Get Mystery Box with random crypto!

ዱአየም...... >>>>>>>>> የፈጠርከኝ ጌታየ አላህ ሆይ!!!! እባክህ እርዳኝ ደካማህ ባሪያህ | ISLAMIC SCHOOL

ዱአየም......
>>>>>>>>> የፈጠርከኝ ጌታየ አላህ ሆይ!!!! እባክህ እርዳኝ ደካማህ ባሪያህ ነኝ ;ካሊድ ከሁሉም ወንድ የተሻለ ነዉ ለኔም የተሻለ ሰጥተህኛል አቃለሁ ...ማንም ከሚወደኝ በላይ ይወደኛል ..ማንም ሳያከብረኝ እሱ ግን አክብሮኛል ....የእኔ እና እሱን የመጨረሻዉን በሰላም አርገህ አሳየኝ...ማንነቴን ነግሬዉ ከተቀበለ አልሀምዱሊላህ እሰየዉ .ነገር ግን ማንነቴን የማይቀበለኝ ከሆነ በዱንያ መሬት መኖር አልፈልግም ;እኔም ታንቄ መርዝም ጠጥቼ መሞት አልፈልግም አንተዉ እንደፈጠርከኝ ግደለኝ ... ጌታየ ሆይ ወድጄ አይደለም...ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም፡፡ ስቃየ በዛ እኔም ተሳቅቄ በማንነቴ ተሸማቅቆ መኖር በቅቶኛል ፡፡ ሞትን የመረኩት ምክንያት አለኝ ------ ማንነቴን የሚቀበለኝ ከሌለ በዱንያ ላይ ወንድን አልፈልግም #አንተዉ_በጀነት_ላይ_አንተን_ሲገዛ_የኖረ_አንተ_ከምወደዉ_ባሪያህ_መርጠህ_ታጋባኛለህ ..የማገባዉ ጀነት ዉስጥ ብቻ እንዲሆን ነዉ የምፈልገዉ ...መቼም ይሄንን ሁላ ግፍ አሳልፌ ከልጅነቴ ጀምሬ ሳለቅስ ኑሬ ስጨናነቅ ኑሬ በዱንያ የሀሳብ እና በእንባ ጎርፍ በአንተዉ ዉሳኔ ተቀጥቼ....እራሴን አጥፍቼ አንተ ጋር ብመጣ  ይሄንን ሁላ ግፍ ለቅሶ አሳልፌ በአንተ ራህመተህ እዝነትህ የጀሀነም እንደማታደርገኝ እርግጠኛ ነኝ..... ለነገሩ ምን እርግጠኝነት አለ??? አንተዉ ፈጥረሀኝ ወደ አንተዉ ተመላሽ ነኝ ምን ዋስትና አለኝ??? የሰዉ ልጅ ለመሞት አንድ ስንዝር ስትቀረዉ በአላህ ሲያምፅ ኑሮ የጀነት ስራ ሰርቶ ጀነት የሚገባ እና በተዘዋዋሪ የጀነት የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ለመሞት አንድ ስንዝር ስቀረዉ የጀሀነም የሚያስገባ ስራ ሰርቶ ጀሀነም የሚገባ አለ ....እራሱን ያጠፋም ጀነት እርም እንደሆነ አቃለሁ ብቻ አንተዉ ጠብቀኝ እኔም ግራ ገባኝ፡፡ #አላህዋ ካሊድ የኔን ማንነት የማይቀበል ከሆነ እዚሁ ሱጁድ ላይ እንዳለሁ ግደለኝ ..ሂወት በቃኝ ግደለኝኝኝኝ  መኖር አልፈልግም ይበቃኛል፡፡  እስከ አሁን ደስተኛ ሁኜ የኖርኩበት ቀን የለኝም...የኔ ደስታ አንተ ያዘጋጀህልኝ ጀነት ነዉ ጌታየ አንተዉ ሽማግሌ ሁነህኝ ደስታየን በጀነት ወንድ አርግልኝ ....,እየደጋገምኩ እየደጋገምኩ ካሊድ ማንነቴን የማይቀበለኝ ከሆነ ግደለኝ መኖር አልፈልግምምም እያልኩ ስጁድ ላይ እማባየን አፈስ ይዣለሁ
 
ካሊድ በቀን አንዴ እየደወለ አረ አስጨነቅሽኝ ምን ሁነሽ ነዉ??? ንገሪኝ እያለ ይጠይቀኛል
.....እኔም ሀሙስ ተባብለናል ሀሙስ ሲደርስ እነግርሀለሁ እለዋለሁ፡፡


የማይደርስ የለም የፈራሁት ዱአ ያረኩበት ልነግረዉ የወሰንኩት ቀን ሀሙስ ደረሰ ..
....ካሊድ ጋር ተገናኘን ወሬዉን ለመስማት ቸኩሏል፡፡ሰንገናኝ የምንዝናናበት ቦታ እንሂድ እንዴ??? አለኝ
......እኔም አንተ መኖሪያ ቤት ይሻላል አልኩት..,ምክንያቱም በመንገድ ስመጣ ወይም እዛ ማልቀሴ የማይቀር ነዉ ሰዉ እይታ እንዳልገባ በማሰብ ነዉ መኖሪያ ቤቱን የመረጥኩት
....እሱም እስከዛሬ ወንድ ቤት አልሄድም ብየ ስላስቸገርኩት . ..እርግጠኛ ነሽ እኔ ቤት እንሂድ??? አለኝ
......እኔም አዎ አንተ ቤት ነዉ የምነግርህ አልኩት
..............እሺ መርሀባ ብሎኝ ወደ እሱ ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ ፡፡ ግን ምን ሁነሽ ነዉ?? ንገሪኝ በጣም ተጨነኩኝ እቤት እስከምደርስ አላስቻለኝም አለኝ
.......እኔም ምንም አልሆንኩም ቤት ስንድረስ ብነግርህ ይሻላል አልኩት .
ከዛም በመኪናዉ መኖሪ ቤቱ ወሰደኝ
..... እቤት እንደገባሁ ብዙም የተካበደ ሳይሆን የወንደ ላጤ ግብዣ ጋበዘኝ እና...የኔ ፍቅር ምንሁነሽ ነዉ ???ንገሪኝ እኔም በጭንቀት አለኩኝ እኮ ስራ መስራት አልቻልኩም አለኝ

....እኔም ለመናገር ምራቄን ዋጥ አርጌ ምላሴ ለመንገር እየፈራ እየተንቀጠቀጠ መንገሬን ጀመርኩ....ካሊድ አንንተተ ምን ያህል እንደምወደኝ እንደ እንደደደ ምታፈቅረኝ  አቃለሁ ፡፡ አፈቅርሀለሁ ብየ ባልዋሽህም እወድሀለሁ አንተተተን ማማማጣት አልፈልግም ....አንድ ስለ እእእእኔ ማንነት የምነግርህ አለ ይሆናልልልል ብለህ የማጠብቀዉ ነዉ፡፡
  
ለካሊድ ባለፈዉ ያረገልኝን ቀለበት አዉጥቼ ሰጠሁት ፡፡አሁን የምነግርህን የማትቀበለኝ ከሆነ ቀለበቱን እንደያዝከዉ ለኔ አታድርግልኝ ዝም ብለኝ ...ምንም አስተያየት ጥያቄ አንዳታነሳብኝ ..እንዴት ለምን ሆነ ??እያልክ ታሪኩን  እንድጠይቀኝ አልፈልግም...ከቤት ዉጪ በለኝ ከቤት እወጣለሁ ደግሜ በሒወትህ በጭራሽ አልገባም ከአሁን ቡሀላ በጭራሽ አንገናኝም ..ብሞት ለራሱ ነዋል አላህ ይርሀማት ብለህ ለመቅበር እንዳትመጣ
....እሱም አረ ምንድን ነዉ ነገሩ?" አስጨነቅሽኝ አለኝ
.......,እኔም እስከማንነቴ ለመቀበል ለመወሰን ጊዜ እሰጥሀለሁ ይሄ ነገር ቀልድ አይደለም፡፡ አንድ ቀን ፈጣሪ ካለ አንድ ላይ ሁነን ትዝ ብሎህ ወይም ከተጋባን ቡሀላ ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ??ብለህም እንድትጠይቀኝ አልፈልግም...በጠቅላላ ዛሬ ከነገርኩህ ቡሀላ፡ዳግመኛ ይሄን ወሬ ማዉራት አልፈልግም አልኩት፡፡
ይሄን ወሬ ለመስማማት ወይም ለመተዉ 24ሰአት እሰጥሀለሁ ..አሁን 8:00ነዉ አይደል ??? አልኩት
.....እሱም አዎ አለኝ
.....እኔም ነገ ጁምአ 8:00 ላይ ደዉለህ ዉሳነኔህን ታሳዉቀኛለህ ፡፡ ከስምንት ሰአት አንድ ደቂቃ ካለፈ ሀሳብህ አልፈልግሽም ስለሆነ እንዳትደዉል መቼም ይቅር ልልህ አልችልም አልኩት
....እሱም ደነገጠ አረ ምን ሁነሽ ነዉ???ይለኛል
......በቃ ልነግረዉ ነዉ......የስንት አመት የታፈነዉን የሆድ ዉስጥ ፉም እሳቱን ልነግረዉ ማልቀስ ሆነ ስራየ... ልረጋጋ አልቻልኩም እምባየ እንደወራጅ ወንዝ ይጓዛል ...ካሊድ አላስቻለዉም አብሮኝ ያለቅሳል አረ ንገሪኝ የአንቺን ሀዘን ማየት አልችልም እያለ መላቀስ ይዘናል

እኔም መናገር አቃተኝ እንዴት ብየ ቃላት አዉጥቼ ልንገረዉ ?? ሁለታችንም እየተያየን መላቀስ ሆነ ፡፡ አፌ ተያያዘ ልጅ ሁኜ ተደፍሬ ነበር ብየ እንዴት ብየ ልንገረዉ ???.ከዛም አንድ ሀሳብ መጣልኝ ስልክህን ያዝ text አሁን እልክልለሁ አንተ የምትለኝ እዉነትሽን ነዉ ...ብቻ በለኝ ጥያቄ እንዳታበዛብኝ  አልኩት
....እሱም እሺ አለኝ
.........እኔም ሳይበዛ በmessage በአራት አመቴ በጎረቤት ልጅ ተደፍሬ ነበር የነገረችኝ የቤት ሰራተኛችን ናት..አባቴ የጎረቤታችን ልጅ በልጅነትሽ የተደፈርሽዉ ብላኝ አባቴ በሽጉጥ ሊገላት ነበር ብየ በአጭሩ ፃፍኩለት
....ካሊድ እየደጋገመ የላኩለትን Message አነበበዉ አነበበዉ ...በአንዴ ፊቱ ተቀያየረ መናደዱ ፊቱ ላይ ያስታዉቃል ከንፈሩን በፊት ጥርሱ ነክሶ ፍጥጥ ብሎ ያየኝ ጀመረ.... ..እንም የካሊድን ለኔ ያለዉን አመለካከት ስመለከት በጣም ደነገጥኩ፡፡ ከመደንጠጤ የተነሳ ልቤ ከቦታዉ ተነቅላ የሄደች ነዉ የመሰለኝ .... ምን ይደረጋል የፈራሁት ስጨነቅበት የነበረዉ ነገር ደረሰ


#ክፍል
ይ.........ቀ........
.......ጥ .........ላ...........ል


    Join     `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•