Get Mystery Box with random crypto!

እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ???       አሚር ሰይድ        አሰላሙ አለይኩም እንዴት ና | ISLAMIC SCHOOL

እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ???
      አሚር ሰይድ

       አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ
ዛሬ ላማክራችሁ የፈለኩት አንድ ግራ የሚያጋባ ጥያቄ ከተወሰኑ ቀናታት በፊት በቻናል መጥቶልኝ ነዉ፡፡ እስከዛሬ በቻናል የሚመጡትን ጥያቄዎች ለብቻየ መፍትሄ መስጠት ችዬ ነበር ይሄ ግን ትንሽ ከበድ ብሎኝ ነዉ

እናንተ ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?? በጣም ከባድ ስለሆነ ነዉ ከምትሰጡት አስተያየት አንዱ ከአንዱ ስለሚሻል መፍትሄ ሀሳብ ልቀበልና ለባለታሪኳ እልከዋለሁ


ምን መሰላችሁ እሷና እሱ ለአምስት አመት በላይ ይዋደዳሉ ግን በመሀላቸዉ እየተዋደዱ አንድ ላይ ለመሆን በጣም ሰፊ ክፈተት ነበር ያንን ሰፊ ክፍተት ትንሽ ጠበብ አድርገዉ የዛሬ 3 አመት በፊት ጀምሮ አንድ ላይ ለመሆን ጥረት ያደርጋሉ ግን ያበፊት የነበረ ሰፊ ክፍተት ግን የእሷ ቤተሰቦች ከተስማሙ ቡሀላ ወደ ትዳር ለመግባት 90% ፕሮሰስ ተጨርሶ በተለያዩ ምክንያቶች በእሷም በእሱም በዛ በበፊት ሰፊ ክፍተት ምክንያት አንድ ላይ ሳይሆኑ ቀሩ...ሁለቱም ግን ፍቅር አለባቸዉ 5 አመት ያህል ይዋደዳሉ ስሜቱን ተረድታችሁታል???ሁለቱም በመለያየታቸዉ በፍቅር በትዝታ ተጎዱ ብዙ ወራትን ሳያወሩ ቀሩ፡፡  ግን ህይወት ነዉ እሱ የሌላ ሆነ አጭቷል...እሷ ደግሞ ሌላ ትዳር ቢመጣላትም አይሆንም አሉ ቤተሰቦቿ ፡፡

ባለታሪኳ እንደነገረችኝ አሁን ዋናዉ ችግር እሱ አጭቶ የሌላ ሁኗል በቅርቡ ወይም 2016 ላይ ያገባል እሱ እንደ አጨና እንደሚያገባ አዉቃለሁ

..,ግን ማወቅ ያለብን እሱም ሌላ አጭቶ ሊያገባ ተዘጋጅቶ  ልቡ 5 አመት የሚወዳት እሷ ጋር ነዉ...

  የእሱ እንደልሆን  አዉቃለሁ ነግን ፍቅር የሚባል ህግ አስገድዶን  አሁንም ድረስ እያወራን ነዉ አለችኝ፡፡

መፍትሄዉ እኔም እሱም እናቀዋለን
☞የመጀመሪያዉ እሱ ጋር ማዉራት ማቆም ነዉ

እሱንም ወስኛለሁ....ከአሁን ጀምራችሁ ማዉራት አቁሙም ሊሆን ይችላል ግን አለማዉራቱ በብዙ ምክንያት ጉዳት አለዉ እንደምትሉ አቃለሁ ግን ለጊዜዉ በቴሌግራም ብቻ ማዉራታችን አይቀርም የምናወራዉም አልፎ አልፎ ነዉ እያወራን ለወደፊት ለሚያገባት ሚስቱ ነዉ የምጨነቀዉ የወደፊት ህይወቱን እንዲያስተካክል ጭምር እየታገልኩ ነዉ ሁሉን በሆዴ አምቄ ይዤ
ከአገባ ቡሀላ በአላህ ምያለሁ ላላወራዉ ለእሱም ለኔም ህይወት ስል ላያወራኝ ወስኗል ፡፡ በተጨማሪ
እሱ ከሚኖርበት ሀገር ለመቀየር ወስኛለሁ ...አገሩንም ለመቀየር አመቻችቼ ጨርሻለሁ 2016 መስከረም ላይ እሱ ከሚኖርበት ከተማ እለቃለሁ፡፡ግን እሱ የሚኖርበትን ከተማ ስለቅ ከጊዜ ብዛትም ቢሆን ማግባቴ እኔም የሌላ እሆናለሁ ይሄ ግዴታ ነዉ ህይወት እስከ ሆነ ድረስ

☞ሁለተኛዉ አለመገናኘት ነዉ ግን እሱ ጋር አንድ ሰፈር ነን መገናኘታችን አይቀርም ግን መንገድ ላይ ብንገናኝም ምንም እንዳልተፈጠረ ስቀን በአየር ላይ ሰላም ተባብበለን እንተላለፋለን፡፡

የሚገርመኝ እኔም የእሱ አይደለሁ እሱም የኔ አይደለም
ግን ሁለታችን ስናወራ የሆነ ደስ የሚል የተረጋጋን እንሆናለን የምናወራዉ ግን በቴሌግራም ብቻ ነዉ የኔ አለመሆኑን ከአወኩ በስልክም አዉርተን አናቅም፡፡
ይሄን ስላችሁ በቴሌግራምም ማዉራት አቁሙ ልትሉ ትችላላችሁ ግን እኔ ያማከርካችሁ እንደዚህ እንድትሉኝ አይደለም
ፍቅር ከባድ ነዉ ግን ከፍቅር በላይ የሚከብደዉ ትዝታዎቹና እሱ የሌላ ሁኖ ማየቱ ነዉ
መፍትሄ ሀሳቡ እኔና እሱም እናቀዋለን አለማዉራት ነዉ ግን ሞከርን ሞከርን ሞከርን አልቻልንም ቀን በቀን ባይሆንም በተወሰነ ቀናቶች ልዩነት በtg እናወራለን ያዉ እንደበፊቱ አይነት ወሬ አይደለም
ኖርማል ወሬ ነዉ፡፡


አሁን ከእናንተ የምጠይቃችሁ ሀሳባችሁን እርዳቻችሁን የፈለኩት እነዚህ እታች በቅደም ተከተል በጥያቄ መልክ ካቀረብኳቸዉ ጥያቄዎች እላይ ካነበባችሁት ፁሁፍ ጋር አመዛዝናችሁ እንድትመልሱልኝ ነዉ ለወደፊት እሱ ከአገባ ቡሀላ እኔም ሀገር ከቀየርኩ ቡሀላ እሱም ለሚስቱ እኔም ለወደፊት ህይወቴ መስመር እንድናሲዝ በሀሳብ እንድትተባበሩን ነዉ፡፡


➊ በዚህ ቻናል ዉስጥ እየተዋደዳችሁ ግን በቤተሰብ አይሆንም ወይም በተለያዩ ምክንያት የምወዱትን ያጣችሁ...ግን ወይ የማይወዳችሁን በቤተሰብ ያገባችሁ ሴቶች ካላችሁ የትዳር ህይወት እንዴት ነዉ??የሌላ ሁኖ መልመድ ይቻላል ወይ?? ትዳር ላይ ሁኖ የበፊት ፍቅር ያስቸግራል አያስቸግርም??
የሌላ የሆናችሁ ወንዶች የምወዳት ልጅ ሚስትህ ጋር ሁነህ በሀሳብህ በህልምህ እየመጣች አላስቸገረችህም?? ከረሰሀት ጥሩ ግን ሳትረሳት በሀሳብህ እየመጣች ትዳርህን እንዴት እያስሄዳችሁ ነዉ??
አስተያየታችሁን በዚህ ይላኩልኝ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

➋ እንደዚህ አፍቅራችሁ ያጣችሁ የዚህ አምስት አመት ነዉ...ከአምስት አመት ወይ ከአምስት አመት በታችም ይሁን የምወዱትን ሌላ ሲያገባ ስሜቱን ታቁታላችሁ ከዛ ስሜት ወጥታችሆል??አሁን እሱ የሌላ ሲሆን ወልዶም ሊሆን ይችላል ላይወልድም ይችላል ምን ተሰማችሁ???
አስተያየታችሁን በዚህ ይላኩልኝ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot


➌ አሁን እሱ የሌላ ለመሆን ጨርሷል ሽማግሌ ልኮ የሰርጉን ቀን ቆርጧል...እሱ ለወደፊት እንዳይቸገር ራቂዉ እንደምትሉኝ አቃለሁ እኔም ያሰብኩት ነዉ ግን እሱ እሷ ጋር ጥሩ የተረጋጋ ህይወት እሷ ጋር ተዋደዉ ልጅ የልጅ ልጅ እንዲኖረዉ የዘወትር ዱአየ ነዉ
እሱም ለኔ የሚያስብልኝ ለወደፊት ጥሩ ህይወት እኔ የሚወደኝን አግብቼ የተሻለ ኑሮ እንድኖር ይፈልጋል ኢንሻ አላህ ፈጣሪም ያገዝናል ከአላህ ተስፋ አንቆርጥም...ግን በዚህ ላይ ሁለት ጥያቄ ለአእምሯችሁ ልስጣችሁ በተለይ አግብታችሁ ያላላችሁ ወይም የሰዉ ታሪክ ከሰማችሁት አንፃር
☞አንተ ትዳር ነዉ ብለህ ሌላ የምወዳት እያለች አግብተህ ከእሷ ዉጭ ሌላ ሴት አይታይህም ነበር ግን የአገባሀት ሚስት በፍቅር በእንክብኬቤ የድሮ ፍቅረኛህን አስረስተሀለች??? አልሀምዱሊላህ እሷ ቀርታ ፈጣሪ እሷን የሰጠኝ ብለህ አመስግነሀለል??ከአመሰገንክ ማሻ አላህ ግን እንዴት ልታስረሳህ ቻለች??

እሺ በተቃራኒዉ እንየዉ የአገበሆት ሚስት በፊት ቤተሰቦቿን ጠይቀህ እምቢ የተባልከዉ ጋር ስታወዳድራት የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አላት ያንን ሁሉ ሸፍነህ እንዴት እሷ ጋር አብረህ  እየኖርክ ነዉ??? ልጅም ወልደህ ይሆናል ግን እንዴት ሳትወዳት አብረህ ወልደህ እየኖርክ ነዉ??
ፍቅር ከትዳር ቡሀላ ነዉ ይባላል ግን ከትዳር በፊት የነበረ ፍቅር ያስቸግራል እንዴት በአዲሷ ሚስትህ በፍቅር የተጎዳዉን ልብህን አከምክ??
በዚህ አስተያየትዎን ይፃፉ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

☞እሺ አንቺስ አሁን አግብተሽ ልጅ ወልደሽም ይሆናል....የምወጅዉን ቤተሰብ በሚያሳምንም በማያሳምን ምክንያት አጣሽዉ..ግን እሱ የትዳር ስበብ
ሲያደርስ ከጎኑ ሁነሽ በነበር የመሳካቱ ቻንሱ ሰፊ ነበር እንበል ...እናም ይሄ ምነዉ ሰበቡን አድርሼ በነበር ብለሽ ከአጣሽዉ ቡሀላ ልትቆጭ ትችያለሽ ግን ህይወት ነዉ እኔም ሌላ አገባለሁ በቅርቡ ኢንሻ አላህ ግን የአገባሽዉ ባል እንክብካቤ ሁኔታ በፊት የምወጂዉን አስረስቶሻል??አልሀምዱሊላህ እሱ ቀረብኝ ለኸይር ነዉ እሱን የሰጠኝ ብለሻል???