Get Mystery Box with random crypto!

እህቴ ሆይ አስተዉይ ☞መጀመሪያ በአንቺ በቤተሰቦችሽ የመጣ ትዳር ፈላጊ ነዉ ተብሎ 75% ይታሰባል | ISLAMIC SCHOOL

እህቴ ሆይ አስተዉይ
☞መጀመሪያ በአንቺ በቤተሰቦችሽ የመጣ ትዳር ፈላጊ ነዉ ተብሎ 75% ይታሰባል
☞ነገር ግን በጓደኛሽ የመጣ ከሆነ ..አላህን የማፈራ የሙስሊምም ሆነ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ብትሆንም አንቺን ከእሱ በምታገኘዉ ጥቅማ ጥቅም  ልትሸጥሽ እንደሆነ 90% ይጠረጠራል፡፡ እናም ይሄ ልጅ ለአንቺ ያለዉ አመለካከት..ስለ አንቺ ጥሩ ነገር ያወራል ካለችሽ እባክሽ ተጠንቀቂያት ሴት ስትፈግ ሴትን በሴት እሾህን በእሾህ ነዉና..የአንቺ ጠቃሚሽም ጎጅሽም ሴት እህቶችሽ እንደሆኑ ሁሌ አትዘንጊ

ዉድና የተከበራችሁ ቤተሰቦች የማጠቃለያ ፁሁፍ በጊዜ ማነስ አስቤበት አላዘጋጀሁም ነገር ግን በታሪኩ ላይ ብዙዉን ጠቅሸዋለሁ...

መልካም ንባብ ተመኘሁ
አስተያየት አልቀበልም ለምን እራሴ ለራሴ መቋቋም የማይቻልበት አቅም ላይ ተሁኖ አስተያየት መቀበሉ ጥቅም የለዉም..ደግሞ በአስተያየት የሰዉ ልጅ መፅሀፍ ነዉ ብዙ የደበቀዉ አለ አንዳንዴ ስለምሰማ ራሴን መሆን እያቀተ የሰዉ ሀሲብ ሲጨመር ከባድ ነዉ የሚሆነዉ ፡፡ እናም በአስተያየት መስጫ bot ትችትም ጥሩ ሀሳብም ለወደፊት የሚስተካከል ብየ የምቀበለዉ የለኝም...መፃፍ አቁሚያለሁ ይሄም የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ለyoutuber እና ለቻናሎች በማሰብ ነዉ የበፊቱ 45 part ስለነበር ሳይዙን ቀንስልን ስላሉኝ ነዉ 2013 የተነበበ ታሪክ አሁን የተደገመዉ፡፡

ብዙ ቀን ለምን ታሪክ አታዘጋጅም ቻናልህ ሰዉ እየቀነሰ ነዉ ምናምን የሚል አስተያየት አያለሁ...እኔ አንድ ሰዉ ቻናል ላይ ቢቀር አይመለከተኝም እኔ እንደሙነሺዶች ዩቲዩብሮች በስሜ ነግጄ ብር ማግኘት አልፈልግም ሁሉም የራሱ አቋም አለዉ....እኔ የራሴ በጣም ቢዚ የሚያደርግ ስራ አለኝ ፁሁፍ በፊትም በትርፍ ሰአቴ ለሊት ነበር የማዘጋጀዉ እንደሙነሺዶች እንደ አንዳንድ ፀሀፊዎች ሚዲያ ለኔ ቀጥታ ስራየ ሳይሆን ትርፍ ሰአቴን ነዉ የተጠቀምኩበት፡፡ እናም ከቻናል መግባት መዉጣት የባለቤቱ ባለእጁ ዉሳኔ እንጂ ገና ቻናል ሰዉ ወጣ ብየ 100% ሁኜ ልንገራችሁ ለወደፊት የሚዘጋጅ ታሪክ የለም፡፡ብዙ እዉነተኛ ታሪክ በእጄ ነበር ግን ጥቅምና ጉዳቱን ሳነፃፅረዉ ለኔ ስላልተዋጠልኝ ላለመዘጋጀት ወስኜ ትቸዋለሁ፡፡ ይሄም የማይቀየር አቋሜ ነዉ፡፡

ብዙ ሀጃ አለኝ የሰዉ ልጅ ዱንያ ነዉ ይከፋል ይደሰታል..,የኔ መከፋቴ ማዘኔ ጨምሯልና ሙስሊም ወንድማችሁ ነኝ ዱአ አርጉልኝ..,,
እንደበፊቱ አሚር ሰይድ መሆን የማይቻልበት ላይ ነኝ ብቻ በዱአ እንደሚስተካከል አምናለሁ..ነብዩ ሰዐወ ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል ብለዋል ኢላህ ኢማኔ እንዲጨምር እናንተም በዱአ አትርሱኝ
መአሰላም

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ