዎን እንዳይረሱ!!

ለማዳመጥ ከስር See more ሚለውን ይጫኑ
ማሳሰቢያ:–ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም ተለቋል።ገብታቹ ማየት ነው።

ሙስሊም አይዋሽም ውሸት ሀራም ነው

See more
See more
238 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 13:41:39 ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳወሳችው ሰዕድ (ኢብን ሙዐዝ) በኸንደቅ ጦርነት የእጁ ዋነኛ ደም ስር ላይ ቆሰለ፡፡ ነቢዩም በመስጊድ ውስጥ አንድ ድንኳን ጣሉ በቅርብ ለመከታተል እንዲችሉ፡፡ በመስጊዱ ውስጥ የበኒ ጊፋር ድንኳንም ነበር፡፡ ከሰዕድ ድንኳን ወደ በኒ ጊፋር ድንኳን ደም መፍሰስ ጀመረ፡፡ ‹‹እናንተ ባለ ድንኳኖች ከናንተ ወደኛ የሚመጣው ምንድን ነው?›› በማለት ጮሁ፡፡ ከሰዕድ ቁስል በከፍተኛ ሁኔታ ደም እየፈሰሰ ነበር፡፡ ሰዕድ በድንኳኑ ውስጥ እያለ ሞተ፡፡

(ቡኻሪ ዘግበውታል)

@Damemaka
@Damemaka
567 views10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 08:07:24 ‍ #የስኬት_መንገድ

ብዙም ባይኖረዉም ስላለዉ አመስግኖ በደስታ የሚኖር አንድ አፍሪካዊ ገበሬ ነበር። አንድ ቀን ጎረቤቱ የገበሬዉ ቤት መጥቶ በወሬ መሃል እንዲህ አለዉ “አዉራ ጣትህን የሚያክል አልማዝ ቢኖርህ የራስህ ከተማ ይኖርህ ነበር። የእጅህን ጭብጥ የሚያክል አልማዝማ ቢኖርህ የራስህ አገር ይኖርሃል።”

ያን ቀን ለሊት ገበሬው እንቅልፍ ባይኑ አልዞር አለዉ። ሰውዬው የነገረዉን ነገር ሲያወጣ ሲያወርድ እንዲሁ ነጋ። ጠዋት ተነስቶ እርሻዉን ሸጦ፣ ቤተሰቦቹንም ለሰዉ አደራ ሰጥቶ አልማዝ ፍለጋ ከቤቱ ወጣ። ካገር አገር ብዙ ተንከራተተ። የፈለገዉን አልማዝ ግን ሊያገኝ አልቻለም። በመጨረሻም ብዙ ደክሞ፣ ተጎሳቁሎና መንፈሱ ተሰብሮ ተስፋ ስለቆረጠ ራሱን አጠፋ።

የእሱን እርሻ የገዛዉ ሰው በእርሻው ዉስጥ የሚያልፍ ወንዝ ጋር አንድ ቀን እንስሶቹን ውሃ ሲያጠጣ በጣም የሚያብረቀርቅ አለት አየና ለቤት ጥሩ ጌጥ ይሆናል ብሎ ቤቱ ዉስጥ አስቀመጠዉ።

የመጀመሪያዉን ገበሬ ስለአልማዝ የነገረዉ ጎረቤት ያን ቀን የዚህ ሰው ቤት መጥቶ ያን የሚያብረቀርቅ አለት ተመለከተና “ለመሆኑ እርሻዉን የሸጠልህ ገበሬ ከሄደበት ተመለሰ?” ብሎ ጠየቀዉ።

አዲሱ የእርሻ ባለቤትም “አይ አልተመለሰም። ምነዉ ጠየቅህኝ?” አለዉ።

ሰውዬዉም “አልማዝ ማለት እኮ ይሄ አንተ ያገኘኸዉ ድንጋይ ነዉ! ያን ፍለጋ እኮ ነዉ ወጥቶ የቀረዉ!”

“የዚህ አይነትማ ግቢዉን ሞልቶታል ና ላሳይህ” ብሎ በግቢዉ የሞላዉን እስከዛን ቀን ግን አያዉቀዉ የነበረዉን አልማዝ አሳየዉ ይባላል።

#ጭብጥ
በዙሪያችን ብዙ እድሎች አሉ፤ ርቀን መሄድ ላያስፈልገን ይችላል። ከኛ የሚጠበቀዉ አይናችንን ከፍተን በማስተዋል መጓዝ አጋጣሚዉን ስናገኝም ወደስራ መግባት ነዉ።

share ማድረግ እንዳይረሳ!

@Damemaka
@Damemaka

For any Comment @Isehac
2.5K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 22:33:21 የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ትሩፋቶች እና ፈጅርን አለመስገድ ያለው አደጋ
~ ~ ~~~~ ~~~ ~
1. ፈጅርን ስገድና በአላህ ጥበቃ ስር ሁን፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም]
2. ፈጅርን ስገድ ሌሊቱን በሶላት እንደቆምክ ይቆጠርልሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
3. ሱብሕን ስገድ እራስህን ከሙናፊቆች መገለጫ አፅዳ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ለጭንቅ ቀን ብርሃን ይሆንሃልና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በጨለማዎች ወደ መስጂዶች የሚጓዙትን በቂያማህ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አብስራቸው” ይላሉ፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 570]
5. ሱብሕን ስገድ መላእክት ይመሰክሩልሃል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “በናንተ ውስጥ የሌሊት መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡ በፈጅር ሶላት እና በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡ ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት (ወደ ሰማይ) ይወጣሉ፡፡ ይህኔም ጌታቸው በነሱ ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ ተዋቸኋቸው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
6. ሱብሕን ስገድ ሙሉ የሐጅና የዑምራን አጅር እፈስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የማለዳን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!” ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3403]
7. ፈጅርን ስገድ በአለም ላይ ካሉ ፀጋዎች ሁሉ በላጭ የሆነ ፀጋ የምትጎናፀፍበት እድል ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የፈጅር ሱንናህ (ከፈርዱ በፊት የምትሰገደዋ ትርፍ 2 ረከዐ ሶላት) ከዱንያ እና በውስጧ ካለ ሁሉ በላጭ ነች” ይላሉ፡፡ [ሙስሊም]
8. ፈጅርን ስገድ ከጀሀነም መትረፊያ ጀነትን መጎናፀፊያ ብስራትን ታገኛለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ፀሀይ ከመውጣቷ እና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም” ይላሉ፡፡[ሙስሊም] እነዚህ ሶላቶች ፈጅርና ዐስር ናቸው፡፡ በሌላም ሐዲሥ “ሁለት ብርዳማ ሶላቶችን የሰገደ ጀነትን ይገባል” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
9. ፈጅርን ስገድ ከፀጋዎች ሁሉ በላጭ ፀጋ የሆነውን የላቀውን ጌታ መመልከትን ትታደላለህና፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “እናንተ ይህን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ታያላችሁ፡፡ እሱን በማየትም አትቸጋገሩም፡፡ ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለ ሶላት አለመረታት ከቻላችሁ አድርጉት (ስገዱ)” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
10. ፈጅርን ስገድ ጥሩ ነፍስ ይዘህ አንግተህ ንቁ ሆነህ ትውላለህ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ተጠንቀቅ!
1. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ከፈጅር ሶላት መሳነፍ አደገኛ የሆነ የሙናፊቆች ምልክት ነውና!! [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ የሸይጣን መፀዳጃ አትሁን፡፡ በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ እስከሚነጋ ድረስ ሌሊቱን ስለሚተኛ ሰው ተወራ፡፡ ይህኔ እሳቸው እንዲህ አሉ፡- “ያ በጆሮዎቹ ውስጥ ሸይጣን ሽንቱን የሸናበት ሰው ነው!” አሉ፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 644]
3. የፈጅርን ሶላት ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ያለበለዚያ የሸይጣን ወጥመድ ሲሳይ ትሆናለህ፡፡ ቀንህን ሙሉ ድብርት ይጫጫንሃል፣ ንቃት ይቀልሃል፡፡ ፈጅር ላይ ተነስቶ ውዱእ አድርጎ ያልሰገደ ሰው ቆሻሻ ነፍስ ይዞ እንደሚያነጋና ስንፍና እንደሚጫጫነው ተናግረዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
4. ፈጅርን ስገድ ያለበለዚያ በቀብርህ ውስጥ እስከ እለተ ቂያማ የሚዘልቅ ዘግናኝ ስቃይ ትሰቃያላህ፡፡ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተላለፈው አንድ ሰው ተንጋሎ ሌላው ካጠገቡ ቋጥኝ ይዞ በመቆም እራሱን ይደቁሰዋል፡፡ ድንጋዩ ተንከባሎ ሲሄድም እሱን አምጥቶ እስከሚመለስ ድረስ እራሱ እንደነበር ይመለሳል፡፡ ከዚያም እንደ መጀመሪያው ይሰራበታል፡፡ ቂያማ እስከሚቆም ድረስም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል፡፡ ይህን በዚህ መልኩ የሚሰቃየውን ሰውየ ምንነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጂብሪል ሲጠይቁት “ይሄ ቁርኣንን ይዞ ፊት የሚነሳው ከግዴታ ሶላትም የሚተኛ ነው” አላቸው፡፡

ወንድሜ ሆይ! ከፈጅር ሶላት አትዘናጋ፡፡ ወቅቱን ጠብቀህ እንድትሰግድ የሚያግዝህን ብልሃትም ተጠቀም፡፡
1. በጊዜ ተኛ፡፡ የምሽት ወሬ ይቅር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዒሻ በፊት እንቅልፍ፣ (ከዒሻ) በኋላ ደግሞ ወሬ ይጠሉ ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. ቀኑን በወንጀል ከማሳለፍ ተጠንቀቅ፡፡ ወንጀል ከኸይር ስራ ያቅባል፡፡ በሌላ በኩል ለኸይር ስራ ትጋ፡፡ ኢስላማዊ የመኝታ ስርኣቱን ጠብቅ፡፡ የኸይር ስራ አንድ ሽልማቱ ለሌላ ኸይር ስራ መታደል ነውና፡፡
3. ማታ ከመተኛትህ በፊት ለፈጅር ለመነሳት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርግ፡፡ ረጅም ጉዞ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ቢኖርብህ ያለ ማንም አጋዥ ምናልባትም ያለአላርም እየነቃህ ለሶላት ሲሆን መዘናጋትህ ስለእውነት ከባድ የሞራል ልሽቀት ነው፡፡
4. ማንቂያ ደወል (አላርም) ተጠቀም፡፡ ምናልባት ሳይታወቅህ አጥፍቶ የመተኛት አጉል ባህሪ ካለብህ ትንሽ ራቅ አድርገህ አስቀምጠው፡፡
5. በሰአቱ ነቅተህ ከተጫጫነህ “ትንሽ ተኛ” ለሚሉ ሸይጣን እና ነፍስያ ሸንጋይ ጉትጎታ እድል አትስጥ፡፡ መነሳትህ ያለውን ዋጋ፣ መተኛትህ ያለውን አደጋ ላፍታ አስብ፡፡ ብትነሳ 50 ዶላር ይሰጣል ቢባል የሚኖርህን ንቃት ቃኝና እራስህን ታዘብ፡፡ ፈርዱ ቀርቶ ትርፍ የሆነችዋ የፈጅር 2 ረከዐ እንኳን ከዱንያ ፀጋ ሁሉ በላጭ እንደሆነች እራስህን አስታውስ፡፡
6. በመልካም የሚያግዝ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር ካለህም እሰየው፣ ተጠቀምበት፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 21/2007)

@Damemaka
@Damemaka
1.9K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 09:32:59
እኛም በአቅማችን በሶሻል ሚድያ ድምፃቻችንን እናሰማ

የሶሻል ሚድያ ዘመቻ


ፕሮፋይል ይደረግ የጎንደር ሙስሊም ወንድሞቻችን እያለቁ ነው
የፍልስጢንን ክብር በደማቸው የሚጠብቁ ለአንድነታቸው የሚዋደቁ ጀግና ልጆች ያሏት የአቅሷ ፍሬዎች ወኔ እኛም ጋር አለ ሁሉም ልብ ሊል ይገባዋል የነገ ዲናችን ክብር አደጋ ላይ ወድቋል ወንድሞቻችን እየታረዱ ነው

ለአላህ ብላቹ ይሄን ሁላቹም ፕሮፋይል አድርጉት ሙስሊም ነኝ ካላችሁ


ስልካችሁ ላይ ላሉ ሁሉ ሙስሊሞች አዳርሱ
ቢያንስ ለ 20 ሰው በአላህ ስም ተጠይቃችኋል
#share
2.3K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 09:20:29 ከ ጎንደር የተላከ መልእክት ሙስሊም የሆነ ሁሉ ሼር ያድርግ
2.7K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 14:54:38
ፕሮፋይል አድርጉት ትልቅ በላእ ከፊታችን አለ

profile እናድርገው
3.1K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 06:42:59
2.5K views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ