Get Mystery Box with random crypto!

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ እንዴት ናችሁ              አሚር ሰይድ     | ISLAMIC SCHOOL

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
እንዴት ናችሁ
             አሚር ሰይድ

    ከተወሰኑ ቀናቶች በፊት በተፓሰተዉ በHiv positive ያለባቸዉ ችግሮች እና እነሱ ትዳር እርስ በራሳቸዉ ለመገናኘት ከባድ ፈታኝ ችግር ስለሆነ በቻናል ላይ የጤና ባለሙያዎች እና ማንኛዉም ያነበበዉ ሙስሊም የራሱ ሀሳብ ካለዉ እና Hiv positive የሆናችሁ በአስተያየት መስጫ bot እንዲያሳዉቁኝ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ፓስቼ ነበር
ከሞላ ጎደል ከአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ አንፃር Data ስለተዘጋ በpisphon ብቻ ስለምንጠቀም በpisphon የማይጠቀምም ስላለ በተጨማሪም የተፓሰተዉ ረመዳን ሊገባ 10 ቀን ሲቀረዉ ስለሆነ በዚህ ቀናቶች ደግሞ አንዳንድ ወገኖች ረመዳንን ብቻ ሚዲያ አልጠቀምም ብለዉ የሚቶብቱ ስላሉ አላህ በዛዉ ከሚዲያ የሚጠፉ ያድርጋቸዉና እንደታሰበዉ ፁሁፉ ለብዙ ሰዉ ተደራሽ ባይሆንም ግን ከታሰበዉ እቅድ 55% ግብ ላይ ዉሏል

☞በአስተያየት ላይ ሰዉ በጣም ሰፊ ልዩነት ያለዉ እንደዉ ስለ Hiv አያቁም ወይ ያስብላል የሚሰጡት comment ደባሪ የሰጡ አሉ ምን ይባላል ጀሊሉ እዉቀትን ጨምርላቸዉ ከማለት ዉጭ.. ስድብም የሰደቡኝ ነበሩ እነሱ የማይጠቅም የማይጎዱ ስለሆኑ
ከቻናል ተጭረዋል መቀመጣቸዉ ቻናል ከማሞቅ ዉጭ ጥቅም የላቸዉም

☞ የተወሰኑ ወደ 5 comment ደግሞ Hiv ይለቃል የሚሉም አየሁ ይሄን እያዩ አንዳንድ ከተሞች ሰፈሮች የፈጣሪ ቁጣ እንጂ በሽታ አይደለም ብለዉ ራሳቸዉን ያሳመኑም አሉ ....
የለቀቀዉ ሰዉ ብሎ የነገሩኝ ግራ ገብቶኝ የጤና ባለሙያ ስጠይቅ አይለቅም ግን በሽታዉ ስለሚዳከም ስትመረመር ላያሳይ ይችላል ብለዉኛል እናም ይለቃል ብላችሁ ባይዳከሙ ባይ ነኝ፡፡ ግን አንድ አዲስ አበባ የተፈጠረ የማቃት ልጅ የነገረችኝ ገርሞኛል ግን መንገሩ ጥሩ ስለማይሆን በደንብ ማሰቡ ይሻላል

☞ በቻናል Hiv positive ራሳቸዉን ይፋ ያደረጉት ሴቶች ብቻ ሲሆኑ ..ግን ተማሪዎችም ስራ ላይ ያሉም የወለዱም አሉ ግን ፈጣሪ ይድረስላቸዉ 95% ተስፋ የቆረጡ ሁነዉ አግኝቻቸዋለሁ :: የተወሰኑትም ተስፋ ቆርጠዉ መድሀኒት እስከማቆም የደረሱ ነበሩ እነሱን በሶይኮ ማከምና እነሱን የስነልቦና ምክርን በመስጠት መድሀኒት በማስጀመርና ለወደፊት ህልም ሰንቀዉ ተማሪዎችም ተምረዉ እንደነሱ hiv+ የሆኑትን መርዳት እንዳለባቸዉ የተለያዩ ምክሮች ልምዶች በመስጠት እነሱን በፊት ካሉበት ዲፕሬሽን በማዉጣትና መድሀኒት ያቋረጡትን ደግሞ እንዲጀምሩ በማድረግ በቅርብ በመከታል 97% ተሳክቷል አልሀምዱሊላህ ለወደፊትም ከጎናቸዉ ሁኜ እከታተላቸዋለሁ

☞አንድ እንኳ ወንድ ማግኘት አልቻልንም..ይሄ ማለት
ብዙዎች ደብቀዋል ወይም ከኑሮ ዉድነት አንፃር አሁን ላይ ትዳር ለመመስረት ስለከበደ ሊሆንም ይችላል እናም ለማገናኘት የተለባለዉ ወንድ ማግኘት አልቻልንም....
የHiv+ group አለ እዛ ወደ 20 ወንዶች ነበሩ ግን ከወሬ የዘለለ ቁም ነገር የላቸዉም...እነዚህን አግቡ ማለት ስስ የሆነ የሴት ልብን መጉዳት ነዉ፡፡ ለምን ብዙ ሴቶች በዚህ ኬዝ ያሉ እዉነት ስለሚመስላቸዉ የትዳር ፕሮሰስ ተጀምሮ ቢያፈገፍጉ የሴቱ ልብ ይጎዳል ከዚህ አንፃር ለማግባት የነየተን እንጂ እኔም የዚህ ኬዝ ካላት ጋር ወሬ ብቻ የሚወራን ማገናኘቱ ለሴቶቹ ጉዳት መጨመር እንጂ ጥቅም ስላልታየ ትተነዋል

☞ አዲስ አበባ ላይ መድሀኒቱን የሚሰጠዉ የጤና ባለሙያዉን ለማማከር በየጊዜዉ ይቀያየራሉ ብለዉኛል ይሄ ትንሽ ለማማከር ይከብዳል ግን ከአዲስ አበባ ዉጭ ያሉ ከተሞች መድሀኒቱን የሚሰጠዉ  አንድ የጤና ባለሙያ የተወሰኑ ወራቶች እስከ አመታትም ስለሚቆይ ብታማክሩ አሪፍ ነዉ መፍትሄ ግብ ላይ መድረስ ግዴታ ስበብ ማድረስ ስለሚያስፈልግ፡፡ Hiv+ ስለትዳር ሲታሰብ የመጀመሪያ ዉሳኔ መሆን ያለባቸዉ የጤና ባለሙያ ማማከር መሆኑን አንዘጋ...ግን የወሰኑ ሴቶች የጤና ባለሙያ ስናማክር የምናገኘዉ እድሜዉ ከ40 በላይ የሆነ ነዉ ያሉኝ አሉ በዚህ በእድሜ የተነሳ እንዳላገቡ ነግረዉኛል፡፡ይሄ በኔ የሚወሰን አይደለም ትዳር የፍላጎት ምርጫ ስለሆነ ገብቶ ከመጨቃጨቅ ከመናናቅ የሚወዱትን መስፈርታቸዉን የሚያሟሉ  ማግባት የራሳቸዉ ምርጫ ስለሆነ በእድሜ የገፋ አግቡ ብየ ማስገደድ አልችልም....
ፈጣሪ ያሰባችሁትን ያሳካለችሁ ከማለት ዉጭ


☞ አዲስ አበባ AHF Addis clinic /kolfe clinic የሚባል ለም ሆቴል አካባቢ አለ HIV positive ለሆኑ ሰዎች ትዳር ያገናኛሉ ብለዉኛል ይሄ የኮሚሽን ግን ይቀበላሉ ብለዉኛል እንደ አማራጭ ይያዛል


☞ለታዋቂ ሰዎች ማድረስ በሚለዉ ደግሞ ለተለያዩ ፀሀፊዎች ለተለያዩ ኡስታዞች የትላልቅ ሚዲያ ባለሙያዎች በማድረስ ከአንድ በኔ ሀሳብ በምትሄደዉ የዲን እህቴ ጋር በመናበብ 80% ያሳወቀን በዚህ ዙሪያ የቻሉትን እንዲሰሩ ታገለን ነበር ያዉ የዘንድሮ ሙስሊም ከኢንሻ አላህ ዉጭ የሚሰራ የለም ኢንሻ አላህ ብለዉ ዘግተዉናል
የአሁን ብዙዉ ሙስሊም ኢንሻ አላህ ብሎ ወደ ግራ የሚሄድ ነዉ ምንም ማድረግ አልችልም በተቻለን አላህን ይዘን መታገል ብቻ ..አሁን ላይ ከዳኢዎች ከኡስታዞች ጥሩ ምላሽ መጠበቅ ከብዷል አላህ ለዚህ የዋህ ሙስሊም ኡማ ይድረስልን

☞ አንድ ብቻ ሙስሊም ወንድም የጤና ባለሙያ ሙስሊሞችን Hiv+ የሚያገናኝ አለ ግን አሁን ረመዳን ነዉ ከረመዳን ቡሀላ ብሎኛል ፡፡ ግን ከአገናኘሁ ቡሀላ እየተጣሉ እየተፋቱ ተቸግሪያለሁ ለምን ይሁን ይሁን ችግር የለም በሚል ከተጋቡ ቡሀላ ብዙዉ ሳይግባቡ ስለሚጋቡ ሲግባቡ ችግር እየመጣ በጣም ተቸግሪያለሁ አለኝ...እናም ከረመዳን ቡሀላ ብሎኛል እናም እዚህ ያላችሁ
Hiv + የሆናችሁ የቻናል ቤተሰቦች ፈርታችሁ ያልተናገራችሁ በዚህ bot አሳዉቂኝ የእሱን ስልክ ቁጥር እሰጣችሆለሁ በዚህ bot ያሳዉቁኝ

T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

☞  የተቸገሩን ኸይር መስራት የፈለገ Hiv+ ሆነ ከዛ ዉጭ ያሉ መርዳት የሚፈልግ ካለ እኔ ችግረኞችን በስልክ ወይ በtg acount አገናኛችሆለሁ ራሳችሁ መርዳት የምችሉበትን አመቻችላችሆለሁ ...እኔ ሚዲያ ላይ የማቃቸዉ በጣም ብዙ የተቸገሩ አሉ በራሴ አቅም የቻልኩትን ባደርግም ግን ብዙ ከአንድ ሰዉ አቅም በላይ ነዉ እናም ኸይር መስራት የሚፈልግ የተቸገረዉን እኔ ላገናኛችሁ ችግሩን ሁኔታ ራሱ ያስረዳችሆል የምረዱትን ቀጥታ እነሱ ጋር ማገናኘት እችላለሁ የመርዳት ንያዉ ያለዉ በዚህ bot ያሳዉቀኝ

T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

☞ደግሞ በተሻለ መልኩ የክርስቲያን ሀይማኖት የሰጡት ገንቢ አስተያየት ነበር እነሱን ሳላደንቅ አላልፍም...አሁን ላይ እነሱ ይሰራሉ ለሀይማኖታቸዉ ደስ ይላሉ እኛ ግን እነሱ ሰሩ ቦታ ተቀበሉ ብሎ ጫጫታ ነዉ ለእምነታቸዉ የመስራት ፈጣሪ ብለዉ ከያዙት ግዴታ ስለተሰጣቸዉ ይሰራሉ ሰሩ ብሎ እርይ አያዋጣም ይልቅ እኛ ኢንሻ አላህ እያሉ ከመሹለክ እንደ እነሱ ተናቦ መስራት ያዋጣል፡፡ እናም ከልምድ አንፃር ለሰጣችሁኝ አስተያየት ጥቆማ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡