Get Mystery Box with random crypto!

ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ታሪክ ጨርሰናል ፡፡እስኪ ስለታሪኩ ወን | ISLAMIC SCHOOL

ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች የሆድ ዉስጥ ፉም እሳት ታሪክ ጨርሰናል ፡፡እስኪ ስለታሪኩ ወንድሜችሁ አሚር ሰይድ የመሰለኝን ትንሽ ብቻ ልናገር ለምን አሁን ሰሚ የለም ሁሉም በራሱ አለም ላይ ነዉ ያለዉ

በዚህ ታሪክ ላይ ከሙሉ ፁሁፉ ቢያንስ 20% በራሴ አመለካከት ስላስገባሁ ታሪኩ በመሀል ያሉት የራሴ አመለካከት ስለሆነ ያበቂ ነዉ ግን በተጨማሪ
☞በአሁን ጊዜ በህፃንነታቸዉ ወይም አድገዉ ተገደዉ ሴት ልጅ መደፈር የሴት ልጅ ጥቃት በየሰፈሩ በየመንደሩ የቡና መጠጫ ወሬ ሁኗል..ይሄ ታሪክ በዚህ ሰለባ የሆነች እህታችን እዉነተኛ ታሪኳን አቅርቢያለሁ ግን ማወቅ ያለብን ከዚች ልጅ የባሰ ብዙ የሒወት ተራራን ለመግፋት የተገደዱ እህቶች አሉ ታዳ እነዚህን እህቶቻችንን ማን ነዉ ተርድቶ ከአእምሮ መጨናነቅ ዲፕሬሽን ሊያላቅቃቸዉ የሚችለዉ?? ዘመድ ቤተሰብ ወይስ ጓደኛ??? ወይስ እንደዚሁ ሰዉ ሲያያቸዉ እየሳቁ ብቻቸዉን እንዳለቀሱ እንዲኑሩ የተፈረደባቸዉ እህቶቻችንን ለማን አቤት ብለን ድምፃችንን በሰማን?? ለመንግስት ወይስ ለሀይማኖት አባቶች ወይስ ለፓለቲካ ፓርቲዎች?? ሁሉም ይሄን ግፍ ያወቀዋል ግን ለምን አሁን ድረስ መፍትሄ ለምን ጠፋ?? መቼ ድረስ ነዉ የሴት ልጅ ጥቃት የሚቆመዉ?? ይሄ ጥያቄ የሁሉም ሰዉ ጥያቄ ነዉ መልሱ ግን እስከ አሁን ከሰዎች አንደበት ሲመለስ ሰምቼዉ አላቅም ፈጣሪ የተሻለዉን ያዉቃል ብለን እንለፈዉ ..ግን ለወደፊት ይሄ ነገር መቅረት የሚችለዉ እንዴት ይሆን??እስኪ ሁሉም ብቻዉን ሰአት ሰጥቶ ይሰብበት....

በታሪኩ ላይ ድንግል አይደለሁም ተደፍሪያለሁ ብላ አስባ ስንት ትዳር ሲመጣ በልጅነቴ ተደፍሪያለሁ ለማለት ስትጠበብ ስትጨነቅ ስንት ስቃይ እንዳሳለፈች አይተናል..ግን ወንድሞቼ ለትዳር ቢክራ መሆን መስፈርት ነዉ ወይ?? በልጅነታቸዉ ሳይወዱ በግዳቸዉ የተደፈሩ..በስራ ብዛት ..በምቾት..በወር አበባ ብዛት አብሮ ድንግልናቸዉ የሚሄድ እህቶች እኮ በጣም ብዙ ናቸዉ..ታዳ ለእነዚህ ንፁህ እህቶቻችን ንፁህ ልባችንን ከፍተን የምንረዳቸዉ መቼ ይሆን ??
በጣም ማሰብ አለብን ይሄ ነገር እኮ እኛ ካልተረዳናቸዉ ለሌላ ሀይማኖት አጋልጠን ሰጠናቸዉ ማለት ነዉ..ለምን ድንግልና ለትዳር መስፈርት ያልሆነ ሀይማኖት ተከታዮች አሉና...


በዚህ ታሪክ ላይ የትምህርት ቤት ላይፍ አይተናል፡፡ የማይካድ ሀቅ ነዉ...አሁን ትምህርት ተዘግቶ ምነዉ ትምህርት በተከፈተ ብለዉ የሚናፍቁ ተማሪዎች ትምህርቱ ናፍቋቸዉ ሳይሆን ላይፉ ናፍቋቸዉ እንደሆነ ጥርጥር የለዉም፡፡ትምህርት ቤቶች ሴትና ወንድ አንድ ላይ እየተማሩ ይሄ ይቀራል ብሎ ማሰብ ቤንዚን ላይ እሳት ጨምሮ አይነድም እንደማለት ይቆጠራል ፡፡ ለምን ነዳጅ ለማስሞላት ገና ማደያ ስንገባ ስጋራ ማጨስ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ይዞ መግባት ክልክል ነዉ የሚል በማንኛዉም ማደያ ቦታ ተለጥፏል ፡፡ታዳ ሁሉም ማደያዎች ቅድመ ጥንቃቄ ማስጠንቀቂያዉ ተለጥፏል እኛስ ይሄን የወንድና የሴት አብረዉ እየተማሩ ዱርየ ቢሆኑ ይፈረዳል ወይ??? ግን አንድና አንድ መፍትሄ አለ ይሄም መፍትሄዉ በሁላችንም አእምሮ እና ጥረት የሚስተካከል ነዉ ብየ አስባለሁ .

እስኪ እኔ በራሴ ያጣራሁትን ልንገራችሁ፡፡ ደሴ ከተማ አንድ ጓደኛየ ሳዳትን በደንብ ያቀዋል ከሱ ነዉ ቂርአት የቀራዉ ብሎ አስተዋወቀኝ ከዛም ስለሳዳት ጥርጥር ያለብኝን ነገር ሁሉ ጠየኩት ልጁ ጋር የሚገርማችሁ 99% ተግባባን በጥሩም በመጥፎም ጎኑም ብዙ ነገሮች ተመካከርን ግን ትምህርት ኢህቲላጥ እያላችሁ ለምንድን ነዉ የምከለክሉት?ብየ ጠየኩት..ልጁም ሳዳት አይከለክልም የሚከለክለዉ የደሴዉ ሙስጠፋ ነዉ አለኝ፡፡ እኔም በጣም ቅርብ 6አመት ሙስጠፋ ኪታብ ያቀራዉን ልጅ ጠየኩት
ለምንድን ነዉ ኢህቲላጥ እያላችሁ ትምህርትን የምከለክሉት?? ብየ ጠየኩት
እሱም እንዲህ ብሎ መለሰለኝ ወደ ቁርአን ሀዲስ ስንመልሰዉ መደባለቅ አላህ ከልክሏል ፡፡ እና ነብዩ ሙሀመድ ሰዐወ እና አራቱ ኸሊፋዎች ዘመን ወንድና ሴት ተደባልቆ አልተማረም ..ደግሞ የበላዮች ህግ የሚለዉ ህገመንግስት እያልን ነዉ የምትማረዉ የበላዮች ህግ ግን ቁርአን ነዉ ..ይሄ ትምህርት ዱንያዊ እንጂ አኼራዊ አይደለም ብሎ መለሰልኝ
..እኔም መጀመሪያ እኮ ኢህቲላጥ ሀራም ነዉ ማለት ያለባችሁ ሴትና ወንድ የማይደባለቅበት ከፍታችሁ ነዉ መከልከል የምችሉት ስለዉ
እሱም ዱአ አድርግ በKGጀምረናል ለወደፊት አንደኛም ሁለተኛም ደረጃ እስከ ኮሌጅ ለመክፈት አስበናል:: በተጨማሪ የሙስሊም ሴቶች ሲወልዱ በሙስሊም ሴቶች እንዲወልዱ እስከ ሆስፒታል ድረስ በደሴ አስበናል አለኝ ፡፡ ከዚህ በላይ መጠየቅ አልፈለኩም አላህ ይገዛችሁ በአቅሜ የበኩሌን አደርጋለሁ አላህ ይገዛችሁ ብየ ጥያቄየን ጨረስኩ፡፡
☞አንድ ነገር ማወቅ ያለብን የሁሉንም የኢስላም ኡስታዞች ትምህርት ማዳመጥ ጠቃሚ ነዉ እኔ የሳዳትንም የሙስጠፋንም የነአቡበከር ያሲን ኑሩ ወዘተ በተመቸኝ አጋጣሚ አዳምጣለሁ ከሁሉም ኡስታዞች የሚጠቅመንን መያዝ እንጂ የአንድ ወገን አመለካከት ጨምድዶ መያዝ ሞኝነት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡

ለማንኛዉ አሁን ተደነጋግረናል ፈጣሪ ከድንግርግር ይጠብቀን....
አንዱ ባለፈዉ በደርግ ጊዜ የተማረ ወይ በ19 ክፍለ ዘመን የተማረ መሰለኝ እኔ እስከ 12 ተምሬ እስከምጨርስ 1000 ብር አልጨረስኩም ዛሬ ልጅ ትምህርት ቤት ይዞት የሄደዉ ከ3000 ብር በላይ ሁኗል ብሏል፡፡ እዉነት ነዉ ፓርሳ 1500-1000 ደብተር 800 የትምህርት ክፍያዉ እስክርቢቶዉ ሁሉ ሲሰላ ከ3000 ይበልጣል እናም በኑሮ ዉድነት ወጭ ወጥቶ እየተማሩ ወላጅ ቢከታተል ጥሩ ነዉ፡፡



ማወቅ ያለብን ጓደኛ ወሳኝነት ነዉ በታሪኩ ላይ ስለ ጥሩ ጓደኛ ብዙ ቦታ አስገብቻለሁ...
☞ሚፍታህ ነዋልን የጀመረዉ የሱፍ ዳረኝ ብሎት እንደሆነ አንብበናል.ሁሌም ቢሆን አደራ ለሀላል ከሆነ የምፈልጋት በጓደኛችሁ አደራ እንዳትጀምሩ ለምን የቅርብ ጓደኛህ አይሆን...ሴትና ወንድ ሲያወሩ ምን እንደሚፈጠር አናቅምና እሱ በአፉ በጣም ቀልጣፋ ከሆነ ሴት ልጅ ልቧ ያለዉ ጆሮዋ ላይ ነዉ ይባላል. እናም የሰማችዉን ሁሉ ስለምታምን አስታርቃለሁ ብሎ ገብቶ አፍኜ ብበላ ብሎ ከኳስ መጫወቻ ሜዳ ዉጭ ጠርዞ እንዳያወጣህ

እኔ ወላሂ ከዚህ ታሪክ ጋር የተያዘዘ እዉነተኛ ነዉ..
አንድ በጣም የምቀርበዉ ጓደኛየ ሌላ የእሱ አብሮ አደጉ ጓደኛ አለዉ..ጓደኛዉ አንዲትን ልጅ ይወዳታል ለትዳር እያወራት በመሀል በቀላል ነገር አለመግባባት ይፈጠራል..ላስታርቃችሁ ብሎ ተለሳልሶ ገብቶ አጣልቷቸዋል..ከዛም ለራሱ አድርጎ ሊያገባት ጫፍ ደርሶ ደግሞ ተጣልተዋል፡፡ ግን አስታርቀኝ ያለዉ ልጅ ጓደኛዉ ነዉ እየደበረዉ እየገረመዉ ትችታለሁ ለአንተ ትሁን ብሎ አዝኖ መጥፎም ክፉም ሳይናገረዉ ጓደኝነቱን ሰረዘዉ ..እኔም ወላሂ ይሄን በማድረጉ ባልጣላዉም ግን ለወደፊት እንዳላምነዉ አድርጎኛል..ለምን ነገ የሚሆነዉ አይታወቅምና፡፡
☞ እናም የቻናል ቤተሰብ ምርጥ ወንድሞቼ ለትዳር የሰብካትን ከተጠላህ በሁለታችሁ ብቻ ይፈታ..በሀሳብ ማመን በመነጋገር ማመን አለባችሁ ሚስጥር ከሁለታችሁ ከወጣ ሶስተኛዉ ሰዉ ለምን ይደብቀዋል?? ለምን ከእናንተ አልፏላ... በሁለታችሁ ችግራችሁ  ካልተፈታ ገና ዉስጥ ለዉስጥ አልተናበባችሁም ማለት ነዉ፡፡ አላህ ያግባባችሁ ሌላ ካግባባችሁ በጣም ግራ ነዉ የሚገባችሁ. ችግርን ሁለታችሁ ተነጋግራችሁ መፍታት ካልቻላችሁ ነገ ስትጋቡ ብትጣሉ አስታራቂ ካልተገኘ አራተኛዉ የአለም ጦርነት ፈጠራችሁ ማለት ነዉ