Get Mystery Box with random crypto!

በነገራችን ላይ እንደ ወሎየ እያሰብኩም ሊሆን ይችላል... የኔ ሁለት አያቶቼ ክርስቲያን ናቸዉ .. | ISLAMIC SCHOOL

በነገራችን ላይ እንደ ወሎየ እያሰብኩም ሊሆን ይችላል... የኔ ሁለት አያቶቼ ክርስቲያን ናቸዉ ..አጎት የአጎት ልጅ ምናምን እንደ ወሎ አንድ ላይ በልተን ጠጥተን አድገናል ከዛ አንፃር እያሰብኩም ሊሆን ይችላል....ግን የኛ ሙስሊም ችግር ዲነል ኢስላምን እንኳን ለሌሎች ሀይማኖት ማዳረስ ይቅርና ለሙስሊሙ ለማስተማር ኡስታዞች ሸይሆች ከወጣት እስከ ትልቅ ሙስሊሙ በዱንያ ቢዚ ሁኗል የዚህ ችግር እንጂ
ሞክሩ እነሱን ኢስላምን በማስተማር ቀላል ነበር የኔ ቤተሰቦች 20% የሚሆኑት መልሰዉ ሰልመዋል
የኛ ችግር እነሱ ቦታ ተቀበሉ እንደዚህ አረጉ እርይ ኡኡኡኡ በቃ አለቀ የጮሀዉ ሁሉ 1% ሲሰራ አይታይም ጥጉን ይይዛል.... የሌሎችን ሀይማኖት ተከታዮችን ኢስላምን ለማስተማር እስከ ጥግ ድረስ ጥረት ሲደረግ አላየሁም...

ማወቅ ያለብን ለሌላ ሀይማኖት ኢስላምን ማስተማር ግዴታ እንዲሰልም አይደለም
ለኢስላም መጥፎ አመለካከት እንዳይኖረዉ ለማድረግ ጭምር መሆን መታሰብ አለበት ኢስላም የሚሰጠዉ አላህ ብቻ ነዉና...ከልምድ አንፃር አንድ ሰዉ ማስለም የፈለገ በጥረት የ5-7 አመት ትግል ያስፈልጋል
ሀይማኖት እኮ እንደ ስም በፍርድ ቤት ሂደህ በአንድ ወይ በሁለት ቀን የምትቀይረዉ ነገር አይደለም
ሀይማኖት መቀየር የህሊና ጦርተን ያለበት..ከቤተሰብ ከዘመድ ከወዳጅ የሚያራርቅ ከባድ ዉሳኔ ነዉ ስለሆነም የአሁን ሙስሊም በአንድ ወይ በሶስት ቀን የሚቀይሩ ስለሚመስለዉ አካሄድ አይችልም..እነሱን ከመወንጀል ከመከታተል ዉጭ እናም ይሄ መታረም አለበት በዚህ ቻናል ብዙ የማቃቸዉ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ጋር ስለማቅ ስለምግባባ ጭምር ነዉ ፡፡
እናም መጀመሪያ ሁሉም ሙስሊም የኛ ጥርት ያለ ነዉ ማለት አንችልም የኑሮ ዉድነት እየመጣብን ያለዉ በተለይ በብዙ ስግብግብ ሙስሊም ነጋዴዎች መሆኑ አንዘጋ ይሄዉ ዘንድሮ ተምር 3000 ከዛም በላይ ገብቶ በካርቶን የለመድነዉ በኪሎ አፁመዉናል እኮ መታሰብ ያለበት ተምር የሚሸጡት 90% በላይ ሙስሊም ነጋዴዎች መሆኑን አንዘንጋ

እያየነዉ ባለዉ ተጨባጭ ከሌላ ሀይማኖት ሰልመዉ ወደ ኢስላም የገቡ ናቸዉ ለኢስላም እየሰሩ ያሉት...ሙስሊሙ የኢስላምን ፀጋ ስጦታ አላስተነተነዉም ግን የሰለሙ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠዉ ቆርጠዉ ወደ ኢስላም ስለገቡ ቁርአን ቀርተዉ ሀዲስ ተፍሲር ቀርተዉ ሙስሊም ሁኖ የተወለደን እያስተማሩና ሌሎች ለመስለም ያልታደሉትን ወደ ኢስላም እየጠሩ እያስተማሩ እያሰለሙ እያየን ነዉ እናም አሁን ላይ በጣም ጭፍን ጥላቻ እነሱ ጋር ያለዉ አያስፈልግም ማስተማር እንጂ

እኛም ማወቅ ያለብን ነብዩ ሰዐወ አንድ ሰዉ እናንተን በባህሪ በሁሉ ነገር አይተዉ ለመስለም ጉጉት ካላደረጉ ኢማናችሁ ድክመት አለበት ብለዋል...የኛ ባህሪ ኢስላምን ይጣራል ወይ??



አሁንም በዚህ HIV+ ዙሪያ ገንቢ አስተያየት ካለ እቀበላሁ፡፡ሙሉ በሙሉ ችግሩን መቅረፍ ባንችል አንድ ወይ ሁለትም ቢሆን ትዳር ቢያገኙ ትልቅ ነዉና በተቻለን እንታገል እንረባረብ ...የነገን ማን ያቃል በጣም ከባድ ኬዝ ነዉ እናም  እስኪ HIV+ የሆኑትን ቀረብ ብላችሁ የተወሰነ ለመረዳት ሞክሩ እየሳቁ ብዙ የሚደብቁት ችግር የሙራል የሳይኮ ጉዳት ብቸኝነት ተስፋ መቁረጥ ተሸክመዉ ነዉ የሚዞሩት ወላሂ ብዙዎች ተስፋ የቆረጡ ናቸዉ

ከጎናቸዉ ልንሆን በሀሳብ ልንረዳቸዉ ይገባል ..ብዙዎች ሲወለዱ ከቤተሰብ ነዉ የሚይዛቸዉ ወደዉ ያልተቀበሉት በሽታ ነዉ እናም በሀሳብ ያለንን በመርዳት ትዳር በማፈላለግ ጭምር ከጎናቸዉ እንሁን

አስተያየት ለመስጠት
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot