Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ ሶስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ

የለበስኩትን ቀለበት ብቻ አይተዉ ነዋል ልታገባ ነዉ የሚል ወሬ በእኛ ሰፈርና በኮሌጅ ሳይቀር በአንዴ ተናፈሰ...

በመንገድ ያገኘኝ ሰዉ ነዋል ልታገቢ ነዉ እንዴ?? ብሎ ሲጠይቁኝ.... አብሽሩ መቼም ሰርጉ ሲደርስ እናንተን ጥየ ያገባሁት ሰርግ... ሰርግ ሳይሆን ሀዘን ነዉ ዱአ አድርጉልኝ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን አይቀርም እያልኩ ለሰዎች እመልስላቸዋለሁ፡፡

  ሁሌም ከካሊድ ጋር በሳምነት ጁምአ ከአሱር ቡሀላ ስንገናኝ ልንገረዉ አልንገረዉ እያልኩ ብቻየን አስባለሁ ..ግን ከምኑ እጀምራለሁ??አፍ አዉጥቶ ለመንገር አንደበቴን ይሳናል .....


አላህ ይርዳሽ በሉኝ ለሚመጣዉ ሳምንት ካሊድ በሚመቸዉ ቀን ቀጠሮ ይዤ ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግረዉ ወሰንኩኝ...

   ሰኞ ጠዋት ለካሊድ ደዉየ በጣም እፈልግሀለሁ የማወራህ አስቸኳይ ጉዳይ አለ  አልኩት
.....እሱም ስራ ላይ ነኝ ዛሬ አይመቸኝም ምን አልባት እሮብ እና ሀሙስ ልቀር እችላለሁ ...ለምን ጁምአ በሳምንት የምንገናኝበት ቀን ነዉ ጁምአ አነግሪኝም ወይ ?? አለኝ
.....,እኔም ጁምአ እኮ የደስታችን ቀን ነዉ አሁን የምነግርህ የተደበቀ ሚስጥር ለጁምአ የሚነገርበት ቀን አይደለም አልኩት
......የምነግሪኝ የሀዘን ነዉ ማለት ነዉ???? ...አታስጨንቂኝ አሁን ንገሪኝ አለኝ
.........እኔም ዝም አልኩት፡፡
....እሱም ሀሙስ ከሰአት ስራ አልገባም እንገናኛለን ትነግሪኛለሽ አለኝ.....
...እኔም ኢንሻ አላህ ብየ የስልክ ወሬያችንን ጨረስን

ከካሊድ የምወድለት ሶስት ባህሪዎች አሉት የመጀመሪያዉ ምንም ነገር ቢፈጠር በስራ ቀልድ አያቅም ስራ ስራ ነዉ የሚለዉ ደግሞም ስራ አይመርጥም ሁለተኛዉ በጭራሽ አይዋሽም ሶስተኛ አይደብቅም ለምሳሌ አንዳንድ ሰዉ ስታጠፋ መስመር ስታልፍ የሚደብቅልህ አለ እሱ ግን ሀቅ ከሆነ ከፈለገ ቅር ይበልህ እንጂ እሱ ነዉርን ካየ ፊለፊት ነዉ የሚናገረዉ ይሄ ባህሪዉ ይመቸኛል ፡፡

  ስልክ አዉርተን ብንጨርስም ካሊድ እየደወለ በጣም አስቸገረኝ ምንድን ነዉ የምነግሪኝ??? ነዋል እባክሽ ንገሪኝ በሀሳብ ልሞት ነዉ?? ስራ መስራት አልቻልኩም እያለ በየሰአቱ እየደወለ ነዉ፡፡ እኔም ተጨኔቄ እሱንም አስጨነኩት
....እኔም ይሄንን ሀሳብ ተረጋግቼ ማሰብ ስላለብኝ እሱም እየደወለ ሲያስቸግረኝ ...ካሊድ እኔም ለራሴ ሀሳብ ላይ ነኝ በአላህ አንድ ነገር ተባበረኝ???አልኩት
.....እሱም ምን ልተባበርሽ ??? አለኝ.....
....,እኔም ሀሙስ እስከሚደርስ በተደጋጋሚ አትደዉል በቀን አንዴ ከደወልክ ይበቃል በዚህ ተባበረኝ አልኩት
......እሱም ጭራሽ የማይሆን ነዉ እኔም ተጨንቂያለሁ..,የኔ በተደጋጋሚ አለመደወል አሁን ለአንቺ ሰላም የሚያረግሽ ከሆነ እሺ ሳልወድ በግዴ የተናገርሽዉን አከብራለሁ አለኝ
....በዚህ ሀሳብ ተስማማ

እኔ ይሄን ያልኩበት ምክንያት ካሊድ በኔ ፍቅር በጣም እየተጎዳ ስለሄደ ...በቀን አንዴ ከደወለ ይበቃል ..እኔ ስነግረዉ እንደማይቀበለኝ አቃለሁ በዚህ የተነሳ እኔን እየረሳኝ ይሄዳል ብየ አሰብኩኝ ፡፡ካሊድ በቃሉ መሰረት በቀን አንዴ መደወል ጀመረ

   እኔም መደወል ሲያቆም ትንሽ ጊዜ አገኘሁ ወላሂ ቢላሂ ቀን ማታ ማልቀስ ሆነ ስራየ ፡፡ ለሊት እየተነሳሁ ሶላት እየሰገድኩ ወላሂ ዱአ እያረኩ አለቅሳለሁ፡፡ ሶላተል ሀጃ ሶለተል ኢስቲሀራ አየሰገድኩ በቂያምም በሩኩኡም በሱጁድም እያለቅሱ አላህን እጠይቀዉ እለምነዉ ይዣለሁ አላህ እርዳኝ ካሊድ ማንነቴን እንዲቀበለኝ እርዳኝ .... ሁሌ ደካማ አታርገኝ አሁንስ ደከመኝ ማን ማንነቴን ይረዳኝ ??ጌታየ እኔንም በማንነቴ ካሊድንም በፍቅር አታሰቃየን ፡፡ እያልኩ ዱአ ማድረግ ተያይዠዋለሁ...እናንተም በዱአችሁ አትርሱኝ

★★★ ዱአ
ዱአ በሀይማኖታችን ዉስጥ ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉ ሲሆን እኛን የሰዉ ልጆች ደካማነትና ረዳት የለሽነት በመለኮታዊ ችሎታ ፊት የማቅረቢያ መንገድ ነዉ።

አንድ ባሪያ ጉዳዮቹን ይፈፅምለት ዘንድ ወደ ሀያሉ አላህ ፊት ይዞ ሲቀርብ ከቃላት ማነብነብ ባለፈ ልባዊ በመሆንና ፊትን ወደ አላህ በማዞር መሆን አለበት። ይህም ሲሆን ሁል ጊዜም ቢሆን አላህን በመፍራትና ምህረቱንም ተስፋ በማድረግ መካከል መሆን ግድ ነዉ። ለምሳሌ አንድ አማኝ አላህ ሀጥያቱን እንዲምረዉ ከፈለገ በዱአዉ ዉስጥ ሙሉ ትኩረት ማድረግና ጉዳዩን በሙሉ ልቡ ለፈጣሪዉ ማቅረቡን ማረጋገጥ ይኖርበታል። በፀፀት በተቃጠለ ልብና እንባ የሚያወርዱ አይኖች የፈጣሪን ትኩረት የማግኘት እድላቸዉ ሰፊ ነዉና።

በሁሉም አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች አንድ አማኝ የአላህ ባሪያ መሆኑን ከሚያረጋግጥባቸዉ መስፈርቶች አንዱ ሁል ጊዜም እርሱን መለመን መቻሉ ነዉ። ባሪያ የመሆን ሚስጥሩና የእዉነተኛ አምልኮት አስኳል የሚገኘዉም አላህን በተከታታይና በዘዉታሪነት በመለመን ነዉ። ምክንያቱም ሶላትና ዱአ ወደ አላህ የሚወስድ ወሳኝ መንፈሳዊ መንገዶች ናቸዉና።

አላህ በተከበረ ቃሉ በቁርአን እንዲህ ብሏል
ባሮቼ ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ(እንዲህ በላቸዉ)""እኔ ቅርብ ነኝ የአማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ።ስለዚህ በእኔ ይታዘዙ በእኔም ይመኑ እርሱ ሊመሩ ይከጂላልና""(አል በቀራህ186)

ተወዳጁ የአላህ መልክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰላታቸዉ በተጨማሪ እንባቸዉን እያፈሰሱና በመቆም ተረከዛቸዉ እስከሚያብጥ ድረስ አላህን በፅኑ ይማፀኑና ይለምኑ ነበር። አጭርና ልባዊ የሆነን ዱአ የመዉደዳቸዉን ያህል ከልብ ያልሆነን ማነብነብ ይጠሉ ነበር። ተከታዮቻቸዉም እንደሚከተለዉ በማለት ይመክራሉ።
""ባሪያዉ ወደ ጌታዉ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነዉ ሱጁድ ላይ ሲሆን ነዉ። ስለዚህ ሱጁድ ባደረጋቹህበት ጊዜ ብዙ የምትፈልጉትን ነገር አላህ ያሳካላቹህ ዘንድ ለምኑት"" ብለዉናል፡፡

አንድ አማኝ ሁል ጊዜም በዱአ አላህን በመለመን መትጋት የሚገባዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ በእምነት ወንድሙ የሆነ ሰዉም ዱአ እንዲያደርግለት መጠየቅ ይኖርበታል። ይህ ሰዉ ምናልባትም ድሀ፤ደካማ፤ችግረኛ...ቢሆን እንኳን አላህ የእርሱን ልመና ሊሰማዉ ይችላል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ(ሰ.ሰ.ወ) እንዲህ ብለዋል።
"" አንድ ሙስሊም ለሌላዉ ወንድሙ በሌለበት ከሚያደርግለት የበለጠ በፍጥነት ተቀባይነትን የሚያገኝ ዱአ የለም።(ቲርሚዝ) እናንተም በዱአ አግዙኝ
ከሰኞ ጀምሬ ሀሙስ ድረስ ትምህርት ሳልሄድ እቤቴ እየዋልኩ ከሶላት በፊትም ቡሀላም ዱአ ላይ ነኝ ፡፡ ወላሂ እነዚህ ቀናቶችን ዳግመኛ በሒወቴ ላይ ማሰብ አልፈልግም በጥላቴም ላይ በጭራሽ አልመኛቸዉም .ጠዋት ጀምሬ እስከ ማታ ይሄም አልበቃኝ ብሎ አዳሬን ማልቀስ ሆነ የኔ ነገር፡፡ እንቅልፍ አስተካክየ መተኛት እንኳን አልቻልኩም አይኔ አለመፍረጡም የጉድ ነዉ፡፡


የሚገርማችሁ እያለቀስኩ ዱአ ሳደርግ ምን ብየ ዱአ እንደማደርግ ታቃላችሁ?? ከሁሉም ሰዉ የተለየ ዱአ ነበር የማደርገዉ