Get Mystery Box with random crypto!

እባካችሁ አሊሞች ሸይሆች  እኛን ወጣቶች በቁርአን በሀዲስ ኮትኩታችሁ ለነገ ትዉልድ ማስተላለፍ ቢያ | ISLAMIC SCHOOL

እባካችሁ አሊሞች ሸይሆች  እኛን ወጣቶች በቁርአን በሀዲስ ኮትኩታችሁ ለነገ ትዉልድ ማስተላለፍ ቢያቅታችሁ እንደዚህ ፈሳድ የሆነን በየአመቱ ተከታይ አታድርጉን እባካችሁ ወጣቱን የማይጠቅም የማይጓዳ ጀነሬሽን ባለማድረግ ተባበሩን


የተወሰነ ሰዉ ባይሄድ አሁን ባለቸዉ አቋም የሚቀር የሚቆም አይደለም
ግን አለመሄድ የባለቤቱ ወሳኔ ነዉ...አምና ታስታዉሱ ከሆነ ደሴ በተደረገዉ የጎዳና ኢፍጣር ከአየሁ ቡሀላ
በዛዉ በተደረገ ቀን ከአሁን ቡሁላ ላልሄድ ብየ ምያለሁ....ከዘንድሮ ጀምሬ አደባባይ ኢፍጣር አልሄድም
ይሄን ያነበበ አስተንትኖ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም ከሆላም ከፊትም ከሁሉም አቅጣጫ ተመልክቶ በየአመቱ ለወደፊት ለሚካሄድ ኢፍጣር ራሳችሁን ብታገሉ ባይ ነኝ ...የአንድ የሁለት ሰዉ መቅረት ይሄን የአደባባይ ኢፍጣር ለማስቆም አቅም ባይኖረዉም ግን ለወደፊት በየአመቱ ለሚፈጠር ቢድአ ተባባሪ አለመሆን አንድ የሙስሊም ግዴታ ነዉ





ነገር ግን አንዳንድ ደጋግ የአላህ ባሮችና ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በየጎዳናዉ የተቸገሩን ማፍጠሪያ የሌላቸዉን በየጎዳናዉ ያስፈጥራሉ እንደዚህ ያሉትን ደጋግ ባሮች ጀመአዎች ለአላህ ብለዉ የሚሰሩን አላህ ንያቸዉን አጅራቸዉን እጥፍ ድርብ ያርግላቸዉ ይሄ መበረታታት ያለበት ነዉ...ነገር ግን የአደባባይ ኢፍጣር ተብሎ ፆታ መለየት እስከሚያቅት  ወንድ ሴት ተደባልቆ ታላቁ በአይኑ የተለየ ይሄን ያህል ሜትር  ክብረ ወሰን በጠስን እያሉ በዲን ስበብ ፈሳድ ባይበዛ ኸይር ነዉ፡፡


ኸይር ፅፌ ከሆነ ከጀሊሉ ነዉ መጥፎ ወይ ስህተት ፅፌ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አዉፍ በሉኝ ስህተት ከሆነም አሳማኝ ምክንያት ከአገኘሁ ስህተት ነዉ ብየ ፁሁፉን ከቻናል እሰርዛለሁ